ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት ተጨማሪ ማዕቀብና የዩክሬን ጦርነት
Update: 2025-10-24
Description
ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት በያዝነዉ ሳምንት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥለዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ሮዝኔፍና ሉክኦይል የተባሉ የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ኩባንዮች አሜሪካ ዉስጥ ያላቸዉ ሐብትና ንብረት እንዳይንቀሳቀስ አግዳለች።የአሜሪካ ኩባንዮችም ከሁለቱ ኩባንዮች ጋር እንዳይሰሩ ከልክላለች።የአዉሮጳ ሕብረት በበኩሉ የሕብረቱ አባል መንግሥታት ከሩሲያ ፈሳሽ ጋዝ እንዳይገዙ አግዷል።አዉሮጳ ባንኮች ዉስጥ የሚገኝ የሩሲያ ገንዘብን ለዩክሬን ለመስጠትም አባል ሐገራት እየተነጋገሩ ነዉ።
ዛሬ የአዉሮጳ ሐገራት መሪዎች ከዩክሬን ፕሬዝደንት ቮልዶሚር ዜለንስኪ ጋር ለንደን ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።የአዉሮጳና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የወሰዱት የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የዩክሬኑ ጦርነት ሥለሚቆምበት ብልሐት በቅርቡ ፑዳፔሽት-ሐጋሪ ዉስጥ ይነጋገራሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት መሆኑ ነዉ።ሥለ ማዕቀቡና ዉይይቱ የዋሽግተን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ
Comments
In Channel























