የዶቼ ቬለ አጭር ሞገድ ስርጭት ስንብት
Update: 2025-10-24
Description
የዶቼ ቬለ አጭር ሞገድ ስርጭት ስንብት
ዶቼ ቬለ በአጭር ሞገድ በአማርኛ ቋንቋ ሥርጭት ከጀመረ 60 ዓመት አለፈው። ከ30 በላይ በሆኑ የዓለም ቋንቋዎች የሚያሰራጨው ዶቼ ቬለ ከኢንተርኔት እና ሳተላይት ቴክኒዎሎጂ ጋር በተገናኘ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአጭር ሞገድ ስርጭቶችን አቋርጧል። ከፊታችን እሑድ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ደግሞ የአማርኛው የአጭር ሞገድ ስርጭት እንደሚቋረጥ ሰሞኑን ለመግለጽ ሞክረናል።
ለዚሁ የቴክኒዎሎጂ ሽግግር ሲልም ከአንድ ዓመት በፊት ገደማ ጀምሮ በኢትዮሳት የሳተላይት ስርጭት የጀመረ ሲሆን በዲጂታል አማራጮች ማለትም በፌስቡክ፤ በቴሌግራም፤ እንዲሁም በዩትዩብም የቀጥታ ስርጭቱን እያስተላለፈ ነው።
እናም የዶቼ ቬለ አድማጮች ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የሚያገኙን በኢትዮሳት ወይንም (NSS-12) በ10,985.0 ሜጋ ኸርዝ፣ ሆሪዞንታል፣ DW-08 ላይ ይሆናል። ትራንስፖንደሩ፦ ደግሞ MEH 01 ወይንም EAH 01 መሆኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን። በፌስቡክ፤ በቴሌግራም እና በዩትዩብም በየቀኑ የቀጥታ ስርጭት መተላለፉን ይቀጥላል። ይህን በተመለከተ የአድማጮችን አስተያየት ያካተተውን ልዩ ዝግጅት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ
Comments
In Channel























