DiscoverDW | Amharic - Newsድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ አረፈች
ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ አረፈች

ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ አረፈች

Update: 2023-05-12
Share

Description

ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም ድካም በአጸደ ሥጋ ዛሬ ተለየች። ድማጻዊት ኂሩት በቀለ በፖሊስ የሙዚቃና ትያትር ክፍል ለ35 ዓመታት ያገለገለች ሲሆን ከ200 በላይ ዘፈኖችን ማበርከቷን ለማወቅ ተችሏል።



ይህ ፍቅርን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ጀግንነትን ያደመቀ፤ ያሞካሸ ልሳን ላይመለስ ተዘጋ፤ ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ። ድምጻዊት ኂሩት በቀለ ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1980ዎቹ አካባቢ ከ200 በላይ ዘፈኖችን ያበረከተች አንጋፋ ድምጻዊ እንደነበረች በእሷ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አሻራ ያኖሩት አንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ አበበ ለዶቼ ቬለ /DW/ ተናግረዋል።



" በፖሊስ ሰራዊት የሙዚቃ ክፍል ከ1953 ዓመተምህረት ጀምሮ ከ30 ታት በላይ አገልግላለች። በዚህ ጊዜ ውስጥ የዘፈነችው የፍቅር ዘፈኖች በጣም ጥቂቶች ነበሩ አብዛኛውቹ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለኢትዮጵያ ጀግኖች ነው የዘፈነችው።"



በፖሊስ የቲያትርና የሙዚቃ ክፍል ባልደረባ ሆና በሠራችባቸው ጊዚያት ሠራዊቱን ግንባር ድረስ በመሄድ አጀግናለች፤ ስለሐገር መስዋዕትነት ክብርና መዓርግ በጥበባዊ አንደበቷ አቀንቅናለች። አንዳንዴም መድረክ ላይ እየዘፈነች ጥይት በጆሮዋ እያፏጨ ሲያልፍ እንኳን በተመስጦ እንባዋ እየወረደ ጭምር ሠራዊቱን ታጀግን እንደነበረ አርቲስት ተስፋዬ አበበ ያዩትን በእማኝነት ያስታውሳሉ።



"የኪነት ቡድኑ ካራማራ ድረስ ሄዶ ስራዎቹን ሲያቀርብ ጥይት ሲያፏጭ ሙዚቀኖቹ ጥይት ይመታናል ብለው ቁጭ ብለው ሲጫወቱ እሷ ግን ቆማ ``ሺ ገድሎ ከድንበሩ ላይ፤ አልፏል ያ ጀግና ተጋዳይ`` እያለች እንባዋን እያፈሰሰች ነበር የዘፈነችው፤ ይህ እራሴ ያየሁት ው።"



ጽምጻዊት ኂሩት በቀለ በፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃና የቲያትር ክፍል ለ35 ዓመታት አገልግላለች። ኂሩት በአብዛኛው የአገር ፍቅርን ከሚቀሰቅሱ ዘፈኖቿ መካከል «ኢትዮጵያ» ፤ ስለሕይወት ካዜመቻቸው ደግሞ «ሕይወት እንደ ሸክላ» ፣ የሚለውና ሌሎች ጆሮገብ የሙዚቃ ሥራዎቿ አሁንም ድረስ ተወዳጅነትን ያልተለያቸው ድንቅ ሥራዎቿ ናቸው። ኂሩት በቀለ ወደ 40 የሚጠጉ የሙዚቃ ሸክላዎችንና 14 ካሴቶችን ታትመውላታል። ድምጻዊት ኂሩት በቀለ በግል ሕይወቷም ርህሩህና ለሰው ሟች እንደነበረች አንጋፋው አርቲስት ተሰፋዬ አበበ ነግረውናል።



ድምጻዊት ኂሩት በቀለ የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችው በ83 ዓመቷ ሲሆን የ7 ልጆች እናት፤ እና ቅድመ አያትም ነበረች። ባደረባት ህመም በአገር ውስጥና በውጭ ስትታከም ከቆየች ቦኋላ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ታውቋል።



ዶይቼቬለ በድምጻዊት ኂሩት በቀለ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቿና አድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ አረፈች

ድምጸ መረዋዋ አንጋፋ ድምጻዊት ኂሩት በቀለ አረፈች