DiscoverDW | Amharic - Newsበአማራ ክልል ከታሪፍ በላይ የሚጠየቅበት የህዝብ መጓጓዣ
በአማራ ክልል ከታሪፍ በላይ የሚጠየቅበት የህዝብ መጓጓዣ

በአማራ ክልል ከታሪፍ በላይ የሚጠየቅበት የህዝብ መጓጓዣ

Update: 2025-04-30
Share

Description

በአማራ ክልል ተሳፋሪዎች ከታሪፍ በላይ ዋጋ እየተጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ



በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሚደረገው ቁጥጥር የጠበቀ ባለመሆኑ የሕዝብ ተሸከርካሪ ባለንብረቶች ከታሪፍ በላይ እያስከፈሏቸው እንደሆነ ተሳፋሪዎቸ አመለከቱ፤ የትራንስፖርት ባለስልጣናት ደግሞ የቁጥጥር ሥራቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል፡፡



በአማራ ከልል ከወረዳ ወደ ወረዳ በሚደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተሳፋሪዎች ከታሪፍ በላይ እየከፈሉ በመሆኑ ለገንዘብ ብዝበዛ መዳረጋቸውን ገልጠዋል፡፡ አንዳንድ ባለተሽከርካሪዎች “ዘረፋ’’ በሚመስል ሁኔታ ነው ተጨማሪ የትራንስፖርት ክፍያ የሚጠይቁ ሲሉ ነው ሂደቱን የሚኮንኑት፡፡



አንድ ከቡሬ ባሕርዳር ደርሶ መለስ የሄዱ ግለሰብ በትክክለኛው ታሪፍ ደርሶ ለመመለስ 600 ብር መክፈል ሲገባቸው፣ ለደርሶ መልስ 800 ብር ለመክፈል መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡



ከደብረወርቅ ደብረ ማርቆስ 300 ብር ከፍለው መሄድ ሲገባቸው 500 ብር ከፍለው እንደተጓዙ ደግሞ ሌላ የደብረወርቅ ከተማ አስተያየት ሰጪ ይገልፃሉ፣ አንዳንድ የህዝብ ተሸከርካሪ ባለንብረቶች ትክክለኛ ታሪፍ የሚያሳይ ቲኬት ለተሳፋሪዎቸ አድለው ከመናኸሪያ ከወጡ በኋላ ተጨማሪ ክፍያ አስገድደው እንደሚያስከፍሉ አስተያየት ሰጪው ይናገራሉ፡፡



በአማራ ክልል የመንገዶች መዘጋት እያስከተለ ያለው ችግር



“በአንዳንድ አካባቢዎች ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪው እጠፍ ነው” አስተያየት ሰጪዎች



ለባሕርዳር በቅርብ እርቀት ወደሚገኙ ጎንጂና አዴት ወደተባሉ ከተሞች ሳይቀር ከፍተኛ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ መኖሩን ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የሚናገሩት፣ የ50ና 60 ብር ትራንስፖርት ዛሬ በግማሽ ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል፡፡



አንድ የቢቸና ከተማ አስተያየት ሰጪ የትራንስፖርት ዘርፉ በዝርፊያ ላይ ነው ሲሉ የጉዳዩን አስከፊነት ገልፀውታል፡፡



ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የትራንስፖርት ገልግሎት የሚሰጡ አካላትንአሰራር ዘወር ብሎ የሚያ አካል የለም ሲሉም የክትትልና ቁጥጥር ሂደቱን ተችተዋል፡፡



በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰውአለ አንዳርጌ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የተሸከርካሪ ባለቤቶች መኖራቸውን አመልክተው፣ በድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ ተጨባጭ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ የቁጥጥር ሥርዓቱንም በጥብቅ እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡



የአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ኮማንድ ፖስት



“የክትትልና ቁጥጥር ስራችን ተጠናክሯል” የእነማይ ወረዳ



“ ከቢቸና ደብረ ማርቆስ የትራንስፖርት ታሪፍ እስከ ቅርብ ጊዜ 180 ብር ነበር፣ ከነዳጅ ጭማሪ ጋር ተያይዞ አሁን ታሪፉ ወደ 192 ብር አድጓል፣ ወጣ ብለን ቁጥጥር ስናደርግ አንድ አሽከርካሪ በታሪፉ ቆርጦ ከመናኸሪያ ከወጣ ከወጣ በኋላ ከእያንዳንዱ ተሳፋሪ 120 ብር በመቀበል ያልተገባ የታሪፍ ጭማሪ ሲያደርግ በመያዙ እንዲቀጣ ተደርጓል፣ አሁን የስምሪት ባለሙያ፣ የመንገድና ደህንነት ባለሙያዎች ተመድበው የቁጥጥርና ክትትል ሥራው ተጠናክሯል፡፡”ብለዋል፡፡



የአማራና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ውሎ



“E-ticketing ስርዓት ጀምረናል” የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን



የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ዘውዱ ማለደ ህገወጥነትን ለመከላከል የክልሉ መንግስት የኤሌክትሮኒክስ ቲኬቲንግ (e-ticketing) ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩም ተናግረዋል፡፡



ሁሉም የሕዝብ ትራንስፖርት ከወረዳ ወረዳ፣ ከዞን ዞን የሚሄዱ፣ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ከመናኸሪ ሲወጡ በኤሌክትሮኒክስ ቲኬት ስርዓት እንደሚወጡ አመልክተዋል፡፡



አዲሱን ድጅታል የትኬት ስርዓት መጠቀም ከተጀመረ፣ ታዲያ ለምን ተጨማሪ ታሪፍ የቅሬታ ምንጭ ሆነ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል፣ አቶ ዘውዱ ሲመልሱ፣ “በኤሌክትሮኒክስ የትኬት ስርዓት ትኬት ከተቆረጠና መንገድ ከተጀመረ በኋላ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎቹ መንገድ ላ በማስቆም፣ ዋጋ ጨምሩ ባለት ተሳፋሪውን በማስፈራራትና በማንገራገር ተጨማሪ ታሪፍ ያስከፍላሉ፣ ጉዳዩ ትክክል መሆኑ ሲረጋገጥና ሪፖርት ሲደርሰን እርምጃ እንወስዳለን፣ ወስደናልም” ብለዋል፡፡



በአማራ ክልል በ256 የተሸከርካሪ መዳረሻዎቸ የኤሌከትሮኒክስ ቲኬት (e-ticketing) መጀመሩን ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡



ዓለምነው መኮንን



ታምራት ዲንሳ



ጸሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በአማራ ክልል ከታሪፍ በላይ የሚጠየቅበት የህዝብ መጓጓዣ

በአማራ ክልል ከታሪፍ በላይ የሚጠየቅበት የህዝብ መጓጓዣ