DiscoverDW | Amharic - Newsረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ
ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ

ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ

Update: 2024-03-15
Share

Description



በስላም ተጀምረዉ የሚጠናቀቁ የኢትዮጵያ ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ከቅርብ ግዜ ወዲህ የመንግስት የፀጥታ ችግር እየሆኑ መምጣታቸዉ ተነገር። በዓላቱን ከሚታደሙት፤ ታዳሚውን የሚጠብቁት እየበለጡ፤ የከተማው መንገድ እየተዘጋ በአብዛኛዉ ከበዓሉ 2 ቀናት በፊት ጭምር እየተዘጋ ለእንቅስቃሴ ፈተና የሚሆንበት ግዜ እየጨመረ መጥቷል ተባለ። ለዚህም በኢትዮጵያ በሚከበሩ የህዝብ እና ሀይማኖታዊ በዓላትአከባበሩን ለመወሰን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ የቀረበለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲወያይበት ቆይቶ ጉዳዩን ለሁለት ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶታል። ቋሚ ኮሚቴዎቹ ከሚነጋገሩባቸው ነጥቦች አንዱ የሆንውን በሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ በአላት ቀን የሚታየውን ሰንደቅ አላማ በተመለክተ ይሆናል ተብሏል «DW» ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

የሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ በዓላት ለማክበር ሲውጣ ይህን ልበሱ ያንን አውልቁ ከማለት ይልቅ በዓሉን ስርዓት ማስያዝ ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል። በበዓላት ቀን ስው የፈለገውን ለብሶ ቢወጣ ምንም ችግር የለውም፤ እንዲያውም ያላወቅነውን የምናውቅበት እና የምናይበት ይሆናል ሲሉም አክለዋል። በኢትዮጵያ የሃይማኖት እና የህዝብ በዓላትን እና አከባበሩን በተመለከተ የአዋጅ መሻሻል ሲደረግ ከ 5 አስርት ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያው ሲሆን አዋጁ ተሻሽሎ ሲወጣ ሀገሪቱ ያሏትን የህዝባዊ በአላትን ቁጥር ከማስቀመጡም በላይ ኃይማኖታዊ እና ብሔራዊ የህዝብ በዓላት ሲከበር የሚታዩ ሰንደቅ አላማ ላይ ወሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።





ሃና ደምሴ





አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ

ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