DiscoverDW | Amharic - Newsበሰንዳፋ በአሰቃቂ የተገደለችዉ የሁለት ታዳጊዎች እናት ጉዳይ
በሰንዳፋ በአሰቃቂ የተገደለችዉ የሁለት ታዳጊዎች እናት ጉዳይ

በሰንዳፋ በአሰቃቂ የተገደለችዉ የሁለት ታዳጊዎች እናት ጉዳይ

Update: 2025-12-19
Share

Description

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰንዳፋ ከተማ ሰኞ ምሽት በጾታዊ ጥቃት የተገደለችው እናት ጉዳይ በበርካቶች ዘንድ ኀዘን እና ቁጣን ቀስቅሷል። የሰንዳፋ ከተማ ነዋሪዋ አዳነች ኩምሳ የተባሉ ሟች ከሰንዳፋ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አለልቱ ቅርንጫፍ ሠራተኛ ነበሩ፡፡ ሰኞ ታኅሣሥ 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ማምሻውን በሰንዳፋ መፈጸሙ የተነገረለት የዚህ አሰቃቂ ግድያ ተጠርጣሪ እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር አለመዋሉም ተሰምቷል፡፡



በሰንዳፋ ከተማ እየኖሩ ወደ አለልቱ ከተማ ተመላልሰው በኢትዮጵያ ንገድ ባንክ ሠራተኛ የነበሩት ዓለምነሽ ኩምሳ የተባሉ ሟች ለብቻቸው ሆነው ሁለት ልጆቻቸውን በማሳደግ ላይ እንደነበሩ ዶይቼ ቬለ ከቤተሰቦቻቸውና ባለሥለልጣናት ተረድቷል፡፡



«የአሰቃቂው» ወንጀሉ መፈፀም

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የሟች ታላቅ ወንድም አቶ ካሳሁን ኩምሳ አሰቃቂ ያሉትን የግድያውን መፈጸም እንዲህ አብራርተዋል፡፡ «ጸጋዬ አሳልፈው የሚባል» ተጠርጣሪ ከዚህ በፊት ሟች በምታገለግልበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አለልቱ ቅርንጫፍ ከተዋወቃት በኋላ ለጾታዊ ግንኙነት ለመቅረብ ሲፈልግ ሟች ልጆች እንዳሏትና ጥያቄውን መቀበል እንደማትችል ስታስረዳ በጣሙን ሲያስቸግራት እንደነበር ገልጸዋል፡፡



ከሁለት ልጆቿ ጋር ለብቻዋ ከቤተሰብ ተነጥላ ሕይወትን የምትገፋው አዳነች ይህንኑን ለፖሊስ ጓደኛዋ ብታስረዳም ባሳለፍነው ሰኞ ከአዲስ አበባ ስልጠና ወስዳ ስትመለስ ተጠርጣሪው በመንገድ ላይ በመጠበቅ አስገድዶ እራት ካልበላሽ ይላታል፡፡ ተገዳ ምግብ ቤት የገባችው አዳነችም እራቱንም ሳትበላ ሮጣ ልታመልጥ ስትል ተጠርጣሪው ተከታትሏት በጥይትከገደላት በኋላበቱቦ ውስጥ ጥሏት ማምለጡን ወንድሟ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል፡፡ «በሰዓቱም የጥይት ድምጽ ሰምተው የወጡ የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት የሆነውን ባለመረዳታቸው አስከሬኗም ከተጣለበት በጅብ ተበልቶ በማግስቱ የተወሰነ የሰውነት ቁርጥራጭና ልብሶቿ ተገኝተው በፖሊስ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ መላኩን» አስረድተዋል፡፡



«ቀብሯም ለይስሙላ» ተፈጸመ በማለት በተሰበረ ልብ በኀዘን አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡ የ15 ዓመት ወንድ እና የ13 ዓመት ሴት ልጅ፤ ሁለት ልጆችን በማሳደግ ላይ የነበረችን እናት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ እስካሁን በፖሊስ እየተፈለገ ነው በማለትም የሟች ወንድም አቶ ካሳሁን ለፍትህ አቤት ብለዋል፡፡





የመንግሥት አካላት የወንጀል ፈጻሚውና ወንጀሉ ክትትል

ዶይቼ ቬለ ስለዚሁ ወንጀል አፈጻጸም ከሰንዳፋ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክል ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ንጋቱ ዓለሙ ጋር በተደጋጋሚ ቢደውልም ስብሰባ ላይ ነኝ በማለታቸው አስተያየታቸውን ማግኘት አልተቻለም፡፡ ጉዳዩን እንደሚያውቁትና በቅርበትም በመከታተል ላይ መሆናቸውን የነገሩን የኦሮሚያ ክልል ሴቶችና ሕጻናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ መብራቴ ባጫ ግን የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል በሕግ የበላይነት ፍትህ እንዲያገኝ የሕግ አካላቱ በጥረት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ «በየደረጃው ያለው የኛ መዋቅርና የፍትህ አካላት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ነው» ያሉት ወ/ሮ መብራቴ ተጠርጣሪውም እንዲያዝ ጥረቶች መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡



መሰል ወንጀሎች ተገቢውን ፍርድ በማግኘት እንዲቆም እንዲደረግ የሕግ ክፍተቶችን ማሻሻል ጨምሮ ሰፊ ያሉት ሥራዎች በሚመለከተው የመንግሥት መዋቅር ጋር እየተሠራበት እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡ የግድያውን መፈጸም ተከትሎ በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተቃውሞያቸውን በማሰማት ከተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ጋር የሚመጣጠን ፍትህም እንዲሰፍን እየተጣሩ ነው፡፡





ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በሰንዳፋ በአሰቃቂ የተገደለችዉ የሁለት ታዳጊዎች እናት ጉዳይ

በሰንዳፋ በአሰቃቂ የተገደለችዉ የሁለት ታዳጊዎች እናት ጉዳይ

ሥዩም ጌቱ