DiscoverDW | Amharic - Newsየተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻ
የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻ

የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻ

Update: 2025-11-25
Share

Description

የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ -ዘመቻ



በተባበሩት መንግስታት ሴት ድርጅቶች፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚቃወም ዘመቻ ጀመሩ። ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2024 ዓመት ብቻ ወደ 50,000 የሚሆኑ ሴቶች እና ታዳጊ ሴት ልጆች በወዳጆቻቸዉ አልያም በቤተሰብ አባላት ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ መረጃ አዉጥቷል። የመንግሥታቱ ድርጅት አሳሳቢ ያለዉ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ግድያ በያዝነዉ ዓመትም ቁጥሩ አልቀነሰም አልያም ምንም አይነት ለውጥ አልመጣም ብሏል።

ፖለቲከኞች በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመዋጋት የበለጠ እንዲሰሩ በተባበሩት መንግስታት የሴት ድርጅቶች ጥሪ ቀርቧል። የ"ብርቱካን ዓለም" የተሰኘዉ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃቶችን ለማስቆም የተጀመረዉ ዘመቻ ሴቶች እና ልጃገረዶች፤ በህዝባዊ እና ዲጂታል ቦታዎች ላይ በተሻለ ሁኔታ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል አጽንዖትም ሰጥቷል። ለ16 ቀናት በሚዘልቀዉ በዚህ ዘመቻ በርካታ የመዝናኛ ቦታዎች እና ተቋማት ዉስጥ ብርቱካናማ መብራቶችን ወይም "ጥቃት ይቁም" የሚል ጽሁፎችን በማስቀመጥ ዘመቻዉ ለህዝብ እንዲታይ ተደርጓል። ዛሬ በጀመረዉ በዚህ ሴቶች ላይ ጥቃት ይቁም ዘመቻ ላይ የጀርመን ፌዴራል ሚኒስትሮች፣ አብያተ ክርስቲያናት እና የጀርመን እግር ኳስ ማህበር ተሳታፊ ናቸዉ። የመንግሥታቱ ድርጅት በዛሬዋ እለት ማለት በጎርጎረሳዉያኑ ኅዳር 25 ቀን 1999 በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲቆሙ ጥሪ የሚደረግበት ቀን ብሎ መታወጁ ይታወቃል።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻ

የተመድ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ይቁሙ - ዘመቻ