DiscoverDW | Amharic - Newsየትግራይ ክልል ኤኮኖሚ መቀዛቀዝ ወጣቶችን እያሰደደ ነዉ
የትግራይ ክልል ኤኮኖሚ መቀዛቀዝ ወጣቶችን እያሰደደ ነዉ

የትግራይ ክልል ኤኮኖሚ መቀዛቀዝ ወጣቶችን እያሰደደ ነዉ

Update: 2025-04-29
Share

Description

በትግራይ ከጦርነቱ በኃላ ይበልጥ የተበራከተው የወጣቶች ስራ አጥነት እና ስደት ለመቀነስ በኢኮኖሚ ዙርያ ሊሰራ ይገባል ተገለፀ። በክልሉ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ጨምሮ በርካታ ችግሮች ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማሕበራዊ ችግሮች ተባብሰው እንዲቀጥሉ ምክንያት መሆናቸው ተነግሯል።



ከጦርነቱ መቆም ከሁለት ዓመት በላይ ጭምር በትግራይ ይጠበቅ የነበረው ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት አሁንም አለመታየቱ ተከትሎ በዜጎች ላይ የተራዘመ ችግር መፈጠሩ እና የወጣቶች ስራ አጥነት እና ስደት መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ይገለፃል። ከጦርነቱ መቆም በኃላ ቃል የተገቡ የዳግመ ግንባታ እና የኢኮኖሚ ማንቃቅያ ስራዎች አለመተግበራቸው ብቻ ሳይሆን የቀጠለው ፖለቲካዊ ቀውስ ለዚህ ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ ይገለፃል። የትግራይ የንግድና ዘርፍ ማሕበራት ቦርድ አመራር አባል ዲበኩሉ አለም ብርሃነ፥ በትግራይ የተገኘው ሰላም ዘላቂ ለማድረግ በኢኮኖሚ ማነቃቂያ ላይ ትኩረት ያስፈልጋል ይላሉ።



በክልሉ እጅግኑ የተቀዛቀዘው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲያገገም ከሚያስፈልጉ ድጋፎች መካከል የከጦርነቱ በፊት ብድር እና ወለድ መሰረዝ መሆኑ የሚያነሱት በትግራይ ያሉ ባለሀብቶች፥ እንዲሰረዝ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ከጦርነቱ በፊት የተወሰደ ብድር እና ወለዱ መጠን በድምሩ ደግሞ 86 ቢልዮን ብር እንደሚደረስ መረጃ ያመልክታል። ከዚህ መፍትሔ ያልተገኘለት ጉዳይ በተጨማሪ በትግራይ የነዳጅ አቅርቦት እጅጉኑ መቀነስ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያስከተለ ስለመሆኑ ተገልጿል።



የክልሉ አስተዳደር አካላት እንደሚሉት በትግራይ 12 ነጥብ 5 ሚልዮን ናፍታ፣ 2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሊትር ቤንዚል በድምሩ 15 ሚልዮን ሊትር ነዳጅ በየወሩ የሚፈለግ ሲሆን ይህ ግን እየቀረበ አለመሆኑ ይገልፃል። በተለይም ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ደግሞ ወደ ትግራይ የሚቀርብ የነዳጅ መጠን አጅግኑ እየቀነሰ መጥቶ ሙሉበሙሉ መቆም ጨምሮ አሁን ደግሞ ከሚፈለገው እጅግ ያነሰ 3 ሚልዮን ሊትር በወር ወደ ትግራይ እየገባ መሆኑ የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ሐላፊ አቶ ገብረመስቀል ታረቀ ተናግረዋል።



ይህ ለማስተካከል ደግሞ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ንግግሮች መቀጠላቸው ሐላፊው ጨምረው ገልፀዋል። አቶ ገብረመስቀል "አቅርቦቱ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው ያለው፥ በዚህ ጉዳይ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ንግግሮች እየተደረገ ነው። ፕሬዝደንቱ ጨምሮ የንግድ ዘርፍ አመራሮች ከሚመለከታቸው እየተነጋገርን፣ ሙሉበሙሉ ቆሞ የነበረ የነዳጅ አቅርቦት በመግባባት በተወሰነ መጠን መግባት ጀምሯል። ከዚህ በፊት ግን ለሁለት ሳምንት ያክል አንዲት ሊትር እንኳን ያልገባበት ሁኔታ ነበረ" ብለዋል።



በትግራይ ያሉ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች የዳሰሰ ውይይት ሰሞኑን ከክልሉ ባለሀብቶች ጋር ያደረጉት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ለሁሉም እንቅሰቃሴ መሰረት የሆነ ሰላም ለማፅናናት አስተዳደራቸው እንደሚሰራ ገልፀዋል።



ሚሊዮን ኃይለሥላሴ



ነጋሽ መሐመድ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የትግራይ ክልል ኤኮኖሚ መቀዛቀዝ ወጣቶችን እያሰደደ ነዉ

የትግራይ ክልል ኤኮኖሚ መቀዛቀዝ ወጣቶችን እያሰደደ ነዉ