DiscoverDW | Amharic - Newsየኅዳር 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የኅዳር 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የኅዳር 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

Update: 2025-11-10
Share

Description

አርሰናልን ነጥብ ጥሏል ። ሊቨርፑል በማንቸስተር ሲቲ ጉድ ሁኗል ። ሦስተኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ቸልሲ እና 12ኛ ደረጃ ላይ በሰፈረው ብሬንትፎርድ መካከል የነጥብ ልዩነቱ አራት ብቻ ነው ። በቤርሊኑ ግጥሚያ ባዬርን ሙይንሽን የማታ ማታ በቁርጥ ቀን ልጁ ሔሪ ኬን ከሽንፈት ተርፏል ። በመኪና ሽቅድምድም የማክላረኑ አሽከርካሪ ላንዶ ኖሪስ ዳግም ድል ቀንቶታል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ውዝግብ አጥልቶበታል ።



43ኛው ጃንሜዳ ዓለም አቀፍ አገር አቋራጭ ውድድር



43ኛው ጃንሜዳ ዓለም አቀፍ አገር አቋራጭ ውድድር ትናንት እሁድ (ጥቅምት 30 ቀን፣2018 ዓ.ም) ተከናወነ ። በውድድሩ ላይ የቀድሞ ታዋቂ አትሌቶች መታደማቸው ታውቋል ። ውድድሮቹ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቃቸውም ተዘግቧል ። በውድድሩ ላይ የምስራቅ አፍሪቃ አትሌቲክስ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ሳዲቅ ኢብራሂም እና የታንዛኒያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ጆን ማንያማ በክብር እንግድነት መገኘታቸው ታውቋል ። ውድድሮቹ «አስደናቂ እንደነበሩ» መግለጻቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጧል ። የአደይአበባ ስቴዲየምን መጎብኘታቸውንም አክሏል ።



ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን ጉድ ሠራው



ማንቸስተር ሲቲ በፔፕ ጓርዲዮላ 1000ኛ የአሰልጣኝነት ዘመን ግጥሚያቸው ትናንት ሊቨርፑልን 3 ለ0 በማንኮታኮት አንዳች መልእክት አስተላልፏል ። ቀዳሚዎቹን ግቦች ከረፍት በፊት ግብ አዳኙ ኧርሊንግ ኦላንድ እና ኒኮ ጎንዛሌዝ አስቆጥረዋል ። ከረፍት መልስ ደግሞ በግራ ክንፍ የሊቨርፑል ተከላካዮችን ቁም ስቅል ሲያበላ የቆየው ጄሬሚ ዶኩ በድንቅ ሁኔታ ከመረብ አሳርፏል ። ውጤቱ ማንቸስተር ሲቲን ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲሰፍር ብቻ ሳይሆን ከመሪው አርሰናልም ጋር የነጥብ ልዩነቱን ወደ አራት ዝቅ እንዲል አስችሏል ። ማንቸስተር ሲቲ በወሳኝ ግጥሚያዎች ላይ ወሳኝ ድል በመቀዳጀትም ብቃቱን አስመስክሯል ። ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ወደ 8ኛ ደረጃ ተንሸራትቷል ።



የጥቅምት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ



ቀደም ሲል በነበረው ግጥሚያ አስቶን ቪላ በርመስን 4 ለ0 አበራይቶ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል ። ሦስተኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ቸልሲ እና 12ኛ ደረጃ ላይ በሰፈረው ብሬንትፎርድ መካከል የነጥብ ልዩነቱ አራት ብቻ መሆኑ የዘንድሮን ውድድር ብርቱ አድርጎታል ። ዳን ቡርን በቀይ ካርድ አጥቶ በ10 ተጨዋቾች የተወሰነው ኒውካስል ዩናይትድ በሜዳው ደካማ አጨዋወቱ ቀጥሎ ትናንት በብሬንትፎርድ 3 ለ1 ተረትቷል ። ኖቲንግሀም ፎረስት በበኩሉ ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ1 በማሸነፍ የራቀውን ድል ማስመለስ ችሏል፤ በደረጃ ሰንጠረዡ ግን ዎልቨርሐምፕተን ብቻ ነው የሚበልጠው ። ሁለቱ ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች 2 እና 9 ነጥብ አላቸው ።



