DiscoverDW | Amharic - Newsየትራምፕ የእስያ ሀገራት ጉብኝት እና የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረት
የትራምፕ የእስያ ሀገራት ጉብኝት  እና የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረት

የትራምፕ የእስያ ሀገራት ጉብኝት እና የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረት

Update: 2025-10-27
Share

Description

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት ጀምሮ በእስያ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማሌዢያ የጀመሩትን የእስያ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ጃፓን በማቅናት ነገ ማክሰኞ የሀገሪቱን የመጀመሪያዋን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ታካይቺን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ትራምፕ በማሌዥያ፣ቆይታቸው በታይላንድ እና በካምቦዲያ መካከል በተደረገውን የሰላም ስምምነትፊርማ ላይ ታድመዋል ። በሌላ በኩል የአሜሪካ የንግድ ተደራዳሪዎች ከቻይና ጋር የንግድ ስምምነት ማዕቀፍ ላይ ደርሰዋል።ጉብኝቱ ዓላማው ምንድነው?ምንስ ይጠበቃል?በዚህ ወቅት እስያ ለምን?



የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረት



የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደቡብ እስያ ሃገራት ማህበር (ASEAN) እና ከእስያ ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ስብሰባዎች ጋር የተገጣጠመ የእስያ ጉብኝት ጀምረዋል። ይሄው ሁሉም አካላት በአጽንዖት የሚከታተሉት ጉዞ ፕሬዝዳንት ትራምፕን የአካባቢው የንግድ እና የደህንነት ውይይቶች ዋና ማዕከል አድርጓቸዋል። በዚሁ በማሌዥያ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮርያ በሚኖራቸው ቆይታ፣ አሜሪካ ቁልፍ ከሚባሉት አጋሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ዳግም የምታድስበት እድልም የመፍጠርን አላማ ሰንቀዋል። ከየሃገራቱ ጋ ያላትን አጋርነት፣ ከንግድ፣ ከደህንነት እና ዲፕሎማሲ ጋር በማቀናጀት በኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢ ሃገራት ላይ ያላትን ንቁ ሚና አጉልተው ለማሳየት ይሻሉ።



የታሪፍ ግጭቶችን ለማቆም



ከዚሁ ጉዞ ጋ ተያይዞ ከወራት የታሪፍ ግጭቶች በኋላ ዋሽንግተን እና ቤጂንግ ግጭቶችን ለአፍታ ለማቆም እና ለውይይት የተመቻቸ ሁኔታን ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላቸው እያሳዩ ነው። የአሜሪካ የመንግስት መዘጋት አሁን አራተኛ ሳምንቱን አስቆጥሯል። ሁለቱም ፓርቲወች ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ተስፋ እያሳዩ አይደለም። ከ750,000 በላይ ሰራተኞችን ከስራ ውጪ ሆነው፣ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያጣ ነው። ከዚህ አንጻር የትራምፕ ይሄንኑ የእስያ ጉዞ፣ የትራምፕ አስተዳደር ትኩረቱን በሃገር ውስጥ እየጨመረ ከሚሄደው ቀውስ እና የህዝብ ቅሬታ ወደ ውጪ ዲፕሎማሲና አለማቀፍ አመራር ለመቀየር ተስፋ አድርጓል።



የጉብኝቱ በጎ ተፅዕኖዎች



በእስያ ሃገራት ውስጥ የዚህ ጉዞ ተጸዕኖ በጎ ምልክቶች እየታዩ ነው። የኢኮኖሚ የንግድ ታሪፍ የማቆም ስምምነት ተስፋወችን ያየው የእስያ ኢኮኖሚ መነቃቃትን አሳይቷል። በዚህ ጉዞ እና ውይይት መሰረታዊ እና ዘላቂ የሚባሉ ስምምነቶች ባይጠበቁም ተደራዳሪዎች የታሪፍ ማቆሚያውን ለማራዘም፣ ቻይና የአሜሪካን የእርሻ እቃዎች ግዢወችን የምትጨምርባቸው ሁኔታወችን ለማመቻቸት እና በቴክኖሎጂ ንግድ ላይ ገደቦችን ለማቃለል የሚበጅ የሥምምነት ማዕቀፍ ላይ እየመከሩ ነው። ብርቅዬ የምድር ንጥረነገሮች አጠቃቀም እና በሰሚኮንዳክተር አቅርቦት መስመሮች ላይም ውይይቶች ተጀምረዋል። እነዚህ ድርድሮች ግን በአብዛኛው ፖለቲካ መረጋጋትን የሚፈጥሩ እንጂ መዋቅራዊ መፍትሄዎች እንዳልሆኑ እና ስከን ያለ እና ቀጣይነት ያለው መፍትሄ ካልመጣ የትኛውም በጎ ተስፋ በፍጥነት ሊጠፋ እንደሚችል የዘርፉ ባለሞያወች አመላክተዋል።



ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከካናዳ ጋር ያለው እሰጣ ገባ ዳግም አገርሽቷል። ኦታዋ የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን የፀረ-ታሪፍ አስተያየቶችን በመጥቀስ ማስታወቅያ መስራቷ ፕሬዝዳንት ትራምፕን አስቆጥቶ ውይይቶች እንዲቆሙ አዘዋል። ካናዳም ውይይቱ ዳግም እንዲቀጥል የማስታወቂያ ዘመቻውን በፍጥነት ገትታለች። አለመግባባቱ በብረት፣ በአሉሚኒየም እና በአውቶሞቢሎች ውስጥ አቅርቦት ስርዓቱን አናግቷል።





ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።



አበበ ፈለቀ



ፀሐይ ጫኔ



ሽዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የትራምፕ የእስያ ሀገራት ጉብኝት  እና የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረት

የትራምፕ የእስያ ሀገራት ጉብኝት እና የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውጥረትን የማርገብ ጥረት

አበበ ፈለቀ