DiscoverDW | Amharic - Newsወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ?
ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ?

ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ?

Update: 2025-11-21
Share

Description

እንደ የተባበሩት መንግስታት የስነ-ሕዝብ ፈንድ (UNFPA) መረጃ ከሆነ ከሁለት ዓመታት በፊትኢትዮጵያ ውስጥ ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነው ወጣት ሥራ አጥ ነበር። ጤና ይስጥልኝ ውድ የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ተከታታዮች! የተባበሩት መንግስታት የስነ-ሕዝብ ፈንድ በኢትዮጵያ ያለውን ሥራ አጥነት በተመለከተ በጎርጎሮሲያኑ 2023 ዓም ይፋ ባደረገው መረጃ በተለይ በኢትዮጵያ ከተሜ አካባቢዎች የወጣቶች ሥራአጥነት 26.8 በመቶ ያህል እንደነበረ ይጠቁማል። ወጣት ሲል የገለጻቸውም እድሜያቸው ከ15-29 ያሉትን ነው። በኢትዮጵያ ወጣቶች ተነሳሽነት ባለፈው ዓመት ሥራ የጀመረው የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ ወጣቱን በማብቃት ሥራአጥነትን መታገል ይፈልጋል። ሶፎኒያስ ግርማ የሙያ ወግ ዋና ስራ አስኪያጅ ነው።

«የሙያ ወግ የሚል የአማርኛ ስያሜ ነው የሰጠነው።» ሲል የጀመረው ሶፎኒያስ የሙያ ወግ ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ? እንዴት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ብቁ መሆን ይችላሉ? የሚሉ መርኃ ግብሮች የሚዘጋጅበት የ10 ዓመት ኢኒሺየቲቭ ነው» ይላል።



ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ማድረግ



መስራቾቹ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ናቸው። በምስራቅ አፍሪቃ የሚገኙ ዘጠኝ ሀገራት ላይ ትኩረት አድርገን ለመሥራት እንፈልጋለን የሚለው የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጁ ሶፎኒያስ የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ የ 10 ዓመት ግብ ምን እንደሆነ ገልፆልናል። « በ 10 ዓመታት ውስጥ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እና ምስራቅ አፍሪቃውያን ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ማድረግ ነው።» ይላል። ኢትዮጵያም ይሁን ሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት የተመራቂዎች ቁጥር ችግር የለም ዋናው ችግር «ብቃት» የሚለው ነውም ይላል። «ወጣቱ ሥራ አጣሁ ሲል ወይም ሥራ አጥነት ጨመረ ሲባል ይስተዋላል። በዛው ልክ ደግሞ ተቋማቶች የሰው ኃይል ፍላጎት እያላቸው ብቁ የሆነ ሰው ሲያጡ ተመልክተናል። ስለሆነም ያንን ችግር ለመቅረፍ ዘጠኝ ሀገራት ለሚገኙ ወጣቶች ብቁ እንዲሆኑ፤ በተለያዩ መርኃ ግብሮች በመታቀፍ ከታላላቆቻቸው ጋር ሆነው ሙያዊ ብቃታቸውን የሚገነቡበት መድረክ ይዘንላቸው መጥተናል።»



ይህንንም ለማሳካት የሙያ ወግ በአራት ቋንቋዎች ማለትም በእንግሊዘኛ፣ አማርኛ፣ አረብኛ እና ፈረንሳይኛ ፕሮጀክቱን ለመስጠት ቀርጿል። የሙያ ወግ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት የ1500 ወጣቶችን ፍላጎት በማሰባሰብ የዳሰሳ ጥናት አድርጓል። በዚህም ጥናት የከፍተኛ ተቋም ፣ የኮሌጅ እንዲሁም የቴክኒክ እና ሙያ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በጥናቱ አማካኝነት «ወጣቱ ከፍተኛ የመረጃ ክፍተት እንዳለው ለማወቅ ችለናል» የሚለው ሶፎኒያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች ለሥራብቁ እንዳይሆኑ ሌላው ፈተና የሆነባቸው «በትምህርት እና በስራው ዓለም መካከል ያለው የመረጃ ክፍተት ነው» ይላል። «ስለዚህ የሙያ ወግ ይህንን የመረጃ ክፍተት ለመሸፈን እየሞከረ ነው። ለምሳሌ ማክሰኞ ዕለት ያስጀመርነው የዲጂታል ፕላትፎርም የተለያዩ መረጃዎች ስለሚያቀርብላቸው መረጃ ተኮር የሆነ ውሳኔ መወሰን ይችላሉ። ሌላው የሙያ ወግ ሀብ የሚባል የቴሌግራም ፕላትፎርም አዘጋጅተናል።»