ዑኒዮን ቤርሊን የባዬርን ሙይንሽን ልጓም



የባዬርን ሙይንሽን ግስጋሴን ዑኒዮን ቤርሊን ልጓም አበጅቶለታል ። ቤርሊን ከተማ አልተን ፎይርስተራይ ስታዲየም ውስጥ በነበረው ግጥሚያ ዑኒዬን ቤርሊን መጀመሪያ አንድ ለዜሮ ከዚያም ሁለት ለአንድ ሲመራ ቆይቶ ነበር ። የማታ ማት ግን ባዬርን ሙይንሽን በግብ ቀበኛው ሔሪ ኬን 90ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ ሁለት እኩል አቻ መውጣት ችሏል ። በዚህም ነጥቡ በአንድ ብቻ ከፍ ብሎ 28 ደርሷል ።



የሔሪ ኬን ከመረብ ያረፉ ኳስች ደግሞ 13 ደርሰዋል ። የቡድን አጋሩ ሉዊስ ዲያዝ፣ የቦሩስያ ሞይንሽንግላድባኁ ሐሪስ ታባኮቪች እና የአይንትራክት ፍራንክፉርቱ ዮናታን ቡርካርድት በስድስት ግቦች ይከተላሉ ። ቅዳሜ ዕለት ከባዬርን ሙይንሽን ጋር አቻ የተለያየው ዑኒዬን ቤርሊን በቡንደስሊጋው የደረጃ ሰንጠረዥ በ12 ነጥቡ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ። የጥቅምት 17 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ



ቅዳሜ ዕለት በሆፈንሀይም የ3 ለ1 ሽንፈት የቀመሰው ላይፕትሲሽ በ22 ነጥብ፤ ቦሩስያ ዶርትሙንድ እና ሽቱትጋርት እያንዳንዳቸው በ21 ነጥብ እስከ አራተኛ ደረጃ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነትን ቦታ ይዘዋል ። ባዬር ሌቨርኩሰን በ20 ነጥብ በአምስተኛነት የአውሮጳ ሊግ ስፍራን ሲይዝ፤ ሆፈንሀይም በ19 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሰፍሯል ። ሳንክት ፓውሊ በ7 ነጥብ ወራጅ ቀጣናው ጠርዝ ላይ ይገኛል ። ማይንትስ እና ሐይደንሀይም እያንዳንዳቸው በአምስት ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ መጨረሺያ ግርጌ ላይ ተዘርግተዋል ።



የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ውዝግብ



በቅርቡ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ምርጫ ያካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ውዝግብ እያስተናገደመሆኑ ተሰምቷል ። የተጨዋቾች የደሞዝ ክፍያን መፈጸም ያለመቻል፤ የንብረት ይገባኛል ጥያቄ እንዲሁም የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫ እና የአባላቱ የፍርድ ቤት እግድ ቡድኑን ሰቅዘው መያዛቸው እየተሰማ ነው ። በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮ ስፖርት መርኃ ግብር ዋና አዘጋጅ ምስጋናው ታደሰ ጉዳዩን በቅርበት ተከታትሏል ። ከአራት እስከ ስድስት ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው ተጨዋቾች እና የቡኑ አባላት መኖራቸውን ተናግሯል ።



በብራዚል ግራንድ ፕሪ የመኪና ሽቅድምድም የማክላረኑ አሽከርካሪ ላንዶ ኖሪስ ዳግም ድል ቀንቶታል ። የመርሴዲሱ አንድሬያ ኪሚ አንቶኔሊ ሁለተኛ የሬድ ቡሉ ማክስ ፈርሽታፐን ሦስተኛ ወጥተዋል ።



ማንተጋፍቶት ስለሺ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የኅዳር 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የኅዳር 1 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥዩም Mantegaftot Sileshi