DiscoverDW | Amharic - Newsጤናና አካባቢ፤ የኮሌራ ስርጭት
ጤናና አካባቢ፤ የኮሌራ ስርጭት

ጤናና አካባቢ፤ የኮሌራ ስርጭት

Update: 2025-04-15
Share

Description

ከንጽህና ጉድለት ጋር በተያያዘ የሚከሰተውና ዋና የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከሚባሉት መካከል ኮሌራ አንዱ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሽታው በተቅማጥና በማስታወክ መልክ የሚታወቅ ሲሆን አፋጣኝ ህክምና ካልተደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት እንደሚያደርስም ይታወቃል፡፡ የኮሌራ ስርጭት በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በርካቶች መታመማቸውንና ህይወትም ማለፉን የጤና ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

የኮሌራ በሽታ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መከሰቱ መረጋገጡ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ አልማው በብሔረሰብ አስተዳደሩ ጃዊ ወረዳ ቀደም ሲል ኮሌራ መሰል በሽታ ተከስቶ ሠዎች ታመመው እንደነበር አስታውሰው፣ ናሙና ወደ ባሕር ዳር ህብረተስብ ጤና ተቋም ለምርመራ ተልኮ «በሽታው ኮሌራ መሆኑ ተረጋግጧል» ብለዋል፡፡ ከ160 በላይ ሠዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧልም ነው ያሉት፡፡ በሽታው ከተከሰተባቸው አካባቢዎች መካከል ምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ “በርሚል ጊዮርጊስ” እና “ኪዳነምህረት” በተባሉ ሁለት ቦታዎች ቀደም ሲል የነበረው የኮሌራ በሽታ አገርሽቶ ሠዎች በኮሌራ እየተጠቁ መሆናቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጉርባ ገልጠዋል፡፡

በሽታው ባለበት እንዲቆምና የሠዎች እንቅስቃሴ እንዲገታ ቀደም ሲል ከዞኑ ሀገረ ስብከት ጋር ስምምነት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱ የፀበል አገልግሎቱ ለጊዜው እንዲቆም ወረቀት ከመፃፍ ባለፈ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባለማድረጉ የበሽታው ስርጭት ማገርሽቱን ነው ምክትል ጤና መምሪያ ኃላፊው የሚናገሩት፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስቸጋሪ በመሆኑ በፀበሉ አካባቢ ያሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ማከናወን እንዳልተቻለ ሌላኛው ምክንያት እንደሆነ አቶ ዮሴፍ አመልክተዋል፡፡



የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ምላሽ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ አባ ኃይለማሪያም ያሳይ በበኩላቸው ከየካቲት 14/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 29/2017 ዓ.ም የፀበል አገልግሎቱ ተቋርጦ መፀዳጃ ቤቶችና የመጠጥ ውሀ አገልግሎት በአካባቢው እንዲጀመሩ ቢፈለግም የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋምና የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተግባሩን ሊፈፅሙ ሳይችሉ እንደቀሩ አመልክተዋል። ሆኖም ቤተክርስቲያኗ በራሷ ጥረት አስፈላጊ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት ካለፈው ሳምንት ጀመሮ የፀበል አገልግሎቱን ላልተወሰን ጊዜ እንዲቆም መወሰኗን ገልጠዋል፡፡

የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም መግለጫ

የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ በሽታው ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በአማራ ክልል 3 ወረዳዎች መከሰቱንና ከ1ሺህ 400 በላይ ሠዎች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ “የኮሌራ በሽታ ከታህሳስ 23/2017 ዓ.ም እሰከ መጋቢት 28/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ፣ ሰሜን ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ፣ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወርዳና በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተከስቶ ከ1ሺህ 400 በላይ ሠዎች በበሽታው ተይዘው በህክምና ላይ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡ ከተቋሙ ባገኘነው ተጨማሪ መረጃ መሰረት 12 ሠዎችም በበሽታ ህይወታቸው አልፏል፡፡ አብዛኛዎቹ በሽታው የተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀበል ቦታዎች መሆናቸውን የተናገሩት አቶ በላይ፣ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናዎን የፀበል አገልግሎቱ ለጊዜው እንዲቋረጥ የሀይማኖት አባቶች ጥረት እንዲያደርጉና መንግሥትም ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡





የኮሌራ ስርጭት በጋምቤላ ክልል “እየቀነሰ ነው” መባሉ

የኮሌራ በሽታ ከአማራ ክልል በተጨማሪ በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ከየካቲት 3/2017 ዓ. ም ጅምሮ በአኮቦ፣ መኮይ፣ ላሬ፣ ዋንቱዋ፣ ጂካዎ ወረዳና ጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ተከስቶ ከ2ሺህ በላይ ሠዎች በበሽታው ተይዘው እንደነበርና 23ቱ ህይወታቸው እንዳለፍ የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጋትቤል ግርማል ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ መንግሥትና ህብረተሰቡ ባደረጉት ርብርብ በሽታው እየቀንሰ እንደሆነና አሁን ከደቡብ ሱዳን በሚያዋስኑ ሁለት ወረዳዎች ብቻ ችግሩ

እንዳለ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡



የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ዋና ዳይሪክተር አቶ በላይ በዛብህ በሽታው ከቁጥጥር ውጪ ባይሆንም በርካታ ሠዎች የሚገለገሉባቸውና ኮሌራ የታየባቸው ሁሉም የፀበል ቦታዎች ለተወሰን ጊዜ አገልግሎቱን አቁመው በሽታው እንዳይሰራጭ የሚያደርጉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች እንዲሰሩ ሁሉም እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡

ህብረተሰቡም የበሰሉ ምግቦችን ሳይቆዩ እንዲመገብ፣ እጅን በሳሙና በደንብ መታጥብና ውሀን አፍልቶና አቀዝቅዞ እንዲጠጣ የጤና ባለሙያዎችና ኃላፊዎች አሳስበዋል፡፡ በ2015 ዓ.ም በአማራ ክልል በተመሳሳይ 4ሺህ ሰዎች በኮሌራ ታምመው እንደነበርም ዳይሬክተሩ አቶ በላይ አስታውሰዋል፡፡

አጠቃላይ የኮሌራ በሽታ ስርጭት ምን ይመስላል? የሚለውን ለማወቅ ሰሞኑን ለፌደራሉ ህብረተሰብ ጤና ተቋም ምክትል ዳይሬክተር መረጃውን በተናጠል ለመስጠት እንደማይችሉና በቅርቡ ከሚመለከታቸው የጤና ኃላፊዎች ጋር በጋራ እንድሚሰጡ ተናግረዋል፡፡



ዓለምነው መኮንን

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ጤናና አካባቢ፤ የኮሌራ ስርጭት

ጤናና አካባቢ፤ የኮሌራ ስርጭት

ዓለምነው መኮንን