DiscoverDW | Amharic - Newsየቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰብ የመቀላቀሉ የሥራ ሂደት
የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰብ የመቀላቀሉ የሥራ ሂደት

የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰብ የመቀላቀሉ የሥራ ሂደት

Update: 2025-08-13
Share

Description

እነዚህ የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው ያለው ተቋሙ አብዛኛዎቹ ከትግራይ ክልል መሆናቸውና ስልጠና፣ መታወቂያ እና «የአጭር ጊዜ መልሶ መቀላቀል ክፍያ» ተፈጽሞላቸው የተቀላቀሉ መሆናቸውን ገልጿል። የፕሪቶሪያ ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት «ወደ ግጭት የመሩ መሠረታዊ ችግሮች በፖለቲካ ውይይት እንዲፈቱ» ምክረ ሀሳብ ያመላከተ ቢሆንም በተግባር መጓተት በመኖሩን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አንድ ተንታኝ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ተንታኙ እንደሚሉት የስምምነቱ አንድ ተግባር የሆነው የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ የማዋሃድ እና መልሶ የማቀላቀል ተግባር ብቻ ሳይሆን ዋናው ስምምነት በራሱ «ትልቅ ጥላ አጥልቶበታል።»



የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን «በመደበኛ ሕጋዊ የሰላም ስምምነትም ሆነ በመንግሥት፣ በሀገር ሽማግሌዎች እና በሃይማኖት አባቶች የቀረቡ የሰላም ጥሪዎችን ተቀብለው»፣ የሰላም አማራጭን የተከተሉ ያላቸው በአራት ክልሎች ውስጥ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ አውርደው፣ ስልጠና ወስደው ወደ ማኅበረሰባቸው እንዲቀላቀሉና እንዲቋቋሙ መደረጉን የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ መሰለ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።



ተቋሙ ባወጣው መግለጫ መሰረት «ከኅዳር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በትግራይ 53,319፣ በአፋር 1,712፣ በአማራ 5,168 እና በኦሮሚያ 5,365 በድምሩ 65,500 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል።



የፕሪቶሪያን ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር በቅርበት የሚከታተሉ አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ "DDR" ወይም ትጥቅ የማስፈታት፣ መልሶ የማቋቋም እና የመቀላቀል የስምምነቱ ማዕቀፍ አንድ ጉዳይ በመሆኑ ከሙሉ ስምምነቱ ብቻውን ተነጥሎ መታየት የለበትም ብለዋል።



ሥራው ከፍተኛ ገንዘብ እና ልዩ አሠራር የሚጠይቅ ቢሆንም አሁን ባለው የሀገሪቱ ዓቅም እና እየቀነሰ ባለው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ምክንያት «ትጥቅ ማስፈታት፣ መልሶ መቀላቀል እና የማዋሃድ ተግባር ላይ ከፍተኛ እንቅፋት ፈጥሯል» ብለዋል።



ተንታኙ አክለውም ስምምነቱ «ወደ ግጭት የመሩ መሠረታዊ ችግሮችን በፖለቲካውይይት ለመፍታት» ውይይት እንዲደረግ ምክረ ሀሳብ አስቀምጦ የነበረ ቢሆንም በአግባቡ ባለመደረጉ አሁን ሌላ መልክ ያለው ውጥረት መኖሩንና ይህም የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል።



ኮሚሽኑ ብዛት ያለው የቀድሞ ታጣቂ መኖሩ፣ ሥራው ከፍተኛ ገንዘብ መጠየቁና በቂ ድጋፍ አለመገኘቱ፣ በአንዳንድ ክልሎች የሚታዩ ግጭቶችና «አደናቃፊ የፖለቲካ ሁኔታዎች» መኖራቸው «በታቀደው ልክ ለመፈፀም» እንደተቸገረ ከዚህ በፊት ገልጾ ድጋፍ ጠይቋል። የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ መሰለ ይህ ኃላፊነት በቀጣዩ ዓመት ተጠናክሮ እንዲከናወን ጥረት ይደረጋል ብለዋል።



የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ «ግጭትን ሊያስቀሩ የሚችሉ ሰላማዊ አማራጮችን በሁሉም አቅጣጫ ለመሞክርና በሰላማዊ መንገድ ለመታግል ለሚወስኑ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ» እንደሚሠራ አስታውቋል።



ሰሎሞን ሙጬ



ኂሩት መለሰ



ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰብ የመቀላቀሉ የሥራ ሂደት

የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰብ የመቀላቀሉ የሥራ ሂደት