DiscoverDW | Amharic - Newsእንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በአማራ ክልል
እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት  በአማራ ክልል

እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በአማራ ክልል

Update: 2025-12-07
Share

Description

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጎርጎሪያኑ ህዳር 25 እስከ ታህሳስ 10 እየተካሄደ ያለውን «የፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ይቁም የ16 ቀናት ዘመቻ » ምክንያት በማድረግ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሶስት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ ጾታዊ ጥቃት ይደርስባታል።ጥቃቱ በአብዛኛው የቅርብ በምትለው ሰው የሚፈፀም ነው።



ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በኢትዮጵያ ስር የሰደደ ችግር ሲሆን፣ በአገሪቱ እየተከሰቱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች ሳቢያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ቀደም ሲልም በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ለሁለት አመታት የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጾታዊ ጥቃት ተፈፅሟል።ቁጥሩ ይለያይ እንጅ ጦርነቱ በተስፋፋባቸው የአማራ እና አፋር ክልሎችም ጥቃቱ መፈፀሙን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልፀዋል።



በአማራ ክልልምላለፉት ሁለት አመታት በፌደራል መንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭትም ይህንኑ ጾታዊ ጥቃት ማባባሱ ይነገራል።የአማራ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሰሞኑን አዲስ ማለዳ ለተባለ አንድ የሀገር ውስጥ መገናኛ ዘዴ እንደገለፀው በመንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው እና ከሁለት አመታት በላይ በዘለቀው ግጭት ህጻናትን ጨምሮ 3,036 ጾታዊ ጥቃቶች ተመዝግበዋል። በክልሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ በቅርቡ ባወጣው የምርመራ ዘገባም ከ2600 የሚበልጡ ሴቶች በመንግስት ወታደሮች መደፈራቸውን አመልክቷል።

የሕግ አስከባሪ አካላት መዋቅር መፈራረስ፣ የታጠቁ አካላት መብዛት፣ መፈናቀል እና የጤና ጥበቃ አገልግሎቶች መስተጓጎል ሴቶችን ለወሲባዊ ጥቃቶችእንዲሁም ጥቃቱን ተከትሎ ለሚመጣ ጉዳት እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል።እነዚህ ጥቃቶች በህይወት በተረፉ ሰዎች ላይ ከባድ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ከማድረስ ባለፈ ቤተሰቦችን ያፈራርሳሉ፣ ማህበረሰብን ያናጋሉ ፣ ዘላቂ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዘዞችም ያስከትላሉ።

ግጭት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የዛሬው የእንወያይ ዝግጅት ትኩረት ነው።



ይህ ውይይት በሴቶች ወሲባዊ ጥቃቱ አባባሽ ምክንያቶች፣በጥቃቱ ሰለባዎች እና በማህበረሰቡ ላይ ሀገር የሚያደርሰው ጉዳት ምንስ መደረግ አለበት የሚለውን ይዳስሳል።





በውይይቱ የተሳተፉ፤

⦁ ስህን ተፈራ፤ ሴታዊት የተባለ በጾታ ፍትህ ላይ የሚሰራ ተቋም መስራች እና ዳይሬክተር

⦁ ማህሌት ዳዲ ገብረመስቀል፤ የአፍሪቃ የሴቶች ሰላም እና ፀጥታ ተቋም የፕሮግራም ማኔጀር

⦁ አቶ ያሬድ ሀይለማርያም ፤የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ናቸው።



ሙሉ ውይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት  በአማራ ክልል

እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በአማራ ክልል