የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአቶ ዳውድ ኢብሳ የጻፈው ደብዳቤ እና አንድምታው
Description
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በጻፈው ደብዳቤ ባለፉት ሰኔ 30 ማeና ሐምሌ 1 ቀን የተደረጉ የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባዎችን እንደገና እንዲያካሂድ ጠየቀ። ዶቼ ቬለ የተመለከተው ባለ ዘጠኝ ገጽ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ኦነግ ለሁለት ቀናት ያካሄደው ስብሰባ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ማቋቋሚያ አካሄድን የተከተለ እንዳልሆነ ነው።
በደንቡ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለማቋቋም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰብሰብ እንዳለበት ያመለከተው ደብዳቤው የምልዓተ ጉባኤው አልተሟላም ያለው ደብዳቤው በተለያዩ ምክንያቶች በጉባኤው ያልተገኙ የማክላዊ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የተገኙበት ጉባኤ ተደርጎ ለቦርዱ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።
በዚህም ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል የተባሉ አምስት ሰዎች ፣ አድራሻቸው አይታወቅም የተባሉ አራት ሰዎች እንዲሁም በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው ራሳቸውን አገለሉ የተባሉ ሰባት ሰዎች እና የኦሮሚያ ፖሊስ ተቀላቀሉ የተባሉ አባላት ቦርዱ በራሱ ጥሪ የሚያደርግላቸው መሆኑን አመልክቷል።
ቦርዱ በደብዳቤው ኦነግ ቀጣዩን የብሔራዊ ምክር ቤት ጉባኤ የሚያደርግበትን ቀን እና ሰዓት እንዲያሳውቀው የጠየቀ ሲሆን በዕለቱም ታዛቢ ቡድን እንደሚልክ አመልክቷል።
የስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ አስቀድሞ ኦነግ በሊቀመንበሩ በአቶ ዳውድ ኢብሳ እና በምክትላቸው አቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመሩ አንጃዎችን የፈጠረ መከፋፈል አጋጥሞት ነበር ።
በወቅቱ ግንባሩ በመንግስት ተፈጽሞብኛል ካለው የአመራር እስራት ፣ የአባላት ማሳደድ እና ወከባ እንዲሁም የቢሮ መዘጋት በተጨማሪ በውስጥ ተፈጥሮ የነበረው መከፋፈል ብርቱ ፈተና ደ,ቅኖበት አልፏል።
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ























