DiscoverDW | Amharic - Newsእንወያይ፤ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ከምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን?
እንወያይ፤ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ከምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን?

እንወያይ፤ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ከምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን?

Update: 2025-10-26
Share

Description

እንወያይ፤ መንግሥት በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የተሰበሰቡ የሕዝብ ጥያቄዎች ከ 2018 ቱ ምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን ?



በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ዓመታት የሥራ ጊዜ ተሰጥቶ በአዋጅ የተቀመጠለትን ኃላፊነት ለማስፈፀም ሲንቀሳቀስ የቆየዉ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ሥራዉን ባለማጠናቀቁ ባለፈዉ ዓመት የካቲት ወር ላይ የተራዘመለት፤ የአንድ ዓመት ተጨማሪ የሥራ ጊዜ ሊጠናቀቅ፤ የቀረዉ ሦስት ወራት ገደማ ብቻ ነዉ። ምክክር ኮሚሽኑ የተራዘመለት የሥራ ጊዜ ሲያበቃ፤ ከተለያዩ ክልሎች እና በዉጭ ሃገራት ከሚኖሩ ዜጎች ያሰባሰባቸዉን እና የቀረቡለትን አጀንዳዎች ይዞ ሕዝብ ከሚያስቀምጣቸዉ ተወካዮች ጋር ለዋናው ሀገራዊ ጉባኤ ተቀምጦ፤ ዐበይት ያላቸዉን ጨምቆ፤ በምክክር ሂደቱ፤ የለየኋቸው እና ምላሽ የሚያስፈልጋቸዉ፤ የቀረቡልኝ "እነዚህ ናቸው" ብሎ አጀንዳዎቹን ምላሽ እንዲሰጥበት፤ ለመንግሥት ያቀርባል። በዚሁ የምክክር ኮሚሽኑ የስራ ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ምንም እንኳን ኮሚሽኑ በቅርቡ ተቋሙ እንደ ተቋም መቀጠሉ ተገቢ መሆኑን የሚጠቁም ፍንጭ የሰጠ ቢሆንም።



መንግሥት በኮሚሽኑ በኩል፤ ከሕዝብ የቀረቡለትን መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል የሚባሉ ጥያቄዎችን ወይም አጀንዳዎችን ለሀገር ዘላቂ ጥቅም ሲባል ያስፈጽማል ወይም ይፈጽማል ተብሎ ይጠበቃል። ጥያቄዎቹን ለመመለስ ግን፤ ሰፊ ጊዜ፤ የገንዘብ አቅም፤ ብሎም ከባድ ስራ የሚጠይቅ ነዉ ሲሉ ከወዲሁ ብዙዎች አስተያየቶቻቸዉን ይሰጣሉ። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሰረት፤ መንግሥት በዚሁ በያዝነዉ ዓመት ብሔራዊ ምርጫን ማካሄድ ይኖርበታል። በቅርቡ የኢትዮጵያዉ ፕሬዚዳንት ታየ አስቀፅላሴ በዚህ በያዝነዉ 2018 ምርጫ እንደሚካሄድ በይፋ መናገራቸዉም ይታወቃል። መንግሥት ምርጫን ለማካሄድ ብሎም ከህዝብ የቀረበለትን ጥያቄዎች ለመመለስ ጊዜም፣ ሀብትም ያስፈልገዋል፤ ከባድ ስራም ይጠብቀዋል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ በሀገሪቱ ሰላም እና ፀጥታን ማስጠበቅ ይኖርበታል። ታዲያ መንግሥት ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከሕዝብ ሰበሰብኳቸው ያላቸዉን ጥያቄዎች ለመመለስ እና ከዝያም ተከትሎ ምርጫ ለማካሄድ ምን ያህል ብቁ ነዉ? አቅምስ አለዉ ?



ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - የኢዜማ ፓርቲ፤ መንግሥት ይህን ለማስፈፀም ጊዜ አለዉን ወይስ ሌላ የአምስት ዓመት ጊዜ ሊጠበቅ ነዉ ሲል ስጋቱን፤ ምላሽ ያስፈልገዋል ያለውን ጉዳዮች ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል።



በዚህ ዉይይታችን መንግሥት በያዝነዉ 2018 ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ለዓመታት የመከረባቸው እና መልስ ይሻሉ ሲል ላቀረበላቸዉ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ወይም አጀንዳዎች መልስ ለመስጠት ብሎም ብሔራዊ ምርጫን ለማካሄድ በቂ ጊዜ እና አቅም አለዉ?የሚለዉን እናነሳለን። በነዚህ ነጥቦች ላይ ሃሳባቸዉን ሊያካፍሉን፤



ዶክተር ዮናስ አዳዬ -- የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር



አቶ ጌትነት ወርቁ -- የእናት ፓርቲ አመራር እንዲሁም



በፈቃዱ ኃይሉ -- የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፤ ብሎገር እና የመብቶች እና የዲሞክራሲ እድገት ማዕከል(ካርድ ) መስራችና የቀድሞ ዳይሬክተር ቀርበዋል።



አዜብ ታደሰ



ነጋሽ መሐመድ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

እንወያይ፤ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ከምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን?

እንወያይ፤ መንግሥት ለሕዝብ ጥያቄዎች ከምርጫ በፊት መልስ ያገኝላቸዉ ይሆን?

Azeb Tadesse Hahn