DiscoverDW | Amharic - Newsየአሜሪካ ህግ አውጭዎች የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ዉሳኔ አሳለፉ
የአሜሪካ ህግ አውጭዎች የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ዉሳኔ አሳለፉ

የአሜሪካ ህግ አውጭዎች የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ዉሳኔ አሳለፉ

Update: 2025-11-19
Share

Description

የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ተወሰነ

አነጋጋሪው የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲደረግ የአሜሪካየሕዝብ ተወካዮች እና ሴኔት በአብላጫ ድምፅ ወሰኑ ። የሕግ አውጭዎቹ ባለሥልጣናትን ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችን የወሲብ ቅሌት ይዟል የተባለው ሰነድ ይፋ እንዲሆን ድጋፍ ከማግኘቱ በፊት ለዓመታት የዘለቀ ተቋማዊ ክህደት ተፈጽሞበት እንደነበር የጥቃቱ ሰላባዎች ተናግረዋል።





ከቅሌቱ ጋር ስማቸው ተያይዞ የተነሳው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰነዱ ይፋ እንዲሆን የተቀናቃኙ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ጫና ፈጥሯል ብለው መክሰሳቸው ይታወሳል። ነገር ግን ሰነዱ ይፋ እንዲሆን ግፊቱ እያየለ መምጣቱን ተከትሎ የፓርቲያቸው ሪፐብሊካን የሰነዱን ይፋ እንዲሆን ድጋፉን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።





20 ሺ ያህል ገጾች ያሉት የቅሌት ሰነዱ ወሲባዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ፖለቲከኞች ፤ ታዋቂ ሰዎችና እና ሌሎችም የፋይናንስ ተቋማትን ጭምር ያካተተ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።

ከሰነዱ ጋር ስሙ አብሮ የተያያዘው ጄፈሪ ኤፕስታይን ከዚሁ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ እስር ቤት ውስጥ ሞቶ መገኘቱ ይታወሳል። ፖሊስ ተጠርጣሪው ራሱን አጠፋ ከማለት ውጭ ስለትክክለኛ አሟሟቱ አሁንም ድረስ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።





ከአንድ ወር በላይ በክርክር ሂደታ ላይ የቆየው ሰነዱ ይፋ የመሆኑ ነገር ሲሰማ በቅሌቱ ተጎጂ ለነበሩት እና ለዓመታት ፍትህ ሲፈልጉ ለነበሩ ሰዎች እፎይታ ይዞላቸው እንደሚመጣ ነው የሚጠበቀው ። በአንጻሩ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ዝግ ሆኖ ለሰነበተባቸው እና የዋጋ ግሽበት የራስ ምታት ለሆነባቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሕዝብ እምነት ሊሸረሽርባቸው ይችላል በሚል አስግቷል።

ታሪኩ ኃይሉ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአሜሪካ ህግ አውጭዎች የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ዉሳኔ አሳለፉ

የአሜሪካ ህግ አውጭዎች የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲሆን ዉሳኔ አሳለፉ

ታሪኩ ኃይሉ, Tamirat Dinssa Geleta ታምራት ዲንሳ ገለታ