DiscoverDW | Amharic - Newsዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ ዓውደ ጥናት
ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ ዓውደ ጥናት

ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ ዓውደ ጥናት

Update: 2025-10-21
Share

Description

ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ



በአፍሪካ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ በመጣ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ጎርፍ፣ ድርቅ እናየውኃ እጥረት የከፋ ጉዳት እየደርሰ ነው። በአፍሪካ እስካሁን በቂ እና ትክክለኛ መረጃ አለመኖር እና የመርጃ አሰዳደር ሥርዓት አለምኖሩ በተፍጥሮ እና በአየር መዛባት ምክንያት ለሚምጡ ችሮች ምፍትሄ ለማግኘትም ሆነ ቸግሮች ከመፍጠራቸው በፊት ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዳልተቻለ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህንን ችግር ለማቅረፍ ይርዳል የተባበለት ‘’በአፍሪካ የውኃ አስተዳደር የዲጂታል ቴክኖሎጂ መፍትሔዎች" በሚል የሦስት ቀናት አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የአፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦች ለማሳካት አፍሪካ ያለባትን የውኃ መረጃ ክፍተት ችግር መቅረፍ አለባት ለዚህ ደግሞ ዘመኑ ያመጣውን ዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ በዓውደ ጥናቱ ተገልጿል።



የውኃ መረጃ በበቂ ሁኔታ አለመኖር





ቡርኪና ፋሶ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ዛምቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ተሳታፊ የሆኑበት የባለድሻ አካልት ያካተተ ይህ ስብሰባ የሳተላይት ዳታ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል የመስሪያ ስርአቶችን በመጠቀም ሀገራት እቅዳቸውን እንዲያሻሽሉ፣ የውኃ አደጋዎችን አስቀድመው እንዲተነብዩ እና ህዝባቸውን ከአየር ንብረት ለውጥእና ከውኃ አመጣሽ ችግሮች እንዲታደጉ የሚያስችሉ መረጃዎችና አሰራሮችን ይመረመራል ተብሎዋል። ዶ/ር አብዱልከሪምሁሴን ሰይድ የዓለም አቀፉ የውኃ አስተዳደር ተቋም (IWMI) የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ሲናገሩ

«ሀገራት የአየር ንብረትበተለይ ከውኃ ጋር በተገናኘ ለሚሰሩት ስራ በቂ መረጃ ያስፍልጋቸዋል። መረጃ ቁልፍ ነው፤ ኢትዮጵያ እድገትዋን ለማፋጠን ተፈጥሮ የሚሰጣትን የውኃ ጠብታ ቋጥራ እና ቆጥባ መጠቀም ይኖርባታል። ለዚህ ደግሞ ቴክኖሊጂን መጠቀም አማርጭ የሌለው መፍትሄ ነው።»





ከዓውደጥናቱ ምን ይጠበቃል

የውኃን ሀብትን ይበልጥ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር የሚያስችል አዳዲስ መንገዶችን የቀረበበት ሲፖዚየም በዓለም አቀፉ የውኃ አስተዳደር ተቋም (IWMI) እና ዲጂታል ኧርዝ አፍሪካ (DE Africa) የተባሉይት ድርጅቶች በጋራ ያሰናዱት ሲሆን ከነገ በስቲያ ሲጠናቀቅ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ተመራማሪዎችን እና ዲጂታል አበልጻጊወችን በማገናኘት በዳታ የሚመሩ መሳሪያዎችን ተቀባይነት ከማፋጠኑም በላይ በውኃ አስተዳደር ውስጥ ለዲጂታል ለውጥ የሚረዳ አህጉራዊ ፍኖተ ካርታ ይቀርጻል ተብሎ ይጠበቃል ።



ሐና ደምሴ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ ዓውደ ጥናት

ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ የውኃ አያያዝ ዓውደ ጥናት

ሐና ደምሴ