DiscoverDW | Amharic - Newsታዋቂው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ሲታወሱ
ታዋቂው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ሲታወሱ

ታዋቂው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ሲታወሱ

Update: 2025-11-10
Share

Description

በበርካታ የታሪክ መፃህፍቶቻቸው የሚታወቁት የታሪክ ሙህር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ ዴሌቦ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ታዋቂውን የታሪክ ሙህር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲጎለብት የሚያግዙ በርካታ የምርምር ስራዎችን የሰሩ ደፋር ሙህር ሲሉ ያስታውሷቸዋል።ፕሮፌሰር ላጲሶ የኢትዮጵያን ታሪክ ከመደብ ትግል አውጥተው በአግባቡ እንዲሰነድ አድርገዋልም ተብሏል።

በቀድሞው በከንባታ እና ሐዲያ አውራጃ በኩፋላ ሐበሌ ግንቦት 12 ቀን 1930 ዓ.ም የተወለዱት ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ሙህር ።የኢትዮጵያ ታሪክ የሁሉም መሆን አለበት። በሚለው መርሃቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር ላዺሶ፤ የአንዱን ብሔር ወይም ሐይማኖት ታሪክ ነጥለን ከፃፍን ትክክለኛው የሀገሪቱ ታሪክ ማወቅ አንችልም የሚል እምነትም ነበራቸው።በዚህ መሰረትም ፤ፕሮፌሰር ላፒሶ የኢትዮጵያ ረጅም የሕዝብና የመንግሥት ታሪክ ፣.የኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ መሰረቶችና መሳሪያዎች ፣የቀይ ባሕርና የዓባይ ሸለቆ ሚና እና አጭር የጌዴኦ ህዝብ ታሪክን ጨምሮ በርካታ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያተኮሩ መፃህፍትን ፅፈዋል።የፕሮፌሰሩን ህልፈት ተከትሎ፤ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ራሄል ባፌ ህልፈታቸውን በታላቅ ሀዘን መስማታቸውን ይገልፃሉ።ፕሮፌሰር ላፒሶ፤ ደፋር ሙህር ነበሩም ይላሉ።«በጣም ነው ያዘንኩት ዜና እረፍታቸውን ስሰማ በጣም እwqe የታሪክ ሙጅር ከመሆናቸውም በላይ የታሪክ ግድፈቶችን በተመለከተ ትክክለኛ እና እውነተኛ ታሪኮችን በመፃፍ እና በመግለጥ እጅግ ደፋር እና አቋም ያላቸው ሙህር ነበሩ።»በማለት ገልፀዋል።



የታሪክ ፀሀፊው አቶ ጥላሁን ጣሰው በበኩላቸው ቀደም ሲል አብዛኛውየኢትዮጵያ ታሪክ ከመደብ ትግል ጋር ይያያዝ እንደነበር ጠቅሰው ፤ ፕሮፌሰር ላፒሶ ግን ከዚህ አውጥተው የኢትዮጵያን ታሪክ በአግባቡ እንዲሰነድ በማድረጋቸው የሚደነቁ ሙህር መሆናቸውን ያስረዳሉ።«በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ታሪክ ወደ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ወደ መደብ ትግል በመዘዋወሩ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚገባውን ክብር መሰጠቱ ቀርቶ ሁሉም ታሪክ ከመደብ ትግል ጋር በመያያዙ ዝቅ ባለበት ወቅት እሳቸው ተነስተው የኢትዮጵያን ታሪክ በሰፊው መፃፍ የጀመሩ ናቸው።እና በዚህ በኩል አስተዋፅኦ ያላቸው ናቸው።»ካሉ በኋላ ፤«በዚህ በኩል አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው በግሌ »ብለዋል።



የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቢቾ ሆሣዕና ሚሽን ት/ቤት ፣የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ አዳማ በሚገኘው የአጼ ገላውዴዎስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ባይብል አካዳሚ የተከታተሉት ፕሮፌሰር ላፒሶ፤በፍልስፍና እና በታሪክ ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ ትምህርታቸውን በአሜሪካን ሀገር ተከታትለዋል። በኋላም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተው፤ ለሁለት ዓመታት በቨርጂኒያ ዩንየን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተዋል። የ1966ቱን የኢትዮጵያ አብዮት ተከትሎ ግን ወደ ሀገራቸው ተመልሰው፤ በታሪክ ምርምር እና በማስተማር አገራቸውን አገልግለዋል።ፕሮፌሰር ላፒሶ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ለሀገራቸው ከነበራቸው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ነው የሚሉት ዶክተር ራሄል፤ ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲጎለብት የሚያግዙ በርካታ የምርምር ስራዎችን መስራታቸውንም ያብራራሉ።



ፕሮፌሰር ላዺሶ፤ ከመምህርነታቸው እና ከታሪክ ፀሀፊነታቸው ባሻገር በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመገናኛ ብዙኃን ጠለቅ ያለ ትንተና በመስጠትም ይታወቃሉ። ከዚህ አንፃር «የማይተካ ነገር እንዳጣን ይሰማኛል» ይላሉ ዶክተር ራሄል።ነገርግን እንደ ዶክተር ራሄል ፤ፕሮፌሰር ላፒሶ ትተውት ያለፉት ነገር ለመጭው ትውልድ ጭምር የሚያስተምር ነው።ዶክተር ራሄል አይዘውም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።አቶ ጥላሁንም ፕሮፌሰር ላፒሶ፤ በስራዎቻቸው ሲታወሱ እንደሚኖሩ ገልፀዋል።



የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ፤ባለትዳር እና የሦስት ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን፤ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ዘግበዋል።የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሮፌሰር ላጲሶ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።



ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።



ፀሐይ ጫኔ

ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ታዋቂው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ሲታወሱ

ታዋቂው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ሲታወሱ