DiscoverDW | Amharic - Newsያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት
ያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት

ያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት

Update: 2025-11-08
Share

Description

ያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት

በውዝግብ እና ዓመፅ ያታጀበው የታንዛንያ ምርጫ ማሸነፋቸውን ያወጁት ሳምያ ሱሉሑ ሐሰን በአለፈው ሰኞ ቃለ መሐላ ፈፅመዋል። በታንዛንያ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በሰበብ አስባቡ ዘብጥያ በወረዱበት ሁኔታ ምርጫ መካሄድ የለበትም ያሉ ወጣቶች በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠራርተው ዋና ከተማዋ ዳሬሰላምን ጨምሮ በዋና ዋና የሐገሪቱ ከተሞች ሐይልን የቀላቀለ የተቃዎሞ ሰልፎች አካሂደዋል። የሐገሪቱ የጸጥታ ሐይሎች ተቃዋሚዎችን ለመበተን በወሰዱት የሐይል እርምጃ 800 ሰዎች መገደላቸውን የሐገሪቱ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ የሆነውን ቻዴማ ቃል አቀባይ ገልጸዋል። መንግስት ዓመጸኞችን የሚቆጣጠሩ ፖሊሶችን ለማጠናከት የሐገሪቱ የጦር ሐይልም አሰማርቷል።

በሐገሪቱ እየታየ ያለው አለመረጋጋት ቀጣናውን እንዳያተራምስ ተሰግቷል። ተቃዋሚ ሰልፈኞች ባካሄዱት መጽ ጉምሩክን ጨምሮ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የመንገድና የመገናኛ አውታሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። መንግስት አመጹን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርጓል። በመሰረተ ልማቶች ላይ የደረሱ ውድመቶችና ፋም ጋም እያለ ያለው የሕዝብ ተቃዎሞቀጣናውን እንዳያተራምስ አስግቷል።

የባሕር በር የሌላቸው እንደ ማላዊ፣ ዛምቢያና ዙምባብዌ በታንዛንያ ወደቦች ጥገኛ ናቸው። በታንዛንያ የቀጠለው አለመረጋጋት በማላዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን የምጣኔ ሐብት ባለሙያ የሆኑት ክርስቶፈር ሙባክዋ ለዶይቸቨለ ተናግረዋል።





ምጣኔ ሐብታዊ ችግሮች





«በማላዊ የሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ ነው። በታንዛንያ ወደቦች ከሚገቡ አንዱ የአፈር ማዳበሪያ ነው። አሁን በታንዛንያ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል። ገበሬዎች ማዳበሪያ ማግኘት ያለባቸው አሁን ባለንበት በዚህ ቁልፍ ወቅት ነው። ይህ በሚቀጥለው ዓመት የምርት ወቅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ስለኢኮኖሚ ካነሳን የዋጋ ግሽበት ማንሳታችን አይቀርም፤ አለመረጋጋቱ በማላዊ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል።»

ታንዛንያ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ SADC እየተባለ የሚጠራውና 16 ሐገራትን ያቀፈው የደቡብ አፍሪካ ሃገራት የልማት ማሕበረሰብ አባል ነች።



የመኪኖቻችን ሁኔታ ማወቅ አልቻልንም





የታንዛንያ ወደቦች ዙምባብዌ ወደ ሃገሯ በምታስገባቸው ተሽከርካሪዎች ዋነኛ የመግቢያ በር ናቸው። በአመጹ ምክንያት ግን የመኪናዎች ከውጭ የማስመጣት ሥራዎች ክፉኛ መጎዳቱን የዙምባብዊ የመኪና አስመጪ ኩባንያዎች ይናገራሉ። ትሪስ ቺያምባ ከነዚህ ኩባንያዎ ባለቤቶች አንዱ ናቸው።

« ከጉምሩክ አስተላላፊዎቻችን መገናኘት አልቻልንም። ከመርከቦች የተራገፉ መኪኖቻችን ወደ ዙምባቤዌ ለማጓጓዝ በሚያስችል የወደቡ አካባቢ በሚገኝ ማቆያ ስፍራ ቆመው ነበር።በአመጹ ምክንያትተቃጥለው ይሆናሉ የሚል ስጋት አድሮብናል።»

የደቡብ አፍሪካ ሃገራት የልማት ማሕበረሰብ አባል ሐገራት 60 በመቶ የሚሆነው የሐገራቱ አመታዊ አጠቃላይ ምርት በዚህ ኮሪደር እንደሚንቀሳቀስ መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህም ለ 1. 6 ሚልዮን ወገኖች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ይታወቃል። በታንዛንያ የተፈጠረው ቀውስ የነዚህ አባል ሐገራት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በማወኩ ሐገራቱ አማራጭ ወደቦችን በማማተር ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ በራሱ በታንዛንያ ኤኮኖሚና በቀጠናው መረጋጋት ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድር የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

እሸቴ በቀለ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት

ያልተረጋጋችው ታንዛንያ አካባቢውን የማተራመስ አቅም አላት

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር Yohannes G/Egziabher