ህጻናትን ጨምሮ በሕገ ወጥ መንገድ ለመኮብል የሞክሩ ከ700 በላይ ወጣቶች መያዛቸዉ
Description
በሕገ ወጥ መንገድ ለመኮብል የሞክሩ ከ700 በላይ ወጣት እና ህጻናትን መያዙን ፓሊስ አስታወቀ
በሕገ ወጥ መንገድ ከተለያዩ የኢትዮጱያ ክልሎች ተውጣጥተው በሕገ ወጥ ደላላ አማካኝነት ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመኮብለል በማሰብ በጉዞ የነበሩ ኮብላዮች በአፍር ክልል በአደኣር ፓሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል የህገዉጥ ፍልሰተኞቹ ከትግራይ አማራና ኦሮምያ ክልል የመጡ ናቸዉ። ከነዚህ ሕገ ወጥ ኮብላዮች መካከል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ እድሜያቸው ከ13 --15 አመት የሚሆናቸው ህፃናት ይገኙበታ።
ኮብላዮች ይሏቸዋል፤ በደላሎች አነሳሽነት የኢትዮጵያን እና የጂቡቲን በርሃማ አካባቢዎችን አቋርጠው በጅቡቱ በኩል ወደአረብ ሀገር አስከፊውን የባህር ላይ ጉዞ ለማድረግ ምንም የጉዞ መረጃ ሳይኖራቸው ሳውዲ አረቢያን ተስፋ አድርገው የሚጓዙህገወጥ ስደተኞች፤ የእነኝህ ሕገ ወጥ ስደተኞች መከራ ገና ከኢትዮጵያ ሳይወጡ የሚጀምር ሲሆን በደላሎች እና በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳታፊዎች ይደበደባሉ ለፆታዊ ቅጣትም ይጋለጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ሰዎች በባህር ላይ እየሞቱ እነሱይህንን ስቃይ ተቋቁመው ከሀገር መውጣትን ይመርጣሉ፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥም ከ700 በላይ ህገወጥ ተጓዦችየኢትዮጵያን ድንበር ሲያቋርጡ በአፋር ክልል ተይዘው ወደአካባቢያቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል የሚሉት የባቲ ወረዳ ፖሊስ ሃላፊ ኮማንደር አደም መሀመድ ኮብላዮቹ ለበርካታ ችግሮችም ይጋለጣሉ አሁን ላይም እድሜያቸው ከ12ዓመት ጀምሮ ያሉ ህፃናት በደላሎች እጅ እየገቡ ነው ይላሉ፡፡
‹‹የ12 ዓመት፣ የ13 ዓመት ልጅ ያገኘንበት ሁኔታ አለ፤ ስንጠይቃቸው ደላሎች ናቸው ጅቡቲ ቅርብ ነው የምትፈልጉትን ታገኛላችሁ ብለው የሚያመጡን ይላሉ፤ አፋር ክልሎች የተሻለ ነገር እየሰሩ ስለሆነ ነው እንጂ በጣም እየተደፈሩ፤ እየተንገላቱ የሚመጡ ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡›› በየእለቱ የኢትዮጵያን ድንብር አቋርጠው ለመውጣት ከተለያዩ የኢትዮጵያክፍል የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ ነውየሚሉት በአፋር ክልል የአዳአር ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዋናኢንስፔክተር አህመድ አሊ በህገወጥ መንገድ ድንበር ለማቋረጥከሚመጡ ወጣቶች ውስጥም ከአዲስ አበባ እና መቀሌ የሚነሱበርካቶች ናቸው ይላሉ፡፡ ‹‹የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር እየበዛ ነው፤ ከየአቅጣጫው ነውየሚመጡት ከመቀሌ፣ ከወልዲያ፣ በወሎ አካባቢአዲስ አበባነው የሚመጡት አብዝሃኛው ከመቀሌ እና አዲስ አበባየሚመጡ ናቸው ብዙዎቹ፡፡››
እንደ ሀገር የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰነው የሚሉት በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቁጥጥር ላይ የሚሰሩትአቶ እዩኤል ሞገስ ስርዓጥነት፣ ድህነት ፣የደላሎች ሀሰተኛ መረጃ እና በየአካባቢው ያለው ግጭት ለስደቱ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡ ‹‹ሕገ ወጥ ዝውውር በተደራጀ መልኩ ነው እየተሰራ ያለውበእኛ ሀገር እያደረሰ ያለው ጉዳት ከባድ ነው፡፡በየጊዜው ይያዛል። ምክንያቶቹ ድህነት ስራ አጥነት ሕገ ወጥ ደላሎች የሚሰጡትተስፋ በየአካባቢው ያለው የፖለቲካአለመረጋጋት ግጭቶችችግር ናቸው፡፡››
ከእለት እለት እየጨመረ የመጣው የህገወጥ የሰዎች ዝውውርመዳረሻም በአፋር ክልል ኤሊዳአር ወረዳ ውሃ ልማት የተሰኘ ቦታነው የሚሉት ዋና ኢንስፔክተር አህመድ አሊ መንግስትምየተጠናከረ ቁጥጥር እና ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው ሲሉይናገራሉ፡፡ ‹‹በመቀሌ እንደ ጎርፍ ነው የሚመጡት መዳረሻቸው ኤሊዳአርውሃ ልማት የሚባል ቦታ ነው፡፡ አሁን ራሱ 114 ሰው አለ፡፡ 25 ሴት፤ 89 ወንድ፡፡›› አሁን ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተነስተው በጅቡቲበኩል ድንበር አቋርጠው በህገወጥ መንገድ ለመጓዝ የሚመጡወጣቶች አብዝሃኛዎቹ የአርሶ አደር ልጆች እና ምንም የጉዞመረጃ የሌላቸው ናቸው፡፡
‹‹የአርሶ አደር ልጆች አንድ አይነት ቋንቋ የሚችሉ ከትግራይየመጡ አማርኛ የሚቸግራቸው ከኦሮሚያ፣ ከአሰላና አርሲ የመጡ ኦሮሞኛን እንጂ ሌላ የማይናገሩ ጭራሽ ከዚህ ከቴክኖሎጂ እና ሚዲያ ጋር ግንኙነት የሌላቸውናቸው፤ ከገጠር ከየቀበሌው ተሰብስበው የመጡ ናቸው፡፡›› እነኝህ ወጣቶች ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች አሰባስበው ወደ አረብ ሀገር የሚያሻግሩ ደላሎችን መያዝ ከባድ ነው የሚሉት ሕገ አስከባሪዎች ተጓዦች ከደላሎቹ ጋር ከስልክ ውጭ ሌላ ግንኙነትየሌላቸው ይላሉ፡፡
‹‹ደላላ የለም አይገኝም ሀይለኛ ትስስር እና ኔትወር ነው ያላቸው‹‹ከአሁን በፊት አስኮብላይ የምትለው ሰውከፊት ሆኖ ይዞ ሲሄድ ነበር የምታገኘው አሁን ላይ ግን ሰዎቹ ሚስጥር ሊጠብቁ በአካል አይገናኙም በስልክ ነው። ከደላሎች ጋር ስራ ይጠይቀናል፤ መሿለኪያ ቦታዎችን መዝጋት ፣ መንገድ ማጠናከር ያስፈልጋል ደላሎቹን እንኳን ባታገኝ ተጓዦቹን ካስቀረህ ደላላው በራሱ ጊዜ ይቋረጣል፡፡›› በየእለቱ እየጨመረ የመጣውን የወጣቶች ሕገ ወጥ ፍልሰትለመከላከል የተጠናከረ የኬላ ቁጥጥር እየተከወነም ነው ብለዋል፡፡
ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ























