DiscoverDW | Amharic - Newsየአፍሪካ ኅብረት እና ኢኮዋስ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ-መንግሥት አወገዙ
የአፍሪካ ኅብረት እና ኢኮዋስ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ-መንግሥት አወገዙ

የአፍሪካ ኅብረት እና ኢኮዋስ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ-መንግሥት አወገዙ

Update: 2025-12-07
Share

Description

የአፍሪካ ኅብረት እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ወይም ኢኮዋስ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ-መንግሥት “በጥብቅ እና በማያሻማ ሁኔታ” አወገዙ። የሁለቱ ተቋማት ውግዘት የተሰማው ራሳቸውን “የመልሶ ማቋቋም ወታደራዊ ኮሚቴ” ብለው የሚጠሩ የተወሰኑ ወታደሮች በቤኒን ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ፕሬዝደንት ፓትሪስ ታሎን ከሥልጣን መባረራቸውን ከገለጹ በኋላ ነው።



የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ “በመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራው የተሳተፉ ሁሉም ተዋናዮች በአፋጣኝ ሁሉንም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲያቆሙ እና ያለመዘግየት ወደ ሕጋዊ የጦር ሠፈሮቻቸው እና ሙያዊ ግዴታዎቻቸው እንዲመለሱ” አሳስበዋል።



የቤኒን መንግሥት ለሰዓታት የዘለቀውን መፈንቅለ-መንግሥት እንዳከሸፈ ዘግየት ብሎ አስታውቋል። የመፈንቅለ-ሙከራው መክሸፉን የገለጹት የቤኒን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አላሳኔ ሰይዱ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ወታደሮቹ “መንግሥትን እና ተቋማቱን ለማተራመስ አመጽ እንደጀመሩ” ከሰዋል።



የቤኒን ጦር ለሪፐብሊኩ አሁንም ታማኝ እንደሆነ የቤኒን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አላሳኔ ሰይዱ ገልጸዋል።



ለፕሬዝደንቱ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጭ ፓትሪስ ታሎን ደሕና መሆናቸውን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ፕሬዝደንቱ “የቴሌቭዥን ጣቢያ ብቻ በሚቆጣጠሩ ጥቂት ሰዎች” ተጠነሰሰ ያሉትን መፈንቅለ-መንግሥት እንዳወገዙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።



መደበኛው ጦር መልሶ በመቆጣጠር ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የመረጃ ምንጭ ዋና ከተማዋ ኮቶኑ እና ሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ መሆናቸውን ተናግረዋል።



“የኮቶኑ የጥጥ ንጉሥ” በሚል ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት የ67 ዓመቱ ታሎን በመጪው ሚያዝያ ሥልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የቀድሞው ነጋዴ ቤኒን በመሩባቸው አስር ዓመታት ሀገሪቱ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብታሳይም የጂሐዲስቶች ግጭት ተስፋፍቶባታል።



ባለፉት ዓመታት በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙት ኒጀር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ጊኒ እና በቅርቡ ጊኒ ቢሳው እና ማዳጋስካር መፈንቅለ-መንግሥት አስተናግደዋል።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአፍሪካ ኅብረት እና ኢኮዋስ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ-መንግሥት አወገዙ

የአፍሪካ ኅብረት እና ኢኮዋስ በቤኒን የተሞከረውን መፈንቅለ-መንግሥት አወገዙ

Eshete Bekele