DiscoverDW | Amharic - Newsየበረታው የኮሬ ዞን አርሶ አደሮች ጥቃት
የበረታው የኮሬ ዞን አርሶ አደሮች ጥቃት

የበረታው የኮሬ ዞን አርሶ አደሮች ጥቃት

Update: 2025-03-13
Share

Description



የበረታው የኮሬ ዞን አርሶ አደሮች ጥቃት



በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የሚገኘው ዳኖ ቀበሌ በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት ከሚፈጸሙባቸው መንደሮች አንዱ ነው ፡፡ “ ትናንት ረፋድ ላይ የሆነውም ይኼው ነው “ የሚሉት አንድ የዳኖ ቀበሌ ነዋሪ በእርሻ ሥራ ላይ ከነበሩት የቤተሰብ አባላት መካከል አንድ ወጣት በጥይት ተመትቶ መገደሉን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡

ታጣቂዎቹ ትናንት ረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ ከታችኛው የጉጂ ዞን ተሻግረው የመጡ መሆናቸውን የጠቀሱት አስተያየት ሠጪዎች “ ታጣቂዎቹ በእርሻ ሥራ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ መተኮስ ሲጀመሩ ሁሉም አግር አውጭኝ አለ ፡፡ በዚህ መኻል በላይ ጠቅል የተባለ የቤተሰቡ አባል የሆነ ወጣት በተተኮሰበት ጥይት ተመጥቶ ህይወቱ አልፏል ፡፡ ዛሬ ሐሙስ ቀብሩን ፈጽመናል “ ብለዋል ፡፡



የሥጋት ኑሮ



መነሻቸውን ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አድርገዋል የተባሉት ታጣቂዎች ከዳኖ በተጨማሪ የጄሎ ቀበሌ ላይም ተመሳሳይ ግድያ መፈጸማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡ በቀበሌው በከብት ጥበቃ ላይ የነበረ ነዋሪ ከትናንት በስቲያ በጥይት ተገድሎ መቅበራቸውን የጠቀሱት አንድ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ “ ነገን ለመኖር ምን ዋስትና አለን ? “ ሲሉ ይጠይቃሉ ፡፡ ታጣቂዎች ወደ መንደሩ የሚመጡበት ሠዓት አይታወቅም የሚሉት አስተያየት ሰጪው “ ጥቃቱን የሚያደርሱት ቀን ወይም ሌሊት ሊሆን ይችላል ፡፡ ዛሬን ኖረን ወደ ነገ ሥለመሻገራችን እርግጠኛ አይደለንም ፡፡ ኑሯችን በሙሉ የሥጋት ነው ፡፡ በርካቶች ሞተዋል ፡፡ እኛም ሞትን እየጠበቅን እንገኛለን “ ብለዋል ፡፡



ሃላፊነቱን ማን ይውሰድ ?



ዶቼ ቬሌ በኮሬ ዞን የፀጥታ ሥጋት ዙሪያ የኮሬ ዞን ባለስልጣናትንም ሆነ ታጣቂዎቹ መሽገውበታል የተባለውን የኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን አመራሮችን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት አድርጓል ፡፡ ያም ሆኖ አንዳንዶቹ ስብሰባ ላይ ሌሎቹ ደግሞ ጉዞ ላይ መሆናቸውን በመግለጻቸው ምላሻቸው ማካተት አልተቻለም ፡፡

የፌዴራሉ መንግሥት በኮሬ ዞን ለሚፈጸመው ጥቃት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያለውንና “ ሸኔ “ ብሎ የሚጠራውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተጠያቂ ያደርጋል ፡፡ ሠራዊቱ በበኩሉ ለግድያው የኦሮሚያ ሚሊሺያዎች ተጠያቂ ናቸው ሲል በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቸው መግለጫዎች አስታውቋል ፡፡ በዚህ መኻል ግን በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች አሁንም አላቆሙም ፡፡ ዞኑ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከሚዋሰኑ ቀበሌያት ከ2009 ዓም ጀምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሲገደሉ ከ30ሺ በላይ የሚሆኑ መፈናቀላቸውን ዞኑ በተለያዩ ጊዚያት ባወጣቸው ሪፖርቶች ተመልክቷል ፡፡





የእንደራሴዎቹ ውትወታ



ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈጸመበት የሚገኘውን የኮሬ ዞንን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወክሉ እንደራሴዎች የነዋሪዎቹን ሥጋት ሳይገልጹ ያለፉበት ጊዜ እንደሌለ ይናገራሉ ፡፡ በተደጋጋሚ ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር በመወያየት የችግሩን መንስዔ እና መፍትሄ ለፌደራሉ መንግሥት ማቅረባቸውን የጠቀሱት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴ ዶክተር አወቀ ሀምዛዬ “ ጥቃቶቹ እየተፈጸሙ የሚገኙት አርሶአደሩ የእርሻውን እና አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ለማድረግ ነው ፡፡ በአካባቢው ቋሚ የፀጥታ ካምፕ እንዲኖር ምክረ ሀሳብ አቅርበናል ፡፡ ነገር ግን መንግሥት እስከአሁን ከጊዜያዊና ከተንቀሳቃሽ የፓትሮል ጥበቃ በስተቀር ለጉዳዩ በቂ ትኩረት የሠጠው አይመስለኝም ፡፡ በእኛ በኩል ግን አሁንም መፍትሄው በመንግሥት እጅ ነው ብለን እናምናለን ፡፡ መንግሥት አርሶአደሮቹን ከጥቃት እንዲታደግ ለማድረግ ጥረታችንን እንቀጥላለን “ ብለዋል፡፡





ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

እሸቴ በቀለ





Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የበረታው የኮሬ ዞን አርሶ አደሮች ጥቃት

የበረታው የኮሬ ዞን አርሶ አደሮች ጥቃት