DiscoverDW | Amharic - Newsየግብጽ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ማንዣበብ ለቀጣናው ስጋት ወይስ በረከት?
የግብጽ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ማንዣበብ ለቀጣናው ስጋት ወይስ በረከት?

የግብጽ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ማንዣበብ ለቀጣናው ስጋት ወይስ በረከት?

Update: 2025-04-29
Share

Description



የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ ባሳለፍነው ሳምንት ጅቡቲን ጎብኝተው ከጂቡቲው አቻቸው ከኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በጋራና በተለያዩ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ሥምምነት ተፈራርመዋል።ቀደም ሲል ከሶማሊያ እና ኤርትራ ጋር ወዳጅነቷን ያጠናከረችዉ ግብጽ አሁን ደግሞ ከሌላኛዋ የኢትዮጵያ ጎረቤት ጋር ከወትሮ የተለየውን ግንኙነት ለመፍጠር መጣሯ ምን ያመለክት ይሆን?

አብዱልፈታ አልሲሲ በባለፈው ሳምነቱ የጅቡቲ ጉብኝታቸው ከጅቡቲው አቻቻው ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ ጋር በቀይባህር ፈተና እየሆነ የመጣውን የመርከቦች ደህንነትና አጠቃላይ ቀጣናዊ የደህንነት መርህዎ ላይ ስምምነት መፈረማቸው ነው የተነገረው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በመገንባት እያጠናቀቀች ያለችውን የአፍሪካ ግዙፉ የሃይል ማመንጫ ግድብ አግባብነትን በመቃወም በኢትዮጵያ ጎረቤቶች ዙሪያውን በማንዣበብ ጥብቅ ግንኙነት እየፈጠረች ያለችው ካይሮ በአዲስ አበባ በመልካም አይን እንደማትታይ ግልጽ ነው፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጽእኖ



ግብፅለኢትዮጵያ ቁልፍ እና ወሳኝ አገር ከሆነችው ጂቡቲ ጋር አሁን ላይ እያካሄደች ያለችው ግንኙነት ደግሞ ይበልጥ በበርካቶች ዘንድ ስጋትን አጭሯል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን በቅርበት በመከታተል የሚታወቁት የፖለቲካ ተንታኝ አብዱራሃማን ሰይድ ለግብጽ በአፍሪካ ቀንድ መመላለስ ቀዳሚው ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት ያልተደረው የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሊሆን ይችላል ባይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ

“ከኢትዮጵ ጋር ከስምምነት ያልተደረሰበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ቀዳሚው ምክንያት ሊሆን ይችላል” የሚሉት ተንታኙ “ግድቡን በተመለከተ የግብጽ ስጋት ከፍተኛ ነው” የሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቀይባህል አገልግሎት መሻቷን ብግልጽ ማሳወቋ በጎረቤቶቿ ዘንድ ስጋት መፍጠሩን በመግለጽም ግብጽ ይህን ክፍተት ለመጠቀም እየጣረች መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የጅቡቲ እና ኤርትራ ግንኙነት እንደፈተና

ከዚህ ቀደም ግብጽ ከሶማሊያእና ኤርትራ ጋር በመሆን አስመራ ላይ በተፈራረሙት የጋራ ደህንነትን አብሮ የማስጠበቅ ባሉት ስምምነት የወደብ አገልግሎትን በመሻት ላይ ታች ስትል በነበረችው ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ጥረዋል፡፡ በወቅቱ ሰሞነኛዋ የአልሲሲ መዳረሻ ጅቡቲ የነዚህ አገራት ግብራበር ስትሆን አልተስተዋለም፡፡ ከኤርትራ ጋር የራሷ የሆነው ቅራኔ ያላት ጅቡቲ በዚህኛው የአልሲሲ ጉብኝት ከኤርትራ ጋርስ ያላቸውን የድንበር ውዝግብ ቁርሾ እንዲያወርዱ ጥረቶች ይደረጉ ይሆን፡፡ አቶ አብዱራሃማን ምልከታቸውን አጋርተውናል፡፡ “ለግብጽ ስትራቴጂ የጅቡቲ ተሶማሊያሳትፎ ወሳኝ ስለሆነ ግብጽ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ ልትሰራ ትችላለች” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የጅቡቲና ኢትዮጵያ ግንኙነት ይፈተን ይሆን

በግብጽ ወደ ጂቡቲ መምጣትለኢትዮጵያ እጅግ ወሳኝ አገር ተደርጋ የምትታየው ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን መልካም ጉርብትና እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ፈተና ውስጥ ትከት ይሆን የተባሉት ተንታኙ፤ ጅቡቲ ኢትዮጵያ ላይ ካላት ጥገኝነት ይብልጥ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ላይ ያላት ትቅም ጠንካራ ነው በማለት ሂለቱ አጋራት የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል አሁንም እድሉ ሰፊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡



ሥዩም ጌቱ



ነጋሽ መሐመድ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የግብጽ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ማንዣበብ ለቀጣናው ስጋት ወይስ በረከት?

የግብጽ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ማንዣበብ ለቀጣናው ስጋት ወይስ በረከት?