DiscoverDW | Amharic - Newsየአሜሪካ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ዘገባ
የአሜሪካ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ዘገባ

የአሜሪካ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ዘገባ

Update: 2025-08-15
Share

Description

በኢትዮጵያ የዘፈቀደ ግድያዎችና ሌሎች ኢሰብአዊ እርምጃዎች ይፈጸማሉ ሲል የአሜሪካ መንግስት ሪፖርት በቅርቡ ባወጣው አመለከተ። እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር 2024 በኢትዮጵያ የነበረውን የሰብአዊ መብት አያያዝ የዳሰሰው የሪፖርቱ ክፍል፣ሕገ ወጥ ያላቸው ግድያዎችን፣ አካላዊ ጥቃቶችን፣የፕሬስ ነፃነትን፣ የሠራተኛ መብቶችንና በኃይማኖት ነጻነት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ሁሉ የተመለከተ ነው።



የዘፈቀደ ግድያዎች መቀጠላቸው



በሪፖርቱ ላይ እንደተጠቀሰው፣በዜጎች ላይ የዘፈቀደ ወይም ሕገወጥ ግድያዎች የሚፈጽሙት፣ በኢትዮጵያ መንግስት ኀይሎችና የተለያዩ ታጣቂዎች ነው። ማጥፋት፣ማሰቃየት፣ኢሰብአዊ አያያዝና ቅጣት፣የዘፈቀደ እስራት መፈፀም መቀጠላቸውንም አብራርቷል። የዘፈቀደ ግድያዎች እና ኢሰብአዊ የሆኑ አያያዞች የሚፈጸሙት፣ በዐማራ ኦሮሚያና ትግራይን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እንደሆነ ሪፖርቱ ጨምሮ አስረድቷል።

በዐማራና ኦሮሚያ ክልሎች በተለይ፣ ከግጭት ጋር ተያይዞ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች መኖራቸውን ያሳያል ሪፖርቱ።በእነዚሁ ክልሎች የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊነት ቢያበቃም፣ የሚፈጸሙት በደሎች ግን መቀጠላቸውን ጭምር። በዐማራና ኦሮሚያ ክልሎችና በሌሎችም አካባቢዎች በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትና በዐማራ ፋኖ ታጣቂዎች ጭምር፣ በሰላማዊ ሰዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ላይ ሕገ ወጥ ግድያዎች መፈጸማቸውንም መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ሪፖርቱ ገልጿል።

በትግራይ ክልልም፣የንጹሃን ግድያ፣ጅምላ የግዳጅ መፈናቀልና የመደፈር ወንጀሎች መፈፀማቸውን አትቷል። በዓፋር፣በጋምቤላና በሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የአካባቢ ሚሊሻዎች፣በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውንም እንደዚሁ።



በመንግሥት የተወሰዱ እርምጃዎች



መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ባለስልጣናትን በመለየት የተወሰነ የቅጣት እርምጃ መውሰዱን ያመለከተው ሪፖርቱ፣ ዝርዝር መረጃው ግን ጥቂት እንደሆነ አመልክቷል።

በመላ አገሪቱ በመሠረታዊ የመናገር፣የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ላይም የክልከላ እርምጃ እንደተወሰደም ሪፖርቱ አሳይቷል።

እንደ ሪፖርቱ፣ በጋዜጠኞች፣የሲቪል ማኀበረሰብ አባላት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ተቃዋሚዎች ላይም ማስፈራራትና እገዳዎች ተፈጽሟል።



የሪፖርቱ አንድምታ



የዚህን ሪፖርት አንደምታ አስመልክቶ ያነጋገርናቸውና የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ የሚከተሉት ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ፣ የአሜሪካ መንግስት ሪፖርቱን ጫና ለማድረግና የፖሊሲ አቅጣጫውን ለማስተካከል ሊጠቀምበት እንደሚችል ይናገራሉ። "አንዳንድ ጊዜ የአሜሪካ መንግስት፣ ሪፖርት ያወጣና እነዚህን ሪፖርቶች ሃገራት ካነበቧቸው በኋላ፣ንግግር ለመጀመሪያ ወይም ሃሳብ ለመለዋወጥ ይጠቀምባቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለጫና ይጠቀምባቸዋል ግን ፖሊሲዎችን ሊቀየሩ ይችላሉ። የፖሊሲያቸውን አያያዝ አተረጓጎም ሊቀይሩ ይችላሉ።"



የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በየዓመቱ ከሚያወጣቸው ሪፖርቶች በተለየ፣የዘንድሮው ፀረ ሴማዊነትን አካቶ የቀረበበት መሆኑንም ፕሮፌሰር ተሾመ አስረድተዋል።

"ፀረ ሴማዊነትን የሚያበረታቱ ድርጊቶች አዲስ አበባ እየተፈጸመ ነው፣መንግሥት ይጠብቀናል ነገር ግን መድልዎ አለብን በዚህ የተነሳ የሚለውን አስቀምጠውታል፣ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀመጠ ነው።" በቀረበው ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስትን አስተያየት ለማካተት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ጋር ብንደውልም ምላሽ ባለማግኘታችን ለጊዜው አልተሳካም።





ታሪኩ ኃይሉ

ኂሩት መለሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአሜሪካ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ዘገባ

የአሜሪካ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ዘገባ