DiscoverDW | Amharic - Newsየነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር
የነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ  በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር

የነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር

Update: 2025-01-15
Share

Description

ከጊዜ ወደጊዜ የሚያሻቅበው የቤንዚን ዋጋና ህገወጥ የነዳጅ ሽያጭ ሥራቸውን እንዳጎለባቸዉ የአማራ ክልል የህዝብ አገልግሎት ስጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች አስታወቁ።የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ ህገወጥነትን ለመከላከል እየሰራ እንደሆን አመልክቷል።ቢሮዉ ባልፉት 6 ወራት ብቻ 250ሺህ ሊትር ነዳጅ ዘይት በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙንም ቢሮዉ ገልጧል።አለምነዉ መኮንን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።



በተለያዩ የባሕር ዳር ከተማ ማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት ሰልፍ ይዘው ያገኘናችውና ለዶይቼ ቬሌ አስተያየታቸውን የሰጡ የባልሶስት እግር ታክሲና በተለምዶ የዳማት አነስተኛ ተሽከርካሪ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በየጊዜው በሚጭምረው የቤንዚን ዋጋ፣ ቤንዚን ለማግኘት በሚደረግ አሰልቺ ሰልፍና በህገወጥ የቤንዚን ዝውውር ተማርረዋል።



ነዳጅ ከማደያ ለመቅዳት ፈተናው ብዙ ነውተጠቃሚዎች



አስተያየታቸውን ከሰጡን ወጣቶች መካክል አንዱ “ቤንዚን ለመቅዳት ቀናት ማስቆጠሩን አመልክቶ አማራጭ በማጣት እንጂ ሥራውን የመስራት ፍላጎት የለኝም” ብሏል።



“ቤት ከመቀመጥ ወጥቶ መዋሉ ይሻላል ከሚል እንጂ ሥራው ትርፍ የለውም ነው” ያለው።



ሌላው አስተያየት ሰጪ ተሽከርካሪውን ከባንክ ብድር ወስዶ መግዛቱን ጠቅሶ በቤንዚን እጥረቱ ምክንያት ሰርቶ ብድር መመለስ እንዳልቻለ ገልጧል፣ አንዴ ነዳጅ ከቀዳ ሌላ ጊዜ ለመቅዳት ሳምንት እንደሚጥብቅ አመልክቷል፣ ያን ላለማድረግ ደግሞ በውድ ዋጋ ከህገወጥ ነጋዲዎች ቤንዚን ገዝቶ እንደሚሰራ ነው ያስረዳው። መንግሥት በነዳጅ ላይ ዋጋ ቢጭምርም በትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ባለማድረጉ ለኪሳራ እየተዳረጉ እንደሆነም አክሏል።



ቤት ላለመዋል እንጂ ሥራው አዋጪ አልሆን ብሏልየባጃጅ አሽከርካሪ



ሥራ ላልማቆም ሰሞኑን በተደረገው ጭማሪ መሰረት ከማድያ በ102 ብር መግዛት የሚቻለውን አንድ ሊትር ቤንዚን እስክ 300 ብር ከህገወጥ ነጋዴዎች ለመግዛት እንደተገደደ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ አንድ ነዳጅ ማደያ ቤንዚን ለመቅዳት ሰልፍ ይዞ ያገኘንው ወጣት ነግሮናል።



ሰልፍ ለምያዝ በቀን 100 ብር ለጥበቃ እንድሚክፍል የገለጠልን ሌላው ወጣት፣ “4 እና 5 ቀናት በምንቆምበት ወቅት እስከ 500 በር እንከፍላልን” ሲል አመልክቷል፣ በዚህ ሁኔት ሰርቶ ቤተስብ ለማስተዳደር እንደተቸገረ ገልጧል።



በህገወጥ ሲዘዋወር የነበር 250 ሺህ ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር ውሏልየአማራ ክልል ንግድና ገብያ ልማት ቢሮ



የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢብራሒም ሙሐመድ ባልፉት 6 ወራት ሀገወጥነትን ለመከላከል ሰፊ ሥራ መሰራቱን ጠቁመው በዚህም በህገወጥ መንግድ ሲዘዋወር የነበር 250 ሺህ ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት ገቢ ሆኗል ብለዋል።



የአማራ ክልል መንግሥት በነዳጅ ግብይትየሚታየውን ህገወጥነት ለመከላከል ትኩርት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆንም ኃላፊው ተናግረዋል።



“250 ነዳጅ ቦቴዎችና 19 ማደያዎች 6 ወራት ከሥራ ታግደዋልቀጥናዊ ትስስር ሚኒስቴር



የፌደራል ንግድና ቀጠናዊ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ በህገወጥ መንገድ ትርፍ ለማግኘት ከ10 እስከ 15 ቀናት ነዳጅ ጭነው ጥሻ ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 250 የነዳጅ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለው ቅጣት ተጥሎባቸዋል ብለዋል። 100 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን ለቅጣይ 6 ወራትም የነዳጅ ምርት እንዳያዘዋውሩ መታገዳቸው ተገልጧል፣ “ተባባሪ ነበሩ” የተባሉ 19 ማደያዎችም ለ6 ወራት ከግብይት መታገዳቸው በመግለጫው ተመልክቷል።



ዓለምነው መኮንን



ነጋሽ መሐመድ



አዜብ ታደሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ  በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር

የነዳጅ ዋጋ ንረትና ሥዉር ገበያ በአሽከርካሪዎች ላይ ያደረሰዉ ችግር