DiscoverDW | Amharic - Newsሐማስን ትጥቅ የማስፈታቱ ጉዳይ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?
ሐማስን ትጥቅ የማስፈታቱ ጉዳይ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?

ሐማስን ትጥቅ የማስፈታቱ ጉዳይ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?

Update: 2025-10-18
Share

Description

የእሥራኤል ጦር ጋዛ ሠርጥ ውስጥ ከነበረበት ይዞታ ካፈገፈገ በኋላ ሐማስ የጋዛ ሰርጥን ፀጥታ ለማስከበር እና ሥርዓት አልበኝነትን ለማስቆም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተዘግቧል ። ሐማስ በተቀናቃኞቹ ኃላት ላይም የግድያ ቅጣት እየፈጸመ መሆኑም ተዘግቧል ። ሐማስን ትጥቅ የማስፈታቱ ጉዳይ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?



ሐማስ በተለይ ወንጀለኞች የሚላቸውን ላይ ብርቱ ርምጃ እየወሰደ ነው ። የተቀናቃኝ ጎሳ የሆኑ ሰዎችን በወንጀለኞች እና «ከሐዲዎች» በሚል ስም በጥይት አለያም በስቅላት እየገደለ ነው ይላል የኬርስተን ክኒፕ ዘገባ ። አንዳንድ የሞት ፍርዶች በራሱ በሐማስ ጭምር በምስል እና ድምፅ እየተቀረጹ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች እየተሰራጩ ነው ። የተለያዩ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት፦ ሰዎቹ አንድም ግድያ በመፈጸም አለያም ለእሥራኤል በመሰለል በሚል በሐማስ የተከሰሱ ናቸው ሲልም ይቀጥላል ዘገባው ።



በጀርመን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች በርካታ አገራት አሸባሪ ድርጅት የሚል ስያሜ የተሰጠው የሐማስ ታጣቂዎች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ጦርነቱ ባበቃ ጥቂት ጊዜያት ውስጥ ሰልፎች አድርገዋል ።



ሐማስ ላለመጥፋቱ መልእክት ማስተላለፍ ይሻል



የእስራኤሉ ሀሬትስ ጋዜጣ ላይ እንደዘገበው የሐማስ ሚሊሻ አሁንም በርካታ ተዋጊዎች እንዳለዉ ዘግቧል ። እነዚህ አሁን በጋዛ ሰርጥ ጎዳናዎች እና አደባባዮች ላይ ዕየታዩ ነው ። በእየሩሳሌም የዕብራይስጥ ዩኒቨርሲቲ የእልምና ጥናት ተቋም ባልደረባ ሲሞን ቮልፍጋንግ ፉክስ ሐማስ በጋዛ ሠርጥ አለመጥፋቱን ይልቁንም መኖሩን ለማሳየት መልእክት ማስተላለፍ ይሻል ብለዋል።



«ሐማስ በሕዝቡ ላይ ኹከት እና መከራ አመጣ ያለው የእሥራኤል ጦር ይዞታውን በቀየረ ጥቂት ጊዜ ውስጥ እንደ ፖሊስ ኃይል በመንቀሳቀስ እና ኃይሉን ከተማዋ ውስጥ ቦታ ቦታ በመያዝ ብሎም ተባባሪ የሚላቸውን ለማደን በአካባቢው መኖሩን ማሳየቱ አከራካሪ ነው ብዬ አላስብም ። በዚያ ላይ ሐማስ ፈጽሞ የጠፋ ሳይሆን በአካባቢው ሚና መፈጸሙ የሚቀጥል መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው ።»



ምናልባትም የሐማስ ጦር ትጥቅ በራሱ ጊዜ ይፈታል የሚለው አጠራጣሪ ሁኗል ። በጋዛ ሰርጥ ጦርነቱ እንዲያከትም ከፍተኛውን ሚና በቀዳሚነት ያስጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በዕቅዳቸው መሠረት ሐማስ ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ መፍታት አለበት ። ፕሬዚደንቱ፦ ሐማስ በምንም መልኩ «የእሥራኤል የፀጥታ ሥጋት እንዳይሆን» በሚል «ጦር መሣሪያ መፍታት እንዳለበት» እሥራኤል በቆዩበት ወቅት ተናግረው ነበር ።



ፕሬዚደንቱ ከእሥራኤል መልስ በረራ ላይ በነበሩበት ወቅት ግን፦ ሐማስ በጊዜያዊነት ጦር መሣሪያውን እንዲታጠቅ መንግሥታቸው ፈቃደኛ መሆኑን መናገራቸው ተደምጧል ። ሐማስ ከጦርነቱ በርካታ ወራት በኋላ ዳግም ሥርዓት ለማስከበር እየጣርኩ ነው ይላል ። ሲሞን ቮልፍጋንግ ፉክስ ።



«ትጥቅ መፍታትን በተመለከተ ምናልባትም የርቀት ተወንጫፊ መሣሪያዎችን በተመለከተ ከተለያዩ የሐማስ ተወካዮች ጭምር እጅግ ተጻራሪ መግለጫዎችን ነው የምንመለከተው ። ምናልባትም እነዚህ የጦር መሣሪያዎች በሌሎች በዓረብ ተወካዮች ለምሳሌ በግብጽ መንግሥት ጥበቃ ስር የሚሆኑ ከሆነ በሚሉ በአንዳንድ በተወሰኑ ቅድመ ኹኔታዎች ይህንን ለማድረግ ፈቃደኞች እንደሚሆኑ ጠቁመዋል ። ለኔ ግን ከመግለጫዎቹ በእርግጥ ጎላ ብሎ የታየኝ ይህማ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው የሚለው እና እሱንም ለማስወገድ የሚፈልጉት ነገር ነው ።»



ለመሆኑ የጋዛ ሠርጥ ደህንነት የማስጠበቁ ኃላፊነት የማን ነው?



ሐማስ ከሁለት ዓመት በፊት እሥራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከሰነዘረበት ጊዜ ጀምሮ ጋዛ ሠርጥ በእሥራኤል ጦር ቁጥጥር ስር በመቆየቷ ሐማስን ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ ማስፈታት አስቸጋሪ እንደሚሆን ይነገራል ። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ2007 ጀምሮ የፍልስጥኤም ግዛቶች አካባቢን እንዲቆጣጠር ኃላፊነት ተሰጥቶት የነበረው መንግሥት የፖሊስ እና የውስጥ ደሕንነት ላይ ብቻ እንዲያተኩር ነበር የተፈቀደለት ። እናም ሳይመለስ የቀረው ጥያቄ ይህን ኃላፊነት ወደፊት ማን ነው የሚወስደው የሚለው ነው ።



ኬርስተን ክኒፕ/ ማንተጋፍቶት ስለሺ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ሐማስን ትጥቅ የማስፈታቱ ጉዳይ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?

ሐማስን ትጥቅ የማስፈታቱ ጉዳይ ምን ያህል ተጨባጭ ነው?