DiscoverDW | Amharic - Newsበአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተባባሰው የትራፊክ አደጋ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተባባሰው የትራፊክ አደጋ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተባባሰው የትራፊክ አደጋ

Update: 2025-10-20
Share

Description

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የትራፊክ አደጋ የሠዎችን ህይዎት እየቀጠፈ እንደሆነ ነዋሪዎችና የትራፊክ ባለሙያዎች ገልፀዋል፣ ለአደጋዎቹ ምክንያቶች የተለያዩ እንደሆኑ ፖሊስ አመልክቷል፡፡ የትራፊክ አደጋ አሁን አሁን ብዙዎችን ያለቤተሰብ እያስቀረ ያለ ክስተት እየሆነ መጥቷል፣ ብዙዎች በትራፊክ አደጋ እንደወጡ እየቀሩ ነው ሌሎች ደግሞ ለዘላቂ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡



በተለያዩ ጊዜዎች የደረሱ የትራፊክ አደጋዎች



በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ከተማ አቅራቢያ ባለፈው መስከረም 11/2018 ዓ ም በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ እስከ 11 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ ከ10 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን የዞኑ ፖሊስ በወቅቱ ገልጿል፡፡



መስከረም 13/2018 ዓም በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ “ዳባ መግቢያ” በተባለ ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ12 ሠዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 49ኙ ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል፡፡



በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ጥቅምት 2/2018 ዓ ም ለዶይቼ ቬሌ እንደገለፀው ደግሞ በዕለቱ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ጨፋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሠዎች ሕይወት አልፏል 26 ሠዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡



ስለትራፊክ አደጋ የተሰጡ አስተያየቶች



በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ላሎ ወረዳ ነዋሪ በትራፊክ አደጋምክንያት ያሉትንና እየደረሰ ያለውን ጉዳት በተመለከተ ጠይቀናቸው ነበር፡፡

“.እዚህ ሰሜን ሸዋ አካባቢ በሬሳ አካባቢ የገባ (የተገለበጠ) መኪና አለ፣ ህፃናትን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች እንዲሁ የተጋጩ አሉ” ብለዋል፡፡ እንደ አስተያየት ስጪው፣ ያላግባብ መጫን የመንግዶች ምቹ አለመሆን አሮጌ መኪናዎችና ሌሎችም ለትራፊክ አደጋ መነሻ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው ያብራሩት፡፡



ሌላ አስተያየት ሰጪ እንደገለፁት ደግሞ፣ የትራፊክ አደጋ ለቤተሰብ መበተንና ለተጎሳቆለ ህይወት የሚዳርግ ክስተት እየሆነ መምጣቱን ነው ያስረዱት፡፡ ለችግሮቹ መፈጠር የጥንቃቄ ጉድለት እንደሆነ የሚናገሩ አንድ አስተያየት ሰጪ አለአግባብ ጭነትም አንዱ ለትራፊክ አደጋ መፈጠር ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል፡፡



አሽከርካሪዎች በአስፈላጊ ቦታ ላይ ጥሩምባ እንደማያሰሙ አመልክተው፣ ይህም ለግጭት መነሻ እንደሆን ገልጠዋል፡፡ አሁን አሁን ፎርቶ መጋላ ( ከመኪናው ጣራ ላይ) ተሳፋሪ መጫን እየታየ እንደሆነ የተናገሩት እኚህ አስተያየት ሰጪ ይህ በአስችኳይ ሊታረም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ከአቅም በላይ ተሳፋሪን መጫን ሌላው ለአደጋ የሚጋብዝ አሰራር እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎች ገልጠዋል፡፡



የትራፊክ አደጋ እየጨመረ ነው” በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ፖሊስ



በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ንጉሴ ሞግስ በዞኑ በተለያዩ ምክንያቶች የትራፊክ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡



ባለፉት 3 ወራት 33 አድጋዎች መድረሳቸውን የየገለፁት አዛዡ፣ በ82 ሠዎች ላይ ጉዳት ደርሶ 24ቱ ህይወታቸው ሲያልፍ በ34ቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት 9 የትራፊክ አድጋዎች ደርሰው 9 ሰዎች መምታቸውን ያመለከቱት ኮማንደር ንጉሴ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 15 እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

ችግሩን ለመቀነስ በየምናኸሪያዎችና በሌሎችም አካባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆንም አዛዡ አመልክተዋል፡፡



ባለፉት 3 ወራት በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ከሰብአዊ ጉዳቱ በተጨማሪ ከ14 ሚሊዮን 300ሺህ በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙም ተመልክቷል፡፡

የአማራ ክልል የትራፊክ አደጋ ምን እንደሚመስል ለማወቅ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን የተለያዩ ኃላፊዎች በአካልና በስልክ ለማናገር ሞክረን ነበር፣ ሆኖም የሥራ ፈቃድ መታወቂያ ብናሳይም ጀርመን ቦን ከተማ ከሚገኘው የዶይቼ ቬሌ ዋናው መስሪያ ቤት “ደብዳቤ ካላመጣችሁ መረጃ አይሰጥም” በመባሉ መረጃውን ማግኘት አልቻልንም፡፡



ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተባባሰው የትራፊክ አደጋ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተባባሰው የትራፊክ አደጋ

ዓለምነው መኮንን