የፓሪሱ ሉቯር ቤተ መዘክር መዘረፍ ያስከተለዉ ሥጋትና ዉዝግብ
Update: 2025-10-24
Description
የፓሪስ-ፈረንሳይ ዕዉቅ ቤተ-መዘክር ሉቯር ባለፈዉ ሳምንት ዕሁድ መሠረቁ ያስከተለዉ ፖለቲካዊ ጥያቄና የደሕንነት ሥጋት የሐገሪቱን ፖለቲከኞችና ሕዝብ እያከራከረ ነዉ።መረጃዎች እንጠቆሙት ሌቦቹ ከዓለም ትልቁን የሥነ-ጥበብ ቤተ-መዘክርን በርካታ ቅርሶች በተለይም የወርቅና የብር መሐለቆችን ለመዝረፍ የፈጀባቸዉ ጊዜ 8 ደቂቃ አይሞላም።ሌቦቹ ከ2000 የሚበልጡ የወርቅና የብር መሐለቆችን ሰርቀዋል።ባጠቃላይ ከቤተ-መዘክሩ የተዘረፈዉ ንብረት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገምቷል።ተጠርጣሪዎቹ እስከ ዛሬ አልተያዙም።ቤተ-መዘክሩ የተዘረፈበት ፍጥነት፣ መንገድ ተመሳሳይ ዘረፋዎች መደጋገማቸዉ በፈረንሳይ ሕዝብ ዘንድ የደሕንነት ሥጋት አሳድሯል።ፖለቲከኞች በበኩላቸዉ እየተወቃቀሱ ነዉ።ዘረፋ፣ ሥጋት ክርክሩን በተመለከተ የፓሪስ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነሕን በሥልክ አነጋግሪያታለሁ።
ኃይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ
Comments
In Channel























