DiscoverDW | Amharic - Newsየጀርመን ፕረዚዳንት የለንደን ጉብኝት
የጀርመን ፕረዚዳንት የለንደን ጉብኝት

የጀርመን ፕረዚዳንት የለንደን ጉብኝት

Update: 2025-12-03
Share

Description

ለፕረዚደንቱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል



የፌድራል የጀርመን ፕሬዘደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እና ባለቤታቸውን ኤልኬ ቡደንበንደርን በብሪታኒያ ንጉስ ቻርለስ በተደረገላቸው የክብር ግብዣ ለሶስት ቀናት የይፉ ጉብኝት በዛሬው እለት ብሪታኒያ ገብተዋል። የጀርመኑ ፕሬዘደንት ለንደን ሂትሮው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የብሪታኒያው አልጋ ወራሽ ልኡል ዊሊያምና ባለቤታቸው ልእልት ካትሪን ከፍተኛ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፍራንክ-ቫልተር ስቴይንሜየርእና ባለቤታቸው ከልደን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከልኡል ዊሊያምና ልእልት ካትሪን ጋር በክብር ታጅበው ዊንዘር ከተማ ሲደርሱ በተዘጋጀላቸው ሰረገላ በዊንዘር ከተማ ለአቀባበል ለወጣው ህዝብ ሰላምታ በመስጠት ዊንዘር ቤተመንግስት ሲደርሱ ንጉስ ቻርልስና ንግስት ካሜላ በወታደራዊ የክብር ሰልፍ ትዕይንት በታጀበ ታላቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።



በ27 ዓመታት ውስጥ በጀርመን መሪ የተደረገ የመጀመሪያው ጉብኝት ነው





ዊንዘር ከብሪታኒያ ዋና ከተማ (40 ኪሜ) ከማዕከላዊ ማለትም ለንደን በስተ ምዕራብ በኩል የምትገኝ ከእንግሊዝ እና ከብሪቲታኒያ ንጉሣዊ ቤተሰብ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላት ከተማ ናት። ስቴይንሜየር የብሪታኒያ የክብር ጉብኝት በ27 ዓመታት ውስጥበጀርመን መሪ የተደረገ የመጀመሪያው ጉብኝት ነው። ንጉስ ቻርልስና ንግስት ካሜላ ካደረጉላቸው የክብር አቀባበል በኋላ ኘሬዘደንቱ ወደ ለንደን በማቅናት ከሰዓት በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኬይር ስታርመር ጋር ዳውኒንግ ስትሪት በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ በመገኘትን ከብሪታኒያና ከጀርመን የንግድ ተቋም አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ ያተኮረው ብሪታኒያና እና ጀርመን ባለፈው ሐምሌ ወር በለንደን ከተማ የኬንሲንግተን ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የተፈራረሙትን የአጋርነት ውል ሁለቱ አገራት “በቅርበት እንደሚሰሩ”እና ውሉን ለማጠናከር የተደረገ ውይት መሆኑ ታውቋል።





ስምምነቱ የትምህርት ቤት ልውውጥ ጉብኝቶችን እና የፓስፖርት የኤሎትሮኒክ በሮች ነፃ ማድረግ፣ አንዲሁም በብሪታኒያና እና በጀርመን መካከል ቀጥተኛ የባቡር መስመር ከለንደን እስከበርሊን መዘርጋት እና እንዲሁም በንግድ፣ በደህንነት በመከላከያ ላይ የበለጠ ትብብር ለማድረግ ቁርጠኝነትን ያካተተ ውይይት ነበር ።



በብሪታኒያ ፖርላማ ለብሪታኒያ የህዝብ እንደራሴዎች ንግግር ያደርጋሉ





ሽታይንማየር ከብሪታኒያው ጠቅላይ ሚንስትር ጋር የነበራቸውን ውይት ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ዊንዝር ቤተመንግስት በማቅናት በንጉስ ቻርልስና ንግስት ካሜላ ልኡል ዊሊያምና ልእልት ካትሪን በታሪካዊው የንጉሣዊ መኖሪያ ቤት በቅዱስ ጊዮርጊስ አዳራሽ ውስጥ በተዘጋጀላቸው የራት ግብዣ ላይ ለመገኘት ወደ ዊንዘር ቤተመንግስት እቅንተዋል።በግብዣው ላይ 160 የክብር እንግዶች ይገኛሉ. ሐሙስ ጠዋት በቤተ መንግሥቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቻፕል ውስጥ በሚገኘው የሟች ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊ መቃብር ላይ አበባ አስቀምጠዋል፣ የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ወደ ለንደን በማቅናት በብሪታኒያ ፖርላማ ለብሪታኒያየህዝብ እንደራሴዎች ንግግርያደርጋሉ አርብ እለት ደግሞ የጀርመን ፕሬዝዳንት እና ባለቤታቸ ከልዑል ኤድዋርድ፣ የኬንት መስፍን ጋር በመሆን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመኖች በቦምብ በከፍተኛ ሁኔታ በተደበደበችው ኮቨንትሪ ወደተሰኘችው ከተማ በመጓዝ የኮቨንተሪ ካቴድራል ፍርስራሽ ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።





ዋናው የኘሬዘደንቱ የኮቨንትሪ ጉብኝት በ1940 እም በጀርመን የአየር ጥቃት 568 ሰዎች የተገደሉበትንና እና 4,300 ቤቶች የወደሙበት አካባቢና እና የቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን የወደመበትን 85ኛ አመት የመታሰቢያ ክብረ ብአል ይገኛሉ። እንዲሁም በ1962 የተጠናቀቀውን አዲሱን ካቴድራል ይጎበኛሉ። በእለቱምሩ ለሰላም እና ለእርቅ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ቁርጠኝነት በሚያጎላ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይም ፕሬዘደንቱና ባለቤታቸው ይሳተፋሉ። ከዚያም የሶስት ቀን የብሪታኒያ የክብር ጉብኝታቸውን በማጠቃለል ወደ ጀርመን ይመለሳሉ።

ድልነሳው ጌታነህ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የጀርመን ፕረዚዳንት የለንደን ጉብኝት

የጀርመን ፕረዚዳንት የለንደን ጉብኝት