DiscoverDW | Amharic - Newsየማገዶ ጭራሮ እየለቀሙ የሚማሩ የኮሌጅ ተማሪዎች
የማገዶ ጭራሮ እየለቀሙ የሚማሩ የኮሌጅ ተማሪዎች

የማገዶ ጭራሮ እየለቀሙ የሚማሩ የኮሌጅ ተማሪዎች

Update: 2025-10-18
Share

Description

ከ40 አመት በላይ መምህራንን በማሰልጠን የሚታወቀዉ የደሴ መምህራን ማሰልጠልኛ ኮሌጂ በመምህርነት በዲግሪና ዲፕሎማ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች በወር ለምግብ የሚሰጣቸዉ 760 ብር ለመኖር ስላላስቻላቸዉ ሰዉ ቤት ተቀጥረዉ በቤት ሰራተኝነት ከጫካ ጭራሮ እየለቀሙ የራሳቸውን ምግብ ለማብሰል መገደዳቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ ተማሪዎች አንዱ በእንጨት ለቀማ ወቅት ሕይወቱ እንዳለፈም ሰልጣኞቹ ተናግሯል።



ነገ ተማሪዎችን ለማስተማር የሚሰለጥኑ መምህራን የሚማሩትን ሳይሆን የሚበሉትን በማሰብ የማገዶ እንጨት በመልቀም፣ የቀን የጉልበት ሠራተኛ በመሆን፣ እንዲሁም ሊጥ አብኩተው ለምግባቸው የሚሆን እንጀራ በመጋገር ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ ነው የተባለው።



«በወር የሚከፈለን 760 ብር ነው፡፡ አንድ እንጀራ ለመግዛት ዋጋው ውድ ነው፡፡ ከዚህ ኑሮ ውድነት በመነሳት እኛ ወንዶች ኩሽና ተፈቅዶልን እንጀራ እየጋገርን እንኖራለን፡፡ ጭሱም ይወጋናል፤ አይናችንን ለማንበብ በጣም እንቸገራለን፡፡ »



«እንጨት ለመልቀም ወጥቶ የሞተ ተማሪም አለ»



በ760 ብር የምግብ ወርሃዊ ክፍያ የመኖሪያ ቤት ተሰጥቷቸው በኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት በኋላ የሚመገቡትን ምግብ ለማብሰል በደሴ ከተማ ወደሚገኙ የጦሳ፣ አዘዋና ሌሎች እንጨት ለመልቀም ወደሚያስችላቸው ጫካዎች ሲያመሩ ከሞት ጋርም ተጋፍጠዋል፡፡



‹‹እንግሊዝኛ ትምህርትክፍል የዲግሪ ተማሪ ነበረ ሳሙኤል ይባላል። ለመማር በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በጦሳ ተራራ እንደዚሁም በመሳሰሉት በአዘዋ ተራራ ካለቀምን በስተቀር እንጨት አይገኝም እሱም በጦሳ ተራራ ሊለቅም ሄዶ ነበር በህዳር 28 ቀን ህይወቱ አልፏል፡፡»



ችግሩ በተለይ ሴቶች ላይ የጎላ ነው የምትለው ሠልጣኝ ተማሪ የግማሽ ቀን የቤት ሰራተኝነትና በሌሎች ስራዎች እራሳችን እየደጎምን ነው ትምህርት የምንማረው ትላለች፡፡



«የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ባለን አቅም እየሰራንም ነው የምንማረው በትምህርታችን ላይ ውጭ ውለን ስንገባ እየደከመን ማጥናት እንቸገራለን እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ፡፡»



«አሁን አሁንማ ሥራም ጠፍቷል»



አሁን የቀን ስራ ሰርተን ለመማር የማንችልበት ጊዜ ላይ እንገኛለን የሚለው ተማሪ ወቅታዊ ሁኔታው ተጨማሪ ስራ ሰርተን ለመማር አላስቻለንም ይላል::



«ሴቶች የግማሽ ቀን ስራ ካገኙ ይሰራሉ ወንዶች ቅዳሜና እሁድ ይሰራሉ።ዘንድሮ ግን የለም፤ መስራት አትችልም የተግባር ልምምድ ስለምንሄድ ትንሽ ከበድ ይላል። ባለፈው አመት ይሻላል ውጭ ላይም ትንሽ አስፈሪ ነው ሰዓቱ።»



በትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው መባሉን



የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መምህር አበበ ደሴ እንደሚገልፁት ተማሪዎች የዕለት ኑሯቸውን በማሰብ ስለሚጠመዱ ትምህርት የመቀበል አቅማቸው ውስን ሆኗል ብለዋል፡፡



«ግማሾች የቀን ስራ ሰርተው ነው የሚኖሩት። ሴቶችም ቢሆኑ በእንጀራ ጋጋሪና ካፍቴሪያ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው። ክፍል ውስጥም ገብተው ስታይ በአብዛኛዉ ከሚማሩበት የሚያንቀላፉበት ነው የሚበልጠው። ወጥተው የሚመገቡት የለም ፡፡»



የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ በበኩላቸው ተማሪዎቹ ያሉበት ችግር ለመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ያሉ ሲሆን ወርሃዊ የምግብ ክፍያቸውም ከ670 ብር ከፍ እንዲል ለክልሉ ትምህርት ቢሮጥያቄ አቅርበናል ይላሉ፡፡



«በአብዛኛው ከመማር ማስተማሩ ይልቅ ስለ እሚበሉት፣የሚጠጡት ነው የሚያስቡት በትምህርት ላይ ተፅዕኖ አለው። ይህንን ታሳቢ አድርገን ክልል ላይም ጥያቄ እያቀረብንነው፡፡»



በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአማራ ክልልት ምህርት ቢሮ የስራ ኃላፊዎችን ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፡፡



ኢሳያስ ገላው



ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የማገዶ ጭራሮ እየለቀሙ የሚማሩ የኮሌጅ ተማሪዎች

የማገዶ ጭራሮ እየለቀሙ የሚማሩ የኮሌጅ ተማሪዎች

ኢሳያስ ገላው