DiscoverDW | Amharic - Newsጂቡቲ ፤ የጅቡቲ ፓርላማ የፕሬዚዳንቶችን የእድሜ ገደብ አነሳ
ጂቡቲ ፤ የጅቡቲ ፓርላማ የፕሬዚዳንቶችን የእድሜ ገደብ አነሳ

ጂቡቲ ፤ የጅቡቲ ፓርላማ የፕሬዚዳንቶችን የእድሜ ገደብ አነሳ

Update: 2025-11-02
Share

Description



የጂቡቲ ፓርላማ ለፕሬዚዳንታዊ ውድድር ያስቀመጠውን የዕድሜ ገደብ አነሳ ። ፓርላማው ትናንት ቅዳሜ ለፕሬዚዳንታዊ ውድድር የሚቀርብ ዕጩ የዕድሜ ገደብ ማንሳቱ በስልጣን ላይ ላሉት የ77 ዓመቱ ኢስማኤል ዑመር ጊሌህ ለዘጠነኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ ዕድል ይፈጥርላቸዋል። ፓርላማው ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የዕድሜ ገደቡን ለማንሳት የቀረበውን የዉሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን የፓርላማውን አፈ ጉባኤ ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የፓርላማው አፈ ጉባኤ ዲሌይታ መሀመድ ዲሌታ ለዜና አገልግሎቱ በተለይ “የብሔራዊ ምክር ቤቱ የእድሜ ገደብ እንዲነሳ ዛሬ አፅድቋል።» ብለዋል።

ጂቡቲ ቀደም ሲል ከ75 ዓመት ያለፋቸው ሰዎች ለፕሬዚዳንታዊ ዕጩነት እንዳይወዳደሩ የሚከለክል ህግ ነበራት ።





ዑመር ጊሌህ ወደ ፕሬዚዳንታዊ ስልጣን የመጡት በጎርጎርሳዉያኑ 1999 ሲሆን ያለፉትን 25 ዓመታት ያህል በስልጣን ላይ ቆይተዋል።

የጂቡቲ የህግ አውጪው አካል ያሳለፈውን አዲሱን ውሳኔ ተከትሎ ዑመር ጊሌህ በመጪው የጎርጎርሳዉያኑ 2026 በሚደረገው እና ብዙም ተቀናቃኝ ይኖርባቸዋል ተብሎ በማይጠበቅበት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።



ፓርላማው ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በጉሌህ ተቀባይነት ያገኘውን ረቂቅ ሃሳብ ለመጨረሻ ዉሳኔ ድምጽ እንዲሰጥበት ለሕግ አውጪው አካል ልኮ ነበር።

አፈ ጉባኤ ዲሌታ ቀደም ሲል ለዜና ወኪሉ እንዳሉት “ትንሿ አገር፣ ችግር በበዛበት፣ በአፍሪካ ቀንድ፣ ከሶማሊያ፣ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ጋር ያለውን የተረጋጋ ግንኙነት ለማረጋገጥ” ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ አስፈላጊ ነው ። በጎርጎርሳዉያኑ 2021 ጂቡቲ ያስተናገደችውን የመጨረሻውን ምርጫ ጉሌህ 97 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሲያሸንፍ ፓርቲያቸውም አብላጫውን የፓርላማ መቀመጫ ተቆጣጥሯል። ኢስማኤል ዑመር ጊሌህ የቀድሞውን የጂቢቱ የነጻነት አባት ተብለው የሚታወቁትን ሃሰን ጉሌድ አፕቲዶን ለ22 ዓመታት ዋና አማካሪያቸው ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ነበር የተኳቸው።



አንድ ሚሊዮን ገደማ ብቻ ህዝብ እንዳላት የሚነገርላት ጂቡቲ በቀይ ባህር በተለይ ስልታዊ ጠቀሜታ ባለው የባብኤል መንደብ የንግድ መስመር ላይ ትገኛለች። የምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ማኅበረሰብዋና መስሪያ ቤት መቀመጫ የሆነችው ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ ዋነናዋ የወደብ አገልግሎት አቅራቢ ከመሆኗ ባሻገር እንደ አሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ፈረንሳይ ፣ ጃፓን እና ጣልያን ለመሳሰሉ ኃያላን ሃገራት የጦር ሰፈር ሰጥታለች።



ታምራት ዲንሳ



ጸሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ጂቡቲ ፤ የጅቡቲ ፓርላማ የፕሬዚዳንቶችን የእድሜ ገደብ አነሳ

ጂቡቲ ፤ የጅቡቲ ፓርላማ የፕሬዚዳንቶችን የእድሜ ገደብ አነሳ