DiscoverDW | Amharic - News82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ
82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ

82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ

Update: 2025-12-15
Share

Description

82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ



82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው እና ወደ ሕብረተሰቡ እንዲዋሃዱ መደረጉ ተገለፀ።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሐ ግብር (UNDP) እንዳለው፤ የፕሪቴሪያው ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት አካል የሆነው የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማሕበረሰባቸው የማዋኃዱ ተግባር አሁንም የቀጠለ ነው።



በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፋኖ ቡድኖች አንዱ አንጃ የሆነው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ)፤ ባለፈው ሳምንት ከክልሉ መንግሥት ጋር አደረገ የተባለውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና የማዋሃድ ሥራ መጀመሩን የገለፁት የ UNDP የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ጋይዲ፣ ተመሳሳይ ያሉት ሥራ በኦሮሚያ ክልል ለማስጀመር ጥናት መጀመሩን እንደሚያውቁ ገልፀዋል።



የUNDP የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ጋይዲ በጦርነት የከፋ ገዳት ባስተናገደው በሰሜን ኢትዮጵያ ለሰላም፣ ለልማት የበለጠ ሀብት ፈሰስ የምናደርገው በግጭት የተጎዱ ማህበረሰቦችን ሕይወት ለማገዝና ለደረሰው ሰብአዊ ቀውስ የመከላከያ እርምጃ ለማጠናከር ነው ብለዋል። በድርጅት ሥር ያለው የሰላም ድጋፍ ተቋም ጥረት እና የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ አስፈትቶ ወደ ማህበረሰባቸው ለመቀላቀል በሚደረገው ጥረት በዚህ ዓመት ብቻ ወደ 60 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ ማድረጋቸውን ያስታወቁት ተወካዩ ይህም ግጭት እና ጦርነት ምን ያህል አውዳሚ እንደሆነ ማሳያ አድርገውታል። ይህ ገንዘብ ለልማትና ለዘላቂ ሰላም ቢውል ኖሮ ሊመጣ ይችል የነበረውን የዕድገት ሥራም በቁጭት ገልፀውታል። 82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ እንዲቀላቀሉ መደረጉንም ገልፀዋል።



"አሁን በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር እና በኦሮሚያ 82,000 የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ አስፈትተናል። ስለዚህ ወደ ማህበረሰቡ የማዋሃዱ ዘመቻ አሁንም ቀጥሏል። የሰላም ድጋፉ ማህበረሰቦችን፣ ኢኮኖሚያቸውን እና ሌሎችንም መልሶ ለመገንባት እየሞከረ ነው።" ኢትዮጵያ ለአፍሪካም ይሁን ለዓለም እጅግ በጣም ስትራቴጂካዊ ሀገር ናት ያሉት በተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ተወካይ ሀገሪቱ ከቀይ ባህር መገኛ እስከ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫነቷን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ሰላም ከመላው የአህጉሩ ሰላም ጋር የተቆራኘ መሆኑን ጠቅሰው አዳዲስ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማህበረሰቦች የማዋሃድ ጥረት መጀመሩን ገልፀዋል።



በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፋኖ ቡድኖች አንዱ አንጃ የሆነው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ)፤ ባለፈው ሳምንት ከክልሉ መንግሥት ጋር አደረገ የተባለውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና የማዋሃድ ሥራ መጀመሩንም ገልፀዋል። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ለዚህ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። "ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካሉት ቡድኖች አንዱ ጋር የሰላም ስምምነት በተደረገበት ወቅት እንኳን፣ ትጥቅ አስፈትቶ የማዋሃድ ሂደቶችን ለማጥናት ሞክረናል። በአማራም በተመሳሳይ ሁኔታ አንዳንድ የፋኖ ቡድኖች ከክልሉ መንግስት ጋር ለመደራደር በመቻላቸው እነዚያን ተዋጊዎች የማዋሃድ ተግባር ተጀምሯል።"



ዋናው "የውስጥ ሰላም ነው"

በሰሜን ኢትዮጵያ የተደረገው የእርስ በርስ ጦርነት ምንም እንኳን ምን ያህሉን ለሞት፣ ለቁስለት እና ለአካል ጉዳት የተዳረገ መሆኑ ቁጥሩ በውል ባይገለጽም፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታመናል። በዓለም ባንክ እና በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ በተደረገ የኪሳራ እና የጉዳት ግምገማ ግን ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ውድመት ማድረሱ አስቀድሞ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ጋይዲ ድርጅታቸው ባለፈው ሳምንት ለቀጣናው የሰላም ጥረት ከጀርመን የገንዘብ ድጋፍ ሲረከብ እንዳሉት ትክክለኛው ሰላም በሌሎች ጥረት የሚመጣ ሳይሆን በውስጥ ቁርጠኝነት መሆን ያለበት እና ከራሳቸው ከኢትዮጵያውያን መምጣት ያለበት ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

"በብዙ አገሮች ጦርነት ካለፉ በኋላ የጦርነት ድካም የሚባል ጊዜ አላቸው። የሰው ልጅ ስቃይ ስላዩ፣ የዓመፅ ፍርሃትን ስለተመለከቱ ፣ ከዚያም ዳግመኛ እንደማይደገም ይናገራሉ። ስለዚህ፣ ኢትዮጵያ እድል አላት፣ ጦርነት አጋጥሟችኋል፣ ሰላምን ለማስቀጠል የሚያስፈልገውን ለመገንባት ከዚያ ጦርነት የመማር እድል አላችሁ።"





ሰለሞን ሙጬ



አዜብ ታደሰ



ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ

82,000 የቀድሞ ተዋጊዎች በአራት ክልሎች ወደ መደበኛ ኑሮ መቀላቀላቸው ተገለፀ

ሰለሞን ሙጬ