DiscoverDW | Amharic - Newsአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ክንፍ ወደ አዲስ ፓርቲነት ?
አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ክንፍ ወደ አዲስ ፓርቲነት ?

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ክንፍ ወደ አዲስ ፓርቲነት ?

Update: 2025-04-30
Share

Description

በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ክንፍ ራሱን ወደ አዲስ ፓርቲነት ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኑ ተገለፀ። በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን የሰነዶች ዝግጅት በማካሄድ "አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የመመስረት እንቅስቃሴ የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱ" ከመስራቾቹ መካከል አንዱ ለዶቼቬለ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት የማረጋገጥ ጉዳይ አሁንስ መፍትሔ አላገኘም፥ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ለመሰረዝ ያስቀመጠው ቀነ ገድብ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ህወሓት በበኩሉ ሕጋዊ ሰውነቱ በፕሪቶሪያ ስምምነት 'ፖለቲካዊ ውይይት' ሊመለስለት እንደሚፈለግ ሲገልፅ ቆይቷል።



ባለፈው ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓመተምህረት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ህዝብ በአጠቃላይ፣ ወጣቱ እና ምሁሩ ደግሞ በዋነኝነት የጀመሩት ፖለቲካዊ ትግል በተደራጀ መንገድ ለመምራት እና ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመሸጋገር ራሱን ወደ ፓርቲነት ለማሳደግ በመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሶ እንደሚገኝ ገልፆ የነበረው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን፥ በአዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንደሚቀላቀል አስታውቋል።



አዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢቤና ተቃውሞው



ዶቼቬሌ ብያንስ ከሁለት የቀድሞ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት የነበሩና የአሁኑ አዲስ በመመስረት ሂደት ላይ ባለው ፓርቲ መስራቾች እንዳረጋገጠው፥ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን የሰነዶች ዝግጅት በማካሄድ "አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የመመስረት እንቅስቃሴው የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱ" አረጋግጧል።



ከአዲሱ ፓርቲ ስያሜ ጋር በተያያዘ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራር እንዲሁም ከአዲሱ ፓርቲ መስራቾች መካከል የሆኑት እንዳሉን፥ 'የትግራይ ሊበራል ዴሞክራሲ ፓርቲ' የተሰኘ ስያሜ ከበርካታ አማራጮች መካከል አንድ ተደርጎ መቀመጡ ይሁንና ሌላ አማራጭ ስምም ሊወሰድ እንደሚችል ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ አዲሱ ፓርቲ የህወሓት አላማዎች ለማሳካት የሚሰራ ነው ተብሎ የተሰራጨ መረጃ መኖሩ፥ ይሁንና ይህ "ፍፁም ስህተት" ነው ሲሉ አክለዋል።



“መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃር



ከፓርቲ መስራቾች መካከል የሆኑት የመረጃ ምንጫችን የአዲሱ ፓርቲ ርእዮተ ዓለም በግልፅ ባያስቀምጡም "አብዮታዊ ዴሞክራሲ በፍፁም አይሆንም" ብለዋል ሲሉ ግን አረጋግጠዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ጥያቄ ለማቅረብ "ሂደት ላይ ነን" ሲሉም አስታውቀዋል። ተጨማሪ መረጃዎች በቀጣይ እንደሚገለፁ ተነግሯል።



በትግራይ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ይረጋገጥ ፤ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች



በሌላ በኩል ከሕጋዊ ሰውነት ማስመለስ ጋር በተገናኘ እስካሁን መቋጫ ያልተገኘለት ውዝግብ ውስጥ ያለው በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት፥ የፓርቲው ሕጋዊነት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት፣ በፖለቲካዊ ንግግር እና ውሳኔ የነበረው ሕጋዊነት ዳግም እንዲመልስ እንደሚሰራ ሲገልፅ ቆይቷል። እስካሁን የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት ያልተመለሰው በውስጥ በነበሩ ችግሮች ምክንያት መሆኑ ህወሓት በቅርቡ ገልፆ ነበር።



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህወሓት ነሓሴ 3 ቀን 2016 ዓመተምህረት የክልል ፓርቲ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ በልዩ ሁኔታ የምዝገባ እና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሰጥቶት እንደነበረ ገልፆ የነበረ ሲሆን፥ ይሁንና የተሰጠው ፍቃድ ተከትሎ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ተግባራት ባለመከወኑ ህወሓት ለሶስት ወራት ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ቦርዱ ማገዱ ባለፈው የካቲት 6 ቀን 2017 ዓመተምህረት ማስታወቁ ይታወሳል።



ከአዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ነዋሪዎች ምን ይጠብቃሉ?



ከዚህ በተጨማሪ ህወሓት በተሰጠው የሶስት ወራት የእግድ ግዜ ውስጥ የእርምት የተባሉ እርምጃዎች ካልወሰደ ደግሞ ምርጫ ቦርድ የህወሓት ምዝገባን በቀጥታ እንደሚሰርዝ መግለፁም አይዘነጋም። ይህ እግድ ከተጣለ ሶስት ወር ሊሞላ ቀናት ቢቀሩም ህወሓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠው እንደአዲስ የመመዝገብ ፍቃድ ይሁን እግድ እንደማይቀበለው በመግለፅ የነበረው የፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት በቀጥታ እንዲመለስለት የሰላም ስምምነቱ መሰረት በማድረግ እንደሚሰራ ከሳምንታት በፊት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ አማኑኤል አሰፋ ሰጥተውት በነበረ መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል።



በእነዚህ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የተደረጉ ጥረቶች አልተሳኩም።



ሚሊዮን ኃይለስላሴ



ታምራት ዲንሳ



ጸሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ክንፍ ወደ አዲስ ፓርቲነት ?

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ክንፍ ወደ አዲስ ፓርቲነት ?