DiscoverDW | Amharic - Newsየአውሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ያልመከሩበት የአሜሪካ ሩስያ የዩክሬን ጦርነት ማስቆሚያ የሰላም እቅድ
የአውሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ያልመከሩበት የአሜሪካ ሩስያ የዩክሬን ጦርነት ማስቆሚያ የሰላም እቅድ

የአውሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ያልመከሩበት የአሜሪካ ሩስያ የዩክሬን ጦርነት ማስቆሚያ የሰላም እቅድ

Update: 2025-11-20
Share

Description

ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ የዩክሬኑን ጦርነት ሊያስቆም ይችላል የተባለ እቅድ መንደፋቸው ተሰምቷል። አንድ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው የተባሉ ሰውን ጠቅሶ አሶስየትድ ፕሬስ እንደዘገበው እቅዱ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በትላልቅ ጉዳዮች ላይ በሰጥቶ መቀበል እንዲስማሙ ጥሪ ያቀርባል።



የአውሮጳ ዲፕሎማቶች ግን ይህን መሰሉ እቅድ የአውሮፓ ኅብረትና ዩክሬንን ባልተሳተፉበት የትም አይደርስም ሲሉ ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። የኅብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ዛሬ የኅብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ብራሰልስ ውስጥ ስብሰባ ከመቀመጣቸው በፊት በሰጡት አስተያየት ሩስያ ሰላም ፈላጊ ከሆነች ቀደም ባሉት ጊዜያት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ታደርግ ነበር ሲሉ ተናግረዋል። የፖላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ኅብረቱ የሰላም ጥረቶችን እንደሚደግፉ አስታውቀው በጉዳዩ ላይ እኛም መምከር አለብን ብለዋል።



የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ዛሬ ከሚነጋገሩባቸው ጉዳዮች ውስጥ የአሜሪካንሩስያ የሰላም እቅድ ዋነኛው ነው። የሱዳን ጉዳይ ቤልጀየም የሚገኘውን የሩስያ ገንዘብ ለዩክሬን መስጠትና የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ይገኙበታል ። የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን በዛሬው ስብሰባ ትኩረት በተሰጣቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አነጋግረነዋል።



ገበያው ንጉሴ



ኂሩት መለሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአውሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ያልመከሩበት የአሜሪካ ሩስያ የዩክሬን ጦርነት ማስቆሚያ የሰላም እቅድ

የአውሮጳ ኅብረትና ዩክሬን ያልመከሩበት የአሜሪካ ሩስያ የዩክሬን ጦርነት ማስቆሚያ የሰላም እቅድ