አንዳንድ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ይኖራቸዋል ። ነገር ግን ይህን ዕውን የሚያደርጉበት ገንዘብ ስለሌላቸው እቅዳቸው ሳይሳካ ይቀራል። የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ ከተለያዩ እንደ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅቶች (UNICEF) ካሉ ዓለም አቀፍ እና በርካታ ሀገር አቀፍ ተቋማት ጋር የሚሰራ ፕሮጀክት እንደመሆኑ ወጣቶች በፋይናንስ የሚታገዙበት አጋጣሚስ ይኖር ይሆን?«የገንዘብ ድጋፍ እስካሁን ድረስ ውሳኔዎች የሉም። የምናቀርብላቸው ሁለት ነገር ነው። በተለይ የስራ ፈጠራ ላይ መግባት የሚፈልጉ ወጣቶች ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር አቀፍ የሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት አለ። ከእነሱ ጋር እየሰራን እንገኛለን። ከዛ ቀጥሎ የገብያ ድጋፍ እናደርግላቸዋል። የተለያዩ ገበያዎች ላይ ወጣቶች ስራቸውን ማስተዋወቅ እንዲችሉ ወይም ደግሞ ከገበያው ጋር መተዋቀቅ የሚችሉበትን ነገር እናግዛቸዋለን። »

ፕሮጀክቱ በኦንላይን እና በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች እና የማማከር ሥራ የሚሠራ ሲሆን እንደ ሥራ ፈጣራ፤ ሴቶችን ማብቃት ፤ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ወጣቶች ከሙያ ወግ መጠበቅ ይችላሉ።



ወጣቶች የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን ቢፈልጉ እንዴት ማመልከት ይችላሉ? ክፍያውስ?



ሶፎኒያስ የተለያዩ አማራጮችን ይዘረዝራል።«ምንም አይነት ክፍያ የለውም። ቴሌግራም እና ኢኒስታግራም ላይ የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ ብለው ቢፈልጉን ያገኙናል። ሊንክድ ኢን ላይ ቢፈልጉን ዝርዝር ነገሮችን ያገኛሉ። ድረ ገፃችን ላይ ቢፈልጉን ያገኙናል።»

መስፈቶቹ ደግሞ እንደየዘርፉ የተለያዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሶፎኒያስ ገልፆልናል። እድሜ አንዱ መስፈርት ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመልካቾች ስልጠናውን ለመውሰድ በቂ ጊዜ ሊኖራቸው እንደሚገባ ስራ አስኪያጁ ሶፎኒያስ ይናገራል። ሌላው ቁርጠኝነት ነው። ይህም የሚረጋገጠው አመልካቾቹ በያሉበት ሆነው በኦንላይ በሚወስዱት ፈተና አማካኝነት ይሆናል።«ሁሉም ወጣት ሊፈልገው ይችላል። ግን በተለይ ይህንን ስልጠና ወስደው ማኅበረሰቡ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ መሆን አለባቸው። ሁለተኛ ነገር ደግሞ 9 ወር የሚሰጥ ፕሮግራም ነው። በየሳምንቱ የተወሰነ ቁርጠኝነት ይጠይቃል እና ያንን ቁርጠኝነት ሊወጡ ይችሉ እንደሆነ በፈተናው አማካኝነት መለየት ይቻላል።»



ብዙ መስፈርት የሌለው እና ማንኛውም ለሥራ ማመልከት የሚፈልግ ወጣት ሊያደርግ የሚችለው ነገር ግን አለ። «CV የምንለውን ማዘጋጀት የሚችሉበት ፕላትፎርም አለ። ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው ወጣቶች በ AI ወይም የሌሎችን የማመልከቻ ፎርም ወደ ራሳችን ለማምጣት ሲሞከር ነው የሚስተዋለው። ይህንን ፕላትፎርም ለየት የሚያደርገው በአብዛኛው ቀጣሪዎች ዘንድ ተመራጭነት ያላቸው ሶስት ዲዛይኖችን ይዞ ነው የቀረበው። ስለሆነም ወጣቶች ወደ ድረ ገፃችን በመግባት ያለ ምንም ክፍያ ዳውን ሎድ በማድረግ የራሳቸውን የስራ ማመልከቻ ማዘጋጀት ይችላሉ። »

የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ የወጣቶች የዲጂታል ግንዛቤን ማዳበር ላይ እየሠራም ይገኛል። ስልጠናዎች ከዚህ በፊት የተሰጡ እና ወደፊትም የሚቀጥል እንደሆነ የሚናገረው ሶፎኒያስ ቀጣይ መርኃ ግብሮች እንደሚኖሩ እና ወጣቶች አተኩረውበት ሊሠሩበት የሚገባ ነገር እንደሆነ ይመክራል። «ዲጂታል ሊትረሲ ቀላል ነገር ይመስላል ነገር ግን ብዙ ጊዜ ወጣቶች ሲቸገሩ የምናስተውለው እንዴት ዲጂታል መሣሪያዎችን ማግኘት እና መጠቀም ይቻላል የሚለው ነገር ላይ ትንሽ የግንዛቤ ማነስ ይስተዋላል። ያንን የግንዛቤ ክፍቶች ሸፍኖ ስኬታማ የሆነ ቀጠና ለመፍጠር እየሰራን እንገኛለን።»

ይላል የሙያ ወግ ኢኒሺየቲቭ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሶፎኒያስ ግርማ።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ?

ወጣቶች ብቃታቸውን እንዴት ማዘመን ይችላሉ?

ልደት አበበ/ Lidet Abebe