DiscoverDW | Amharic - Newsግጭት በሰሜን ወሎ ወጣቶችን ለህገ ወጥ ለስደት እየዳረገ ነው
ግጭት በሰሜን ወሎ ወጣቶችን ለህገ ወጥ ለስደት እየዳረገ ነው

ግጭት በሰሜን ወሎ ወጣቶችን ለህገ ወጥ ለስደት እየዳረገ ነው

Update: 2025-10-03
Share

Description

ጦርነት ስራ አጥነት በፈለጉት ቦታ በነፃነት መንቀሳቀስ አለመቻል በሰሜን ወሎ ዞን ዞብል ከተማ ለሚገኙ ወጣቶችሀገር ትቶ ለመሰደድ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡



አስተያየቱን ለዶቼቬሌ ያጋራው የዞብል ከተማ ነዋሪ እኔ በምኖርበት አካባቢከሳምንታት በፊት ጀምሮ ወጣቶች በህገወጥ መንገድ ይዞ ጉዞወደ አረብ ሀገራት ጀምረዋል፡፡ ለወትሮው አካባቢው በህገወጥመንገድ ድንበር ማቋረጡ ልማድ ያለበት ቢሆንም የአሁኑ ግንየባሰ መሆኑን ነው ስሙ እንዳይጠቀስ የሚፈልግ ወጣትየሚናገረው፡፡ ‹‹አሁን ማን አለ ሄደዋል የቀረነው 5 ወይም 6 ነን፡፡ ከተማይቱም ሀገሪቱም በቃ እኛ ያለንበት ሄደዋል፤በተለይከዚህ ከ3 ሳምንታት ወዲህ ባለትዳሩም፣ ትዳር የሌለውምነው እየወጣ ያለው፡፡››በማለት ገልጿል።



ጦርነትና ስራ አጥነት ለወጣቶች ስደት ምክንያት



ከሰሞኑ በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎች መካከል ጦርነት የተካሄደበት የሙጃ ከተማ ነዋሪ የሆነው ሌላ ወጣትም በአካባቢው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መኖሩን እና ሥራአጥነት እና የሰላም እጦት ምክንያት መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ ‹‹በርካታ ነው የሄደው ምን አግኝቶ ይረጋጋል፤ የስራ አጥነትአለ፤ የትምህርት እጥረት አለ፣ ሰርቶ እንዳይኖር ስራየለም፣ መሬቱም ጠባብ ነው ፣ በዚያ ላይ ሰላሙም አያሰራም፤ተንቀሳቅሶ ለመስራት ቀኑ ይከብዳል፡፡›› በኢትዮጵያ አማራጭ የሥራ እድል ማጣት በዞብል ከተማ እና ዙሪያው ላሉ ሴትና ወንድ ወጣቶች ፈተና ነው የሚለው አስተያየት ሰጭ የሰላም እጦትና ነፃነት ማጣት ተጨምሮበት ወላጆች ወልደው አሳድገው የልጆቻቸውን ለወግ ማዕረግ መብቃት እንዳያዩ አድርጓቸዋል ይላል፡፡ ‹‹ሁሉም ነገር ያስጠላል ሥራ የለም፤ ጦርነት አለ ከዚህ ሁላእዛ ሄጄ ወይም ያልፍልኛል ወይ እሞታለሁ ብሎስለሚያስብወደፊት ነው ነፃነትም ስለሌለ መሄድ ነው በዚህ ዓመት አድጎየተሻለ ሰው ሆኖ ያገባ ሰው ከተገኘ ለእኔተአምር ነው፡፡›› ብሏል።





በየቀኑ ሁለትና ሦስት መኪና ወጣቶች ይሰደዳሉ





በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦና አካባቢው ያሉ የገጠር ከተሞች ከዚህ ቀደም በህገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የሚጓዙ ወጣቶችመነሻ ቢሆንም አሁን ላይ ግን የወጣቱ በብዛት መጓዝተስፋ አስቆራጭ ሆኗል ይላሉ የአካባቢው ነዋሪ፤ ተደጋጋሚጦርነት እና የኑሮ ሁኔታ በምክንያትነት ይጠቅሳሉ፡፡ ‹‹ምን ስፍር ቁጥር አለው እኛ ጋ መሄድ ነው፤ በመኖርናበመሄድ ከሆነ የለም ባዶ ነው፤ ግን ምክንያቱ አንዱጦርነትሊሆን ይችላል ከዚያ የኑሮ ሁኔታ ተደራርበው ነው እንጂመሄድማ ቀላል ይሄዳል ›› በማለት ገልፀዋል።



ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በስፋት የሚካሄድባቸው አካባቢዎችበየቀኑ የሚጓዙ ወጣቶች መኖራቸውን የሚገልፁት አስተያየትሰጭ በየእለቱ 2 እና 3 መኪኖች ይጓዛሉ ይላሉ፡፡

‹‹ወርቄ፣ ዞብል አዲስ ቅኝ፣ መንደፍራ እነሱ ከፍተኛ ናቸው፡፡ ከዚያ ደግሞ ወደ ዋጃ ቀጠና ባቦኩርማ የሚባሉትበቀን 2 እና 3 መኪና ይወጣል፡፡›› ብለዋል።



ፖሊስ ከ30 በላይ ህገወጥ ስደተኛ ወጣቶችን ይዟል



በዚህ ዜና ዙሪያ የሰሜን ወሎ ዞን የሥራና ሥልጠና መምሪያኃላፊን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም ትናንት ከተለያዩ አካባቢዎችበህገወጥ መንገድ የኢትዮጵያን ድንበር ለማቋረጥ ሲጓዙ የነበሩ 34 ወጣቶችን መያዙን የባቲ ከተማ ፖሊስአስታውቋል፡፡ ኃላፊው ኮ/ር ሀሰን ሰይድ እንደገለፁት ከተያዙትውስጥ መነሻቸውን ሰሜን ወሎ ያደረጉት ስደተኞች አሉብለዋል፡፡



‹‹ጫካ ለጫካ ሲሄዱ ነው በጸጥታ ሀይሎች የተያዙት 7 ሴቶችና 27 ወንዶችያው ጫካ ነው አቋርጠው ነው የሚሄዱት ወደ ውጭ ለመሄድ ነው ፍላጎት ያላቸው ደላላአስኮብላዮች ቅስቀሳ እነሱ በሜዳ ላይአስተኝተዋቸው ነውጫካ ውስጥ ያገኘናቸው፡፡››



አማራ ክልልን ከአፋር ክልል የሚያገናኘውን የባቲን መስመርተከትለው በህገወጥ መንገድ ድንበር የሚያቋርጡ ወጣቶችመጨመር እየታየበት ነው የሚሉት ኮ/ር ሀሰን ተጓዦች በሀገርውስጥ ጭምር ነው ለከፋ እንግልት የሚዳረጉት ይላሉ፡፡ ‹‹እዚሁ ከሀገር ሳይወጡ ከፍተኛ ስቃይ ነው የሚደርስባቸውበየቱቦው ውስጥ እያሳደሯቸው የሚሄዱበት ሁኔታነውያለው አሁን ባለው ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመርታይቶበታል፡፡›› ሲሉ ነው የተናገሩት።



ኢሳያስ ገላው

ነጋሽ መሀመድ

ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ግጭት በሰሜን ወሎ ወጣቶችን ለህገ ወጥ ለስደት እየዳረገ ነው

ግጭት በሰሜን ወሎ ወጣቶችን ለህገ ወጥ ለስደት እየዳረገ ነው

ኢሳያስ ገላው