DiscoverDW | Amharic - News«እምቦጭ አሁንም ለጣና ሥጋት ነው»
«እምቦጭ አሁንም ለጣና ሥጋት ነው»

«እምቦጭ አሁንም ለጣና ሥጋት ነው»

Update: 2025-10-18
Share

Description



በጣና ሐይቅ ላይ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው የእምቦጭ አረም ከመቀነስ ይልቅ ወደሌሎች አካባቢዎች እየተስፋፋ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ነው፣ አረሙ ከዚህ ቀደም ባልታየባቸው ሰሜን ጎጃም አቸፈረ ወረዳና ባሕር ዳር ከተማ አካባቢም መስፋፋት ጀምሯል፡፡ የሐይቁ ህልውና በደለልና በሌሎች አዳዲስ አረሞችም ፈተና እየገጠመው መምጣቱ እየተገለፀ ነው፡፡



እምቦጭ አረም ከመቀነስ ይልቅ እየሰፋ ስለመምጣቱ





ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የጣና ሐይቅ ዳርቻ ቀበሌዎችና በሐይቁ ላይ መታየት የጀመረው የእምቦጭ አረም አድማሱን በማስፋት ወደ ሰሜን ጎጃምና ባሕር ዳር አካባቢ በመግባት ለሐይቁ ህልውና ፈተና መሆኑን ቀጥሏል፡፡

አረሙን ለማጥፋት በሰፊ የሠው ኃይልና በማሽን የታገዙ የተለያዩ ሥራዎች ሲሰሩ ቢቆዩም አረሙን የማስወገዱ ሥራ ካለፉት 2 ዓመታት ጀምሮ በመቀዛቀዙ እምቦጭ፣ ደለልና ሌሎች ለሐይቁ ጠንቅ የሆኑ አዳዲስ አረሞችም እየተከሰቱ እንደሆነ ነው አንድ የምስራቅ ደንቢያ አርሶ አደር ለዶይቼ ቬሌ የገለፁት፡፡

« አረሙ ይበታትናል፣ ይሰባሰባል፣ እምቦጭ እየጨመረ ነው እንጂ እየቀነሰ አይደለም፣ የመከላከል ሥራው ከቆም ብዙ ጊዜ ሆኖታል፣ እሾክ ያላቸው ሌሎች አረሞችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሐይቁ ዳር ዳር እየታዩ ነው» ብለዋል፡፡

አረሙን ከሐይቁ ጠቅልሎ ማውጣት ባለመቻሉከሌሎች አካባቢዎች በሐይቁ ላይ በነፋስ ተገፍቶ የሚመጣ የእምቦጭ አረም በየጊዜው ወደ አካባቢያቸው እንደሚመጣ ሌላ አስተያየት ሰጪ አረሶ አደር አመልክተዋል፡፡



«ሶኬ» የተባለ መጤ አረም ለጣና ሐይቅ ሌላ ፈተና



በአማራ ክልል፣ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የአካባቢ ጥበቃናሥነ ምህዳር ተፋሰስ አያያዝ ቡድን መሪ አቶ መሰለ ተባባል በክልሉ ካለው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ አረሙን የማስወገድ ሥራ በመቆሙ በወረዳው፣ ጃርጃር፣ ጣና ወይና፣ አድሰጌ፣ አቻራና ሰራባ በተባሉ ቀበሌዎች የአረሙ ስርጭት በእጅጉ መስፋፋቱን ተናግረዋል፣ “ሶኬ” የተባለ አዲስ አረምም ሌላ ለሐይቁ ፈተና መሆኑን ያስረዱት አቶ መሰለ፣ ደለልም ለሐይቁ ህልውና ሌላ ችግር ሆኗል ነው ያሉት፡፡

«መገጭ፣ ድርማና ጉማራ የተባሉ ታላላቅ ወንዞች ከጎንድደር፣ ከቆላድባና ከማክሰንት ከተሞች የሚወጡ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ይዘው ወደ ሐይቁ ስለሚገቡ እነኒህ ወንዞች ከፍተኛ ደልለ በሐይቁ ላይ እየፈጠሩ ነው» ብለዋል፡፡



6000 ሄክታር የጣና ሐይቅ በእምቦጭ አረም ስለመወረሩ



በአማራ ክልል የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሀ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ የእምቦጭ አረም ማስወገድ አስተባባሪ አቶ ጤናው ምንውየለት በበኩላቸው ሐይቁን ከእምቦጭ አረም ለማስወገድ ሠፊ ሥራዎች ሲሰሩ መቆይታቸውን አስታውሰው፣ አሁን ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሥራውን በተፈለገው መጠን ማስወገድ አልተቻለም ብለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ወደ 2ሺህ800 ሄክታር የሚሽፍን አረም ከሐይቁ ማስወገድ ቢቻልም፣ አሁንም 6,000 ሄክታር የጣና ሐይቅ በአረሙ እንደተሸፈነ መሆኑን ገልጠዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም አረሙን በከፍተኛ የዘመቻ ሥራ መቀነስ የተቻለ ቢሆንም አሁን ያን ማድረግ ባለመቻሉ አረሙ እየተስፋፋ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዚህም ምክንያት አረሙ ከዚህ ቀደም ታይቶባቸው በማያውቁ በሰሜን ጎጃም አቸፈር ወረዳና በባሕር ዳርከተማ አስተዳደር የሐይቁ ዳርቻዎች መስፋፋቱን የሚናገሩት አቶ ጤናው፣ በባሕርዳር አባገሪማና ወራሚት በተባሉ አካባቢዎች ያለውን አረም በማሽንና በሠው ኃይል የማስወገድ ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ በሌሎች የደቡብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖ በሚገኙ ቀበሌዎች የመከላከል ሥራውን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውንም አቶ ጤናው ገልጠዋል፡፡



ውጋጅ አረሙን ለማንሳት የማሽንና የገልባጭ መኪና እጥረት ስለማጋጠሙ



ባሕር ዳር አካባቢ ከሐይቁ የሚወጣውን አረም ወደሌላ ቦታ ለመውሰድ የማንሻ ማሽንና ገልባጭ መኪና እጥርት እንዳጋጠማቸው የተናገሩት አስተባባሪው፣ የተከማቸው አረም በወቅቱ የማይነሳ ከሆነ ግን ወደ ሐይቁ እንደገና የመመለስና ሌሎች ችግሮችንም የሊፈጥር እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጠዋል፡፡ የማንሻ የማሽንና ገልባጭ መኪና ጥያቄን በተመለከተ ለአንድ የከተማ አስተዳድሩ ከፍተኛ ባለስልጣን ጥያቄውን አቅርበንላቸው፣ “ሌሎች ቢሮዎችን መጠየቅ ይችላሉ” የሚል ምላሽ ስጥተዋል፡፡

ወደ ሐይቁ የሚገቡ ታላላቅ ወንዞች መኖራቸውን ያስረዱት አቶ ጤናው፣ በየዓመቱ ወደ ሐይቁ የሚገባውን ደለል ለመከላከል አሁንም የተፈጠሮ ሀብት ሥራዎች በቅንጅት ተጠናክረው መሠራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

«እምቦጭ አሁንም ለጣና ሥጋት ነው»

«እምቦጭ አሁንም ለጣና ሥጋት ነው»

ዓለምነው መኮንን