DiscoverDW | Amharic - Newsየአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / ተማሪዎች ቅሬታ
የአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / ተማሪዎች ቅሬታ

የአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / ተማሪዎች ቅሬታ

Update: 2025-01-30
Share

Description

የአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / ተማሪዎች ቅሬታ



በዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ማርታ ዱማሎ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት የአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / መከታተል ከሚያሥፈልጋቸው ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት ፡፡ ለዚህም በያዝነው ዓመት መግቢያ ላይ በሠላሌ ዩኒቨርሲቲ መመደቧን የጠቀሰችው ማርታ “ ነገር ግን እኔን ጨምሮ ከአራት መቶ በላይ የምንሆን ተማሪዎች በፀጥታ ሥጋት እና ከቦታ ርቀት የተነሳ ወደዚያ መሄድ አልቻልንም ፡፡ በአቅራቢያችን የሚገኘው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው የትምህርት መረሃ ግብር ማስታወቂያ መሠረት በግል ለመከታተል ተመዘገብን ፡፡ ዩኒቨርሲቲውም መዝግቦና ክፍያ ተቀብሎ ጥር 2 2017 ዓም ትምህርት እንደሚጀምር በማስታወቂያ ከገለጸ በኋላ በመኻል መረሃ ግብሩ እንደማይካሄድ ተነገረን “ ብላለች ፡፡



“ ከሁለት ያጣ ሆነናል “



ልጃቸው ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ መመደቡንና ከቦታው ርቀት የተነሳ ወደዚያው ልከው ለማስተማር መቸገራቸውን የጠቀሱት ሌላው የተማሪ ወላጅ በበኩላቸው ተመሳሳይ ቅሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል ፡፡ ልጆቻችን እዚህ አማራጭ በማግኘታቸው ወደ ተመደቡበት ሳይሄዱ ቀርተዋል ያሉት አስተያየት ሰጪው “ አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲው ለመማር የተመዘገቡ ከአራት መቶ በላይተማሪዎች ትምህርት ሳይጀምሩ መኻል ላይ ቀርተዋል ፡፡ ወደ ተመደቡብት ሄደው እንዳይማሩ ጊዜው አልፏል ፡፡ እዚህ በግል በተመዘገቡበት የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንዳይጀምሩ ደግሞ ማስተማር አልችልም ብሏል ፡፡ በዚህም ምክንያት ከሁለት ያጡ ሆነዋል “ ብለዋል ፡፡



የተቋማቱ ዝምታ



ዶቼ ቬለ የተማሪ እና የዎላጆቹን ቅሬታ አስመልክቶ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል ፡፡ ሃላፊዎቹ ግን ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት ባለማሳየታቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም ፡፡ ያም ሆኖ ቅሬታቸውን ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ሃላፊዎች በደብዳቤ እና በአካል ማቅረባቸውን የተናገሩት ተማሪዎች እና ወላጆች ትምህርቱን መጀመር ያልተቻለው ከትምህርት ሚንስቴር በግል እንዳታስተምሩ የሚል መመሪያ በመተላለፉ መሆኑን በሃላፊዎቹ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡



ዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን ለማነጋገር ሁለት ጊዜ ቀጠሮ ካሲያዘ በኋላ ሃላፊው የሥልክ ጥሪ ባለመመለሳቸው የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱን አስተያየት ማካተት አልተቻለም ፡፡ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም ሆነ ትምህርት ሚንስቴርእስከአሁን በጉዳዩ ላይ ግልጽ ማብራሪያ ባይሰጡም ተማሪዎችና ወላጆች ግን አሁንም ለጥያቄያቸን ምላሽ እንጠብቃለን እያሉ ነው፡፡



ሸዋንግዛው ወጋየሁ



አዜብ ታደሰ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / ተማሪዎች ቅሬታ

የአቅም ማሻሻያ / ሪሚዲያል / ተማሪዎች ቅሬታ

ሸዋንግዛው ወጋየሁ