የአሜሪካ የሰላም ልኡክ በሞስኮ
Description
የሩሲያና ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም አሜሪካ ያቀበረችው የሰላም ሀሳብ በሚስተር ስቴቨ ዊትኮፍ፤ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የሞስኮ ልዩ መልክተኛ በሚመራ ሉኡክ አማካይነት ትናት ለፕሬዝዳንት ፑቲን ቀርቦ ለበርካታ ሰአታት የቆየ ውይይት የተደርገበት መሆኑ ተግልጿል። ከውይይቱ በኋላ ከክሬምሊን የወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሰላም እቅዱን እንዳለ ባይቀበሉትም ግን ደግሞ በሙሉ እንዳልተቃወሙትና ቀጣይ ውይይቶች የሚያስፈልጉት መሆኑን የሚገልጽ ነው።
የፕሬዝዳንት ፑቲን ከፍተኛ አማካሪ ሚስተር ዩሪ ዩሻኮቭ ዩኪሬንሩሲያ ክምትፈልገው የዶንባስ ግዛት ጦሯን ሳታስወጣ ከሰላም ስምምነት መድረስ እንደማይቻል ለጋዜጠኞች በሰጡት መገልጫ አስታውቀዋል። የአሜሪካ መልክተኞች በበኩላቸው ውይይቱ ጠቃሚና ገንቢ ነበር ማለታቸውም ተዘግቧል።
በሰላም ዕቅዱ የተነሱ አከራራክሪ ነጥቦች
ሩሲያ ዩክሬን ከያዘችው የዶንባስ ግዛት ለቃ እንድትወጣ ያቀረበችው ጥያቄ፤ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል ለመሆን ያላትን ዕቅድ መተዋን በይፋ ማስታወቅ አለባት የሚለውና ሌሎች የደህንነትና የዳግም ግንባታ ጉዳዮች በስፋት ውይይት የተደረገባቸውና ከስምምነት ያልተደርሰባቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በአውሮፓውያኖች ላይ ያሰሙት ቅሬታና ውንጀላ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫአውሮፓን ክፉኛ የሚከስና የሚወንጀል ተደርጎ ተወስዷል። “ሁልግዜ ጦርነትን ነው የሚሹት። የሰላም ሀሳብ ብለው የሚያቀርቡት የቀረበውን የአሜርካንን የሰላም ዕቅድ ለማደናቀፍ ያለመ ነው። እኛ በአውሮፓ ጦርነት የመክፍት ፍላጎትም ዕቅድም የለንም። በድንገት ጦርንት ከከፈቱብን ግን ዝግጁ ነን” በማለት የአሜርካው የሰላም ሀሳብ እንዳይሳካ የሚሰሩት በዋናነት አውሮፖች መሆናቸውን ገልጸዋል። ሞስኮ የምትቀበለውና በቀጣይ ልትወያይበት የምትሻውም አሜሪካ ባቀረበችው ባለ 28 ነጥቦች የሰላም ዕቅድ ላይ እንጂ በሌላ የአውሮፓውያኖቹ ፍላጎቶች በታጨቀበት የሰላም ሀሳብ እንዳልሆነም ከክሬምሊን ተጠቁሟል።
በዚህ የሰላም ዕቅድ በቀረበበት ወቅት ፕረዚደንት ፑቲን በተላይ በአውሮፓውያኑ ላይ ከፍተኛ ክስና ወቀሳ ያቀረቡበትን ምክንያት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዴሞክራሲ ጥበቃ ማእክል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ጆን ሃርዲ እንደሚሉት አላማው አሜሪካንን ካውሮፓ ወዳጆቿ መነጠል ነው።
የፕሬዝዳንት ትራምፕ በዩክሬን እርቅ የማውረድ ተነሳሽነት ምክንያቱ
የፕሬዝዳንት ትሩምፕ የሰላም ዕቅድና እርቅ የማውረድ ፍላጎት የኤኮኖሚና ንግድ ፋላጎትም ያለበት እንደሆነ ይነገራል። በሎንደን የቻትሀም ሃውስ የዩክሪን ፎረም አስተባባሪ ሚስ ኦሪሲያ ሉትሴቬይች ፕሬዝዳንት ትራምና ቤተሰባቸው ከሩሲያ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት መጠቀም የሚፈልጉ መሆናቸው የሚታወቅ መሆኑን አንስተው፤ ዋናው ነገር ግን አሉ፤ “ሰላም ማምጣት የሚችሉ፤ የተናጋሩትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ለማሳየትና በአሜሪካ ምርጫም ጠንካራ ሆኖ ለመታየትና የማይቻለውን ማድረግ የሚችሉ መሪ ሆኖ ለመታየት ነው” ሲሉ የፕሬዝዳንት ትራምን ፍላጎትና ምኞት ገልጸዋል።
ዕቅዱ ካልተሳካ ፕሬዝዳንት ትራም ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?
ወይዘሮ ሉትሴቪች በሰላም ዕቅዱ ላይ ከስምምነት ካልተደረሰ ማን ምን ሊያግኝ ወይም ሊጎዳ ይችላል ለሚለው ጥያቄ’፤ “ትራምፕን ማን ቀድሞ ያስቆጣቸዋል የሚለው ላይ ነው እርምጃው የያለው። በዩክሬን ከተቆጡ ሊወስዱት የሚችሉት ትልቁ እርምጃ ለዩክሬን የሚስጡትን የመረጃ ድጋፍ ማቋረጥ ነው። ይህ ድጋፍ ሩሲያን ዘልቅ ለማጥቃትና ለአየር መከላከያ ወሳኝ ነው። በሌላ በኩል በሩሲያ ከተቆጡ በተለይ ከሩሲያ ነዳጅ በሚገዙ ሶስተኛ አገሮች ማዕቀብ የመጣል እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ” በማለት ከየትኛው ጎን ሊቆሙ እንደሚችሉና ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግን ክወዲሁ ማወቅ እንደሚያስቸግር ገልጸዋል።
በሰላም ዕቅዱ የአውሮፓውያን አስተያየት
የሰላም ዕቀዱ በሩሲያ ድጋፍ አላገኘም መባሉአውሮፓንቀድሞም ብለን ነበር በማለት ሰላም ሊወርድ የሚችለው ዩክሬንን የበለጠ በመርዳትና በሩሲያ ላይ የሚደረገውን ጫና በማጠናከር ሩሲያን ማስገደድ ሲቻል ብቻ መሆኑን እየገለጹ ነው። ዛሬ እዚህ ብራስል የተካሂደው የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት የሚኒስትሮች ስብሰባ ዩክሬይንን የበለጠ ለመርዳትና በሩሲያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና አጠናክረው ለመቀጠል የወሰኑ መሆናቸው ተገልጿል።
ገበያው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ፀሐይ ጫኔ























