DiscoverDW | Amharic - News"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜ
"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜ

"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜ

Update: 2025-12-05
Share

Description

ጅማ ከተማ ተወልዶ ያደገው አሰፋ ዳኜ የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎች መጫወት ይችላል። ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ቻይና እና ሩሲያ የተጓዘው የኪን ኢትዮጵያ የባህልና የኪነ ጥበብ ቡድን ባልደረባም ነው።



በዋናነት የስራ ድርሻው ሙዚቃ ማቀናበር እና ቤዝ ክራር መጫወት እንደነበር የገለፀልን አሰፋ በጉዞው እና ባገኘው የልምድ ልውውጥ እጅግ ደስተኛ ነው። "እነሱ የሚያውቋቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እና እኛ ጋር ያሉት በጣም ነው የሚለያዩት። የስኬል ታይባችን ትንሽ ልዩነት አለው። ግን እነሱም ይኼ ቴንታቶኒክ የሚባለውን ይጠቀሙታል። ያንን በማያቁት መሣሪያ ስንጫወት ሲያዩ እጅግ በጣም ደስተኛ ነበሩ።…አንቺ ሆዬ እና ባቲ የሚባሉ ቅኝቶች አያውቋቸውም እና እነዚያን ቅኝቶች ሲሰሙ ይደነቁ ነበር። " ይላል።



የባህልና የኪነ ጥበብ ቡድኑ ከቤጂንግ ቻይና ወደ ሳንት ፔተስበርግ ሩሲያ ቀጥሎ እንደተጓዘ የነገረን አሰፋ በሩስያ የነበረውን ቆይታም ያወድሳል። "በእኛ መስከረም አንድ አዲስ ዓመት ላይ ነበር። አበባ አየሽ ወይ ሁላ ተጫውተናል። እሱ በጣም አስገራሚ ነበር። ሆያ ሆዬ፤ አበባ አየሽ ወይ በድምጽ ብቻ የሚሰሩ ሙዚቃዎች ናቸው። ሁላችንም ያደግንበት ማለት ነው። በእንጨት ላይ ተደርጎ ቆርኪ የምንጫወትበትን ራሱን ነው እዛ የተጫወትነው እና እጅግ ደስተኛ ነበሩ "



"ሰርቶ ማሳየት ነው መፍትሔው "



አሰፋ ውጭ ሀገር ድረስ የኢትዮጵያን ባህል እና ኪነ ጥበብ ማስተዋወቅ እስኪችል ድረስ የነበረው ጉዞ ደግሞ ይህን ይመስላል። "ገና በ11 ዓመቴ ፤ ክራር ፤ ዋሽንት እና ማሲንቆ መጫወት የሚችል ጎበዝ ሙዚቀኛ ነበርኩ" የሚለው አሰፋ ልጅ እያለ ታላቅ ወንድሙ እቤት ውስጥ የሙዚቃ መሣሪያ ሲለማመድ ማየቱ ጠቅሞታል። ሲቀጥል ደግሞ ገና ህፃን ሳለ አባቱ ስፖርት ስታዲየም ይዘውት መሄዳቸው ለሙዚቃ መሣሪያ ፍቅሩ እንዲያድርበት ረድቶታል። "ህፃን ሆኜ በእጁ በሚጎትተኝ ሰዓት ያኔ ሙዚቃ ሲጫወቱ አይ ነበር። ግን አስታውሳለሁ በ 11 ዓመቴ የሙዚቃ መሣሪያ በደንብ እጫወት ነበር"



ልጆች ያላቸውን የሙዚቃ ተሰጥዎ እንዲያጎለብቱ በወቅቱ የሚያበረታታ ማህበረሰብ አልነበረም ይላል አሰፋ። የእሱም ወላጆች በብቃቱ አምነው እስኪያበረታቱት ድረስ ጊዜ ወስዶባቸዋል። ይሁንና አሰፋ ተስፋ አልቆረጠም። ስለሆነም ተሰጥቆ ላላቸው ልጆች እና ወጣቶች "ሰርቶ ማሳየት ነው መፍትሔው ይላል"



"እኔ ለምሳሌ በጣም ለፍቼ ፤ ብዙ ዓመት ሰርቼ ከዛም ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስሰራ የሚያዩ የእኔ ተናናሾች እንደእኔ ለመሆን ጥረት ይጀምራሉ። እኔም በግሌ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የመክፈት ሂደት ላይ ነኝ ያለሁት። እና ያኔ እኔን እያዩ ስለሆነ የሚሰሩት ይበረታታሉ ብዬ አስባለሁ"



ከባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ባሻገር አሰፋ እንደ ድራም ፣ ጊታር፣ ኪቦርድ የመሳሰሉ የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎችም መጫወት ይችላል። ይህም ችሎታው ከበርካታ የኢትዮጵያ አርቲስቶ ጋር መስራት እንዲችል አጋጣሚዎችን ፈጥሮለታል። "በጣም ከትላልቆቹ ካልሆነ በስተቀር ከአብዛኻናቸው ጋር ሰርቻለሁ"



አሰፋ ኢትዮጵያ ውስጥም የተለያዩ አካባቢዎች የመስራት እድል ነበረው። "አፋር ብቻ ነው ያልሄድኩት እንጂ ሁሉም አካባቢዎች ላይ ተንቀሳቅሼ ሰርቻለሁ"



ለሙዚቃ አቀናባሪዎች AI ስጋት ወይስ እድል?



"AI ን በሁለቱም መንገድ ብናየው ጥሩ ነው። አንድ አቅም ያላቸው እነሱ የሚፈልጉትን አቀናባሪ ወይም ሶስተኛ ወገን ማግኘት ካልቻሉ ቀጥታ ከ AI ጋር መስራት ይችላሉ። ይኼን ከጥሩ ጎኑ እንየው። ከስጋት ጎኑ ብናየው ደግሞ ሁሉም ሰው ሙዚቀኛ ሆነ ፣ ከመሬት ተነስቶ ማቀናበር ሊጀምር ነው። ያ ደግሞ ብዙ ዓመት ለፍተው ፤ አውቀው የሆነ ቦታ የደረሱ ሰዎችን ያኮላሻል። "



አሰፋ ወደፊት ተወልዶ ያደገባት ጅማ ከተማ እና አዲስ አበባ እየተመላለሰ የሙዚቃ ስራውን ማከናውን ይሻል።



ልደት አበበ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜ

"በ11 ዓመቴ ሙዚቃ በደንብ እጫወት ነበር" የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችና አቀናባሪ አሰፋ ዳኜ

ልደት አበበ/ Lidet Abebe