DiscoverDW | Amharic - Newsየዶቼቬለ የአማርኛዉ ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች ሲታወሱ
የዶቼቬለ የአማርኛዉ ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች ሲታወሱ

የዶቼቬለ የአማርኛዉ ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች ሲታወሱ

Update: 2025-04-06
Share

Description

የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች በጥቂቱ



ዶቼ ቬለ የሬድዮ ጣብያ በሚታወቅበት እና ደወል መሰለ ሙዚቃ የሚጀምረዉ የአማርኛዉ ስርጭት የሬድዮ ጣብያ፤ የስርጭቱ መግብያና መሰናበቻን ይናገር የነበረዉ አቶ አማኑኤል በረከት ነዉ። አቶ አማኑኤል በረከት ለረጅም ዓመታት የአማርኛዉ ክፍል ዋና ተጠሪ ብሎም የስፖርት ፤ የባህል እንዲሁም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀቱም ይታወቃል። አብዛኞች የዶቼቬለ ባልደረቦች የሚጠሩት ጋሽ አማኑኤል ሲሉም ነበር። አቶ አማኑኤል በረከት በተለይ ከአንጋፋዉ የዶቼቬለ ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ጋር ቅርበት ነበረዉ። አቶ አማኑኤል በረከት በጡረታ ከተገለለ በኋላ፤ ባደረበት ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ዓመታት ተቆጠሩ።



ሌላዉ በጡረታ የተገለለዉ የዶቼቬለ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ደስታ፤ ጡረታ እንደወጣ ኢትዮጵያ መኖር ከጀመረ በኋላ በየዓመቱ ወደ ጀርመን እየመጣ የቀድሞ መስርያ ቤት ባልደረቦቹን ይጠይቅ ነበር። ጋዜጠኛ ጌታቸዉ፤ ቀልጣፋ፤ ፈጣን ተግባቢ፤ እንዲሁም ቁም-ነገርን በቀልድ እያዋዛ በመናገሩ ይታወቃል። ሌላዉ በዶቼቬለ አድማጮች ዘንድ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈዉ፤ የጥንት የጠዋቱ ጋዜጠኛ ዘዉዱ ታደሰ ነዉ። ዘዉዱ ታደሰ፤ በሚጽፋቸዉ የተለያዩ ርዕሶች በቃላት አጠቃቀሙ እና ጥልቅ ጥናት እና መሰናዶ አድርጎ በማድረጉ ዝግጅቶቹ የተዋጣላቸዉ በሚል አድማጮች ያወድሱት ነበር።



እዉቁ እና ተወዳጅ የነበረዉ የዶቼቬለ ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ደግሞ፤ ባልደረቦቹ መዝገበ -ቃላት ነዉ ሲሉ ያደንቁታል። ተክሌ የኋላ በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ግጥሞቹም ይታወቃል። በመጨረሻዎቹ ዓመታት፤ ተክሌ የኋላ በአድማጮቹ ዘንድ በሳይንስ ዝግጅቶቹ ቢታወቅም ፤ በተለይ ባህል ነክ የሆኑ ነገሮችን በማቅረቡ ለዓመታት ሰርቷል። ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ በጡረታ ከተገለለ በኋላ በጀርመን ኮለኝ ከተማ ሲኖር፤ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በቅርቡ በሞት የተለየ የዶቼቬለ ባልደረባ ነበር። ጋዜጠኛ ማንተጋፍቶት ስለሺ ተክሌ የኋላ እምቅ የአማርኛ ቋንቋ ችሎታ የነበረዉ፤ ትዕግስት የተላበሰ ሲል ተክሌ የኋላን ያስታዉሳል።



ሌላዋ በጡረታ የተገለችዉ የዶቼቬለ አንጋፋ ጋዜጠኛ አርያም ተክሌ ናት። አርያም ተክሌ በአብዛኛዉ በየሳምንቱ የተለያዩ አፍሪቃ ሃገራት ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በመዘገቧ ትታወቃለች። አርያም ተክሌ ለብዙ ዓመታት የዶቼቬለ አማርኛዉ ቋንቋ ክፍል ምክትል አስዳዳሪ ሆናም አገልግላለች።



የዶቼቬለ የሀዋሳ ወኪል የነበረዉ ጋዜጠኛ ፀጋዬ እንደሻዉ፤ እንዲሁም የዶቼቬለ የአዲስ አበባ ወኪል ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ በሞያቸዉ የተደነቁ ጋዜጠኞች ነበሩ። በመኪና አደጋ በድንገት የተለየን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን በድንገተኛ ሞቱ ፤ የአማርኛዉን ክፍል ብቻ ሳይሆን የዶቼ ቬለ ከ33 በላይ ቋንቋ ክፍል አዘጋጆችን፤ እጅግ አስደንግጦ አሳዝኖአልም። ህጻናት ልጆቹን ባለቤቱን ቤተሰቡን በትኖ መቅረቱ የመላዉን ጣብያ ሰራተኞች አሳዝኗል። የጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ ስም እና ስራዉ በቋሚነት ተቀርጾ፤ ጀርመን ቦን ከተማ በሚገኘዉ ዋናዉ የዶቼቬለ የራድዮ ማሰራጫ ጣብያ መግብያ ላይ በማስታወሻነት ተለጥፎ ይታያል።



አንጋፋዉ ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ ፈጣን ታታሪ እንዲሁም በጣም ተባባሪ ሰራተኛ ነበር ሲል ገልጾታል። በጥሩታ የተገለለዉ የዶቼቬለ ጋዜጠኛ መስፍን መኮንን ፤ አብዛኞቹ ባልደረቦቹ ጨዋ ቁጥብ ታታሪ ሲሉ ይገልፁታል። መስፈን መኮንን በጀርመንኛ ቋንቋ ይጠበባል። በዚህም ምክንያንያ በዶቼቬለ ራድዮ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት አዘጋጅ ሆኖ ለረጅም ዓመታት አገልግሏል። መስፍን ከስፖርት ሌላ የኤኮኖሚ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ሆኖ ለረጅም ዓመታት አገልግሏል። ን በማዘጋጀቱም ይታወቃል።



ከቅርብ ዓመታት በፊት በሞት የተለየን የአዲስ አበባ የዶቼ ቬለ ወኪል ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ተድላ፤ በተለይ በአፍሪቃ ህብረት ስብሰባዎች ላይ እየተገኘ ይዘግብ የነበረ ጋዜጠኛ ነዉ ። ባልደረቦች ሁሉ ጋዜ ሲሉ ይጠሩት የነበረዉ ጌታቸዉ ተድላ፤ ከጋዜጠኝነቱ ባሻገር የዶቼ ቬለ ጋዜጠኞች ጀርመኖችን ጨምሮ የሌሎች ሃገር ጋዜጠኞች ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ መኪናዉን ይዞ ቦሌ ዓለምአቀፍ አዉሮፕላን ጣብያ ከእቅፍ አበባ ጋር ይቀበል የነበረ የዶቼቬለ ባልደረባ ነዉ።



በጀርመን ኮለን ከተማ ነዋሪ የሆነችዉ እና በጡረታ ላይ የምትገኘዉ ሌላዋ የቀድሞ የዶቼቬለ ጋዜጠኛ ንጋት ከተማ ናት። ጋዜጠኛ ንጋት፤ ከባልደረቦችዋ የበለጠ በምታዘጋጃቸዉ ፕሮግራሞችዋ ከዶቼቬለ አድማጮች ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራት ጋዜጠኛ ነበረች። ጋዜጠኛ ንጋት ከተማ ከዶቼ ቬሌ ራድዮ ቀደም ብላ በብስራተ ወንጌል ራድዮ ያገለገለች በዘርፉ በርካታ ልምድን ያካበተች ጋዜጠኛ ናት።



ከአስመራ ዘገባወችን ይልክልን የነበረዉ ሌላዉ የዶቼ ቬለ አንጋፋ ጋዜጠኛ ጎይቶም ቢሆን አድማጮች በተለይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ የድምበር ዉዝግብ ጦርነት ያስታዉሱታል። ጋዜጠኛ ጎይቶም ኤርትራ ከኢትዮጵያ ከመገንጠሏ በፊት አዲስ አበባ ላይ በብስራተ ወንጌል በጋዜጠኝነት ያገለገም ነበር። በኤርትራ ከተገነጠለች ወዲህ አስመራ ላይ ሆኖ ለዓመታት የዶቼ ቬለ ወኪል ሆኖ ያገለገለዉ ጎይቶም ቢሆን በጋዜጠኝነት ሞያዉ ኤርትራ ዉስጥ መቀመጥ ባለመቻሉ ወደ ጀርመን መጥቶ ፍራንክፈርት ከተማ አቅራብያ ሲኖር ሲኖር ባደረበት ህመም ከጥቂት ዓመታት በፊት በሞት ተለይቶናል።



ሌላዉ በተለይ በአነባበቡ በሚያወጣዉ ድምፅ እና ቅላፄ በሚጠቀማቸዉ ቃላቶች የማይረሳዉ የዶቼቬለዉ ጋዜጠኛ የበርሊን ወኪል ይልማ ኃይለሚካኤል በጡረታ ቢገለልም ከበርሊን በቀጭኑ ሽቦ ቦን ከሚገኙት ከቀድሞ ባልደረቦቹ ጋር ግንኙነቱን አላቋረጠም። መዲና በርሊን ለጉዳዩ ጎራ ያለ ይልማ ኃይለሚካኤልን ሳያገኝ የሚመለስ የለም።



በዶቼቬለ የአማርኛዉ አልያም በኢንጊሊዘኛዉ ክፍል አገልግለዉ ወደ ሌላ ስራ አልያም ወደ ትምህርት የተመለሱ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ይገኛሉ። ከነዚህ መካከል ሃሌሉያ ሉሌ፤ ዶ/ር መርጋ ዮናስ ቡላ፤ እንዲሁም ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ተጠቃሽ ናቸዉ።



ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን!

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የዶቼቬለ የአማርኛዉ ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች ሲታወሱ

የዶቼቬለ የአማርኛዉ ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች ሲታወሱ

Azeb Tadesse Hahn