DiscoverDW | Amharic - Newsበሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙ
በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙ

በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙ

Update: 2025-11-25
Share

Description

በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙ



በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ውስጥ ውጤታማ አገልግሎት አበርክተዋል የተባሉ ኢትዮጵያዉያንባለሙያዎች፣የዕውቅና ሽልማት አገኙ። በመላው ዓለም ከሚንቀሳቀሰው ''ፒፕል ቱ ፒፕል'' ዕውቅና ያገኙት እነዚህ ባለሙያዎች፣በሥራ አመራር፣በምርምርና በትምህርት የላቁ እንዲሁም አርኣያነት ያላቸው መሆናቸውን የድርጅቱ መስራችና ፕሬዚዳንት ዶክተር እናውጋው መሐሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር የ2025 ''የፒፕል ቱ ፒፕል'' ተሸላሚዎች፣በየተሰማሩበት ዘርፍ አስደናቂ ስኬት እና ተጽዕኖ ማሳደር የቻሉ ባለሙያዎች ናቸው ይላሉ፣ ዶክተር እናውጋው መሐሪ።



ሌሎችን ለበጎ ሥራ ማነሳሳት



''ፒፕል ቱ ፒፕል'' በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሕይወት ዘመን ስኬት፣ በማደግ ላይ ያለ ኮከብ ሽልማት፣ በማኅበረሰብ አስደናቂ ስራዎቸ ጥሩ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ፣ በወጣቶች ላይ የሚሰሩትን እናመሰግናለን በማለት እውቅና ይሰጣል።'' እንደ ዶክተር እናውጋው ገለፃ፣ የዕውቅና ሽልማቱ፣ ተሸላሚዎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለበጎ ሥራ እንዲያነሳሳ ተብሎ የሚካሄድ ነው።



"ዋናው ቁም ነገሩ ምንድነው? እንደ አገርም እንደ ማኅበረሰብም በየትኛውም በምኖርበት ሃገር፣ ግለሰቦች ከራሳቸው ሥራ፣ከራሳቸው ኑሮ ወጣ ብላው ሌላውን ወገን፣ አገር ለመርዳት በበጎ ፍቃደኝነት የሚያደርጉት ሥራ፣ በሙያቸውም ቢሆን ረጅም ዓመት ላበረከቱት ሥራ እናመሰግናለን ማለት ይገባል። ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ያጠነክራል፣ለላውንም ያበረታታል ስለዚህ በየዓመቱ፣"ፒፕል ቱ ፒፕል'' ይህንን ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።''



ነጻ የሕግ አገልግሎት በመስጠት የተሸለሙት ባለሙያ



ከአምስቱ ተሸላሚዎች መኻከል፣ ጠበቃ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፣ በኮቪድ ወቅትና በኋላ በነበረው አስቸጋሪ ጊዜ፣ለኢትዮጵያውያን ነጻ የህግ አገልግሎት በመስጠት መብታቸው እንዲከበር ማድረጋቸዉ ተነግሮላቸዋል። ሽልማቱን አስመልክቶ፣ዶቼ ቬለ አስተያየት የጠየቃቸው ጠበቃ ደረጄ እንደሚከተለው መልሰዋል። ''እንዲህ ዓይነት ዕውቅና ሌሎችንም የሚያበረታታ ነው።ኢትዮጵያውያኖች በአሜሪካ ያለን የተለያዩ የሕግ ችግሮች ያጋጥመናል።እና በመላው አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውኖች የሚያስፈልጋቸው የሕግ ድጋፍ በጣም ሰፊ ስለሆነ፤ ሌሎች ጠበቆችንም የተለያየ አስተዋጽኦ ያድርጉ እንዲያደርጉ የሚያደርጉም አሉ።እኔ የማውቃቸው ብዙ የሚያበረታታ ነው።እኔ ብዙ የምሰራው በግለሰብ መብት አካባቢ ነው። በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ያሉ ጉዳዮች ያጋጥሙኛል።እና ያንን ደግሞ ወደፊት በተጠናከረ መልኩ ለመስራት የሚያበረታታኝ ነው፤ እኔም ብዙ ያስብኩዋቸው ፕሮጀክቶች አሉ።''



በማደግ ላይ ያለ ኮከብ



ሌላው የእንስሳት ሳይንስ ባለሙያ የሆኑት፣ በማደግ ላይ ያለ ኮከብ ተሸላሚ ዶክተር ዘላለም መኩሪያ፣ሽልማቱን በተመለከተ ጠይቀናቸዉ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተውናል።

"እኔ ጋርም ሆነ ከእኔ በፊት የተሸለሙት ሰዎች በደምብ፣ በትልቅ ደረጃ ብዙ ሥራዎች የሰሩ፣ እንዲሁም ደግሞ ተጠቁመው በደንብ ታይተው ሥራቸው ተገልጾ የተሸለሙ ስለሆነ ክብር ይሰማኛል። ለወደፊት መሥራት ላለብኝ ስንቅ የሚሆን ሽልማት ነው ብዬ ነው የማስበው።''



የዕውቀት ሽግግር

''ፒፕል ቱ ፒፕል'' የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ በዕውቀት ለመደገፍ አሜሪካ ውስጥ ተቋቁሞ፣ በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድስቴትስ፣ ካናዳ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ ውስጥ የሚንቀሳቀስ 100 ሺህ የሚሆኑ አባላት ያሉት ድርጅት ነው። ድርጅቱ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች፣ በጤና፣በትምህርት፣በምጣኔ ሃብትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስተባብራል። በዚህ መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ለመቆጣጠር፣ የጤና ጥበቃን አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ ላይ ለመሰማራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ፕሬዝደንቱ ዶክተር እናውጋው ገልጸውልናል።

"በመሠረቱ ኢንፌክሽን የተባለን ነገር፣ መከላከል ይቻላል። ለመከላከል ደግሞ መረጃ ያስፈልጋል። እና ሕዝባችንን በደንብ መረጃ ከሰጠነው፣ፖሊሲ አውጪዎች ጥሩ ግንዛቤ ካላቸው፣ ኤክስፐርት ከሆኑ ሰዎች ጋር ባለሙያዎችን አምጥቶ ሃገርንና እና ህዝብን ፖሊሲ አውጪዎችን መምከር ትልቅ አገልግሎት ነው ብለን ስለምናምን አብረን እየሰራን ነው።''



ታሪኩ ኃይሉ



ታምራት ዲንሳ



ነጋሽ መሐመድ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙ

በሥራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ተሸለሙ

ታሪኩ ኃይሉ